Saturday 30 June 2018

ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ተሰጠ ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው እምነት ሁሉ አልታደስም ቢል እንኳ ፈጥኖ ይታደሳልለክርስቲያኖች ሁሉ የሚጠቅም ድንቅ ውይይት ፦ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ተሰጠ ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያላረጋገጠው እምነት ሁሉ አልታደስም ቢል እንኳ ፈጥኖ ይታደሳል የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን ፣ ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠ ነውና ኦርቶዶክስ አትታደስም በሚል ሽፋን ፣ በሀገራችን ፣ በተለይም በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከልካይ ሳይኖራቸው ተዘፍዝፈውና ተወዝፈው ያሉ የገድላትና የድርሳናት ጥርቅሞች እንዲሁም ባዕዳን የሆኑ የጥንቆላና የአስማት ልምምዶች የቆሻሻ ያክል ተጠርገው ጋርቤጅ የሚጣሉበት ፣ ጊዜያቸውም ደርሶ የሚቃጠሉበት ዘመን እየመጣ ስላለ ይህ ትምህርት ቃሉ የተጻፈበትን ሃሳብ ተከትሎ በእንዲህ መልኩ ዛሬ ወደ እናንተ ቀርቦአል :: ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠው መጽሐፉ እንደሚነግረን ሃይማኖት ሳይሆን እምነት ነው :: ለዚህም አስረጂ እንዲሆነን መደበኛውን የመጽሐፍቅዱስ ትርጉምና የእንግሊዘኛውን መጽሐፍ ቅዱስ መመልከት በቂ ነው( የይሁዳ መልዕክት 1 ፥ 3 ):: እግዚአብሔር ሃይማኖተኛ ሰዎችን ማፍራት አይፈልግምና ሃይማኖትን ለሰዎች አልሰጠም ፣ ሰጥቶም አያቅም ፣ ወደፊትም አይሰጥም :: እግዚአብሔር የሰጠን ግን እምነት ስለሆነ ፣ በቃሉ የሆነውን እምነት የሰጠን አንድ ጊዜ ነው :: ታድያ ከእግዚአብሔር አንድ ጊዜ የተሰጣትን በቃሉ የሆነን እምነት ያላወቀች ይህቺው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፣ ከያዘቻቸው ደባል ተረቶችና ጥንቆላዎች የተነሳ ይኸው የተሃድሶ ነፋስ ከዛሬ ነገ ያገኘኝና ሥር ነቀል በሆነ ለውጥ ያድሰኛል የሚል ፍርሃት ይዞአት እንቅልፍ የነሳት በመሆኑ እውነትን የያዘች ለመምሰል ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠ ነውና ኦርቶዶክስ አትታደስም ስትል መከላከያ የመሰሉ ቃሎችን ልታቀርብ ትሞክራለች :: የተሃድሶ ንቅናቄ ግን በእግዚአብሔር ችሎትና በመንፈስቅዱስ ጉልበት ጉያዋ ውስጥ ገብቶ ሃይማኖት አንድ ጊዜ ተሰጥቶኛልና አልታደስም ስትል ብታቅራራም እንኳ ላይቀርልሽ ሲል እያደሳትና ተረትዋንም ሆነ ጥንቆላዋን እያስጣላት ይገኛል :: ክብሩ ለወደደን ፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለነገሥታቱ ንጉሥ ለኢየሱስ ይሁንለት አሜን:: ታድያ የዛሬውም ትምህርት የሚያመላክተው ይህንኑ ነው :: ከዚህም ሌላ መናፍቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ መናፍቅ ማን እንደሆነ ፣ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ መናፍቅ በሚለው ዙርያ ምን ዓይነት አቋም እንደነበራቸውና ምን እንደተባሉ ትምህርቱ በሰፊው ያትታል ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ተከታተሉ በትምህርቱም ተባረኩ ፣ ለሌሎችም ሼር ማድረግን አትርሱ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከተሃድሶ ለኦርቶዶክስ አገልግሎት

Thursday 28 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 9 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳየማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነንየውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ ወደ አማርኛው ስተረጉመው የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን የሚለውን ትርጉም ይሰጠናልና ይህ የዛሬው ትምህርት ለዚህ ሃሳብ የማሳረግያና የማጠቃለያ ትምህርት ነው በዛሬው ዕለት በፌስቡክ የላይቭ ቪዲዮ እንደ ትተከታተላችሁት የኢየሱስ ቁጣው ምክንያታዊ መሆኑን የሚገልጹ መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃን የያዙ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል እንደገናም ከዚሁ ጋር በንጽጽር ፈሪሳውያን ተቆጥተዋል ፣ ሰውንም ለመውገር ድንጋይ አንስተዋል ይሁን እንጂ የእነዚህ የሕግ መምህራን ቁጣቸውም ሆነ ለመውገር ድንጋይ ማንሳታቸው ሌላውን ሳይሆን እነርሱን የሚመለከትና ከእነርሱም የሚጀምር መሆኑን ፣ በአጠቃላይ ከእኛ ያልጀመረ ፣ እኛንም ያላማከለ ቁጣም ሆነ ፍርድ ለሌላው ሊሆንና ሌላውንም ሊበይን እንደማይችል በዝርዝር አይተናል በተጨማሪም እኛ ሌላውን እንቆጣለን ፣ በሌላውም ላይ እንፈርዳለን ስንል በተነሣሣንበትና አፋችንንም ሞልተን በተናገርንበት አንደበታችን በትላንቱ ዘመን ለዳዊት የተላከው ዮናታን ሳይሆን ዛሬ ላይ የኢየሱስን ቦታ ተክቶ በምድር ሁሉ ላይ በምልዓት የሚሰራው መንፈስቅዱስ መልዕክቱን ወደየግል ሕይወታችንና ወደ ራሳችንም ጭምር አዙሮ ያ ሰው አንተነህ ይለናል ያኔ ምን እንል ይሆን ? እግዚአብሔር ሆይ ተሳስተሃል !ወይንስ እኔ አይደለሁምና ሌላ ሌላ ሰው ነው ልንል ?መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ ለማንኛውም ግን ለሕይወታችን ጥቅምና ጥሩ ማስገንዘብያ እንዲሆን 2ኛ ሳሙኤል 12 ን በሙሉ እንድታነቡ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጋብዛለሁ በዚህ ውስጥ ታድያ ዳዊት ሙሉ ለሙሉ ስሕተቱን አምኖ ናታንን እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው ናታንም ዳዊትን እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል አትሞትም አለው ይለናል እኛስ ዛሬ በናታን ቦታ ብንሆንና እንደ ዳዊት ያሉ ሰዎች ጥፋትን አጥፍተው ፣ ጥፋታቸውንም አምነው እግዚአብሔርን በድያለሁ ሲሉ ወደ እኛ ቢመጡ የምንሰጣቸው መልስ ምን ይሆን ? አሁንም መልሱን ለእናንተ መተው እፈልጋለሁ ሆኖም ግን ከዚህ የብሉይ ኪዳን ምንባብ አኳያ ዛሬ ላይ ያለነው በሐዲስ ኪዳን ዘመን ውስጥ በመሆኑ የበደሉ ሰዎች እግዚአብሔርን በድያለሁ ሲሉ የሚመጡትና ኃጢአታቸውንም የሚናዘዙት ለዚሁ ለጌታችን ስለሆነ ይሄው እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን በኩል ለሁሉም የሚሆን መልስ አለው ወደ ተነሳንበት የመጀመርያው ሃሳብ ስንገባ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቁጣ የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ እንደተናገረው መዓትን የተሞላ ቁጣ ሆኖ የማርያምም ሆነ የሌሎች ቅዱሳን ምልጃ የሚያስፈልገው አይደለም ከዚህ ይልቅ ቁጣው ምክንያታዊ በመሆኑ ሚዛናዊ ነው ከዚህም የተነሳ ነው እንግዲህ ፦ ___ የማዳንህን ጋሻ ስጠኝ ተግሣጽህም አሳደገኝ ( 2ኛ ሳሙኤል 22 ፥ 36 ) ___ ለደኅንነቴ መታመኛን ሰጠኸኝ ቀኝህም ትረዳኛለች ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች ተግሣጽህም ታስተምረኛለች ( መዝሙር 18 ፥ 35 ) ___ መገሰጽስ እግዚአብሔር ገሰጸኝ ለሞት ግን አልሰጠኝም ( መዝሙር 118 ፥ 18 ) ___ ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው ሞገሱ ለሕይወት ዘመን ልቅሶ ማታ ይመጣል ጠዋት ግን ደስታ ይሆናል ( መዝሙር 30 ፥ 5 ) ___ በዚያም ቀን አቤቱ ተቆጥተኸኛልና ቁጣህንም ከእኔ መልሰሃልና አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ ( ትንቢተ ኢሳይያስ 12 ፥ 1 ) በማለት እነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የተናገሩት የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ይባርክልን ለበለጠ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday 26 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 8 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳየማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነንየውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 መጽሐፈ ሰዓታት የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ማለቱ ኢየሱስ የተቆጣ ፣ መዓትንም ሊያወርድ የተዘጋጀ ስለሆነና ከዚህም የተነሣ የማርያም ምልጃ ያስፈለገው ሆኖ አይደለም :: እርሱ ከቁጣ ሊያድነን ፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ የተቀበለልን ጌታ ነው :: ነገር ግን አሁም መጽሐፈ ሰዓታት የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ማለቱ የተአምረ ኢየሱስን ድርሳን ለመቀበልና ሃሳቡንም ትክክል ነው ሲል በመስማማት ሊያጸድቀው ፈልጎ ነው :: ከዚህ በመቀጠል የተአምረ ኢየሱስን መጽሐፍ ውሸትና ቅጥፈት በሙሉ የሚደረምስ የአምላክ ቃል በመጽሐፍቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ይገኛል ተአምረ ኢየሱስ ኢየሱስ በልጅነቱ ምልክቶችን ( ተአምራትን ) ሰርቷል ሲል ውሸቱን ይናገራል መጽሐፍቅዱስ ደግሞ እንዲህ ሲል እውነቱን ይናገራል ኢየሱስ በልጅነቱ ምንም ምልክት ( ተአምር ) አልሰራም እርሱ ምልክት ተአምር የሚሰራው ሰዎችን ወይም ራሱን ለማዝናናት ሳይሆን ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑበት ብቻ ነው ዮሐንስ 2 ፥ 11 የተአምረ ኢየሱስ መጽሐፍ እውነተኛና ጥንታዊም ነው እንዲባል በቶማስ ስም ተጠርቷል :: የቶማስ ወንጌልም ተብሎአል :: ታድያ ኢየሱስ በዚህ ድርሳን ላይ እንደ ተአምረኛ ሳይሆን እንደ አዝናኝ ( ሰዎችን እንደሚያዝናና ) አስማተኛ ሆኖ ቀርቦአል :: ከዚህም ሌላ ነፍሰ ገዳይም ሆኖ ቀርቦአል :: አንድ የሰፈራቸውን ልጅ ከሞት ካስነሳ በኋላ የአንዲት ጥያቄ መልስ ከእርሱ ጠይቆ ሰማና ወዲያውኑ መልሶ ገድሎታል ይላል ልብ ወለዱ የተአምረ ኢየሱስ መጽሐፍ:: ታድያ ለዚህ ይመስላል የመጽሐፈ ሰዓታት ጸሐፊ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን ያለው :: አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሰውን ዘር ለማዳን የመጣ ፣ ማንንም ከቶ ያልገደለ ፣ ነገር ግን ለጠላቶቹ ሳይቀር ምሕረትን የለመነ የፍቅር ጌታ ነው :: በመሆኑም ነፍሰ ገዳይ ነው ሲሉ ለኢየሱስ ስም መስጠት ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን በጎ ባሕርይ ሳይቀር አለመረዳትና ስሙንም ማጥፋት ነው :: ከዚህ የተነሣ ይህን የመሠለ ተአምር መሠል ተረት ለሰማው ሰው ሳይቀር እጅግ አሳፋሪ በመሆኑ የሀገራችን ሰዎች እንኳ ወንጌል ብለው ለመጥራት ቀፎአቸዋል :: ከወንጌል ጋር ተዳብሎ እንዳይሰበክ በማሰብም ተአምረ ኢየሱስ ሲሉ በልዩ ስም ሰይመውታል :: በተጨማሪም የወንጌልን መደብ ከልክለውት የድርሳናትን መደብ አስይዘውታል :: ይሁን እንጂ ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ አሁንም ጎደሎ አይደለም ፣ ስለ ኢየሱስ የልጅነት ዘመን በቂ መረጃን ይሰጠናል ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር የጀመረው በሠላሳ ዓመቱ ሲሆን የመጀመርያውንም ተአምራት ያደረገው በገሊላ ቃና ሠርግ ላይ ነው :: መጽሐፍቅዱሳችንም ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመርያ በገሊላ ቃና አደረገ ክብሩንም ገለጠ ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ ይለናል የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 11:: ታድያ ከዚያ በፊት የት ነበር ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ በአጭሩ ናዝሬት ነበር ነው :: የናዝሬት ሰዎችም የኢየሱስን ድንቅ ትምህርት ሰምተው ያልተቀበሉት ፣ በመሀከላቸው ስላደገና ስለኖረ ነው :: ኢየሱስም ነቢይ በሀገሩ አይከበርም ያለባት ከተማ ናዝሬት ስለሆነች ኢየሱስ ናዝሬት ከተማ ውስጥ እንደነበረ ያሳየናል ማቴዎስ 13 ፥ 53 _ 58 መልዕክቴን ስጠቀልለው ዛሬም ታድያ በአሁኑ ዘመን ባለች በማንኛዋም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመሀላችን ወገኖች ሲቀቡ የቅናት መንፈስ ይጫወትብናል አዛውንት አባቶቻችንም በምሳሌያቸው ሊያስረዱን አወኩሽ ናኩሽ ያሉን ለዚህ ነው በመሆኑም ከነዚህና ከመሳሰሉት መጽሐፍቅዱሳዊ ምክሮች በመነሳት ጌታ እግዚአብሔር መናናቃችንን አስወግዶ ፣ ዘለቄታዊ ያለው የመቀባበል ፈውስ ለኦርቶዶክሳዊቷ ብቻ ሳይሆን በዘመናችን ላለች ለየትኛዋም ቤተክርስቲያን ያምጣልን እላለሁኝ ተባረኩልኝ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

Monday 18 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 6 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነን የውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በክፍል አራት ቁጥር ስድስት የተመለከትነው ሃሳብ በአጭሩ ድንግል ማርያም ከኢየሱስ ይልቅ የቀረበችን ሆና ጸሎትዋና ልመናዋ ከልጇ ቊጣ ሊያድነን እንደማይችል ፣ እንደገናም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሊቀበልልን የመጣ ጌታ እንጂ ሊቆጣንና የእግዚአብሔርንም ቁጣ በእኛ ላይ ሊያወርድብን የመጣ ጌታ አለመሆኑን ፣ ከዚህም ሌላ ደግሞ ከማርያም ይልቅ በብዙ የሚቀርበን ፣ መቅረቡም ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለማርያምም ጭምር የሆነ በመሆኑ በአጠቃላይ ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራን ያላፈረብንና ከእንግዲህም ወዲህ ባሮቼ አልላችሁም ወዳጆቼ ብያችኋለሁ ከአብ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ ነገርኳችሁ ያለን መሆኑ ከእግዚአብሔር ቁጣ አዳነን ስንል ደግሞ ያዳነን በደሙ መሆኑን ከዚህ የተነሳ ደሙ ሥርየታችን ፣ ቤዛችን ፣ መታጠብያችንም ሆነ መጽድቅያችን መሆኑን ከእግዚአብሔር ቃል በማስረጃ ተምረናል አያይዘንም የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሠርያልና በመሰውያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተሥረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት ይለናል ( ዘሌዋውያን 17 ፥ 11 ) በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ለእኛ መስዋዕት መሆን አስፈለገው ታድያ ቃሉም እንደዚህ ይለናል እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ዕብራውያን 10 ፥ 19 _ 25 ወገኖቼ የተመረቀ መንገድ አለ በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት የሆነን ታድያ ይሄ መንገድ የተመረቀው በኢየሱስ ደም ነው በመሆኑም ከዚህ ከኢየሱስ ደም ውጪ ሌላ መግቢያም ሆነ መተላለፍያ መንገድ እና በር በፍጹም የለም ትምህርቱ የሚያስታውሰን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ሰምታችሁ ተባረኩበት ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

Saturday 16 June 2018

ለተሐድሶ የተሰጠ መልስ ክፍል 1 በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፤ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፤መጋቢ ሐዲስ እሸቱ እና ዲያቆን ያረ...ያበሳጨን ፣ ጠበኛም ያደረገን ፣ አልፎም በሕይወታችን ያታገለንና ያስለቀሰን ወንጌል ፣ ሌባ ሆኖ የሚሰርቀን ሳይሆን ሕይወት ሆኖ ሊያድነን የመጣ ነው ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ። መዝሙረ ዳዊት 119 : 71 ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። ትንቢተ ሆሴዕ 12 : 5 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኦርቶዶክሳውያን እናቶችና አባቶች እንዲሁም ይህን ትምህርት የተከታተላችሁ ወገኖች በሙሉ እንደምን ሰንብታችኋል ከተወደደው የእግዚአብሔር አገልጋይ ቢንያም ወርቅነህ ጋር የለቀቅነው የዛሬው መልዕክት በጣም ወሳኝና አስፈላጊ የሆነ የጊዘው መልዕክት ነውና ደግማችሁ በማዳመጥ እንድትጠቀሙ እንድትባረኩበትም ለማስተላለፍ እወዳለሁ:: በነገው ዕለት ቅዳሜም የምንነጋገርበት ትምህርት በተለመደው ሰዓት ይቀጥላል ::ስለዚህ ለማናችሁም መቅረት አይፈቀድም :: የዛሬው መልዕክት ግን በመረጥኩት የትምህርት አርዕስትና አስረጂ ጥቅሶች መሠረት የቀጠለ ነው :: ይሁን እንጂ ታድያ ይህንንም እንድል የሆንኩበት ዋነኛ ጉዳይ ከብዙዎቻችን ሕይወት ውስጥ ከሚወጣው ብስጩነት ፣ ንዴት ፣ ቁጣ ፣ መሳደብ አልፎም ሄዶ ከውስጣችን ፈንቅሎ ከወጣው ልቅሶና ምሬት የተነሳ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ስለገባን ውጤቱ ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ ምን ሊሆን እንደሚችል ከመረዳትና ከመገንዘብ አንጻር ነው :: ለዚህም ሁኔታ አንድ ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልገኝ አባት ማለትም ጳጳስ ናቸው በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ መሠረት ተቆርቁረው ሲያለቅሱ ሰማናቸው :: እኔም የማከብራቸውና የምወዳቸው ቀደምት አባታችን እንደመሆናቸው መጠን ፣ ልቅሶአቸው ከንክኖኝ ብፁዕ አባታችንን ምን ሆድ የሚያስብስ ነገር ቢገጥማቸው ነው እንዲህ ተንሰቅስቀው ማልቀሳቸው ? ብዬ በጉዳዩ በማዘን የተለቀቀውን የቪዲዮ መልዕክት ፍጻሜ ለማየት ስሞክር ለካስ የብጹዕ አባታችን ትልቁ ስጋታቸውና ልቅሶአቸው እንደገናም ፣ በልቅሶአቸውም ለሕዝባቸው ሊነግሩትና ሊያስተላልፉት የፈለጉት መልዕክት ፣ እንዳትሠረቁ ፣ ራሳችሁንም እንዳታሰርቁ ተጠንቀቁ የሚል ነው :: እንደ ብፁዕ አባታችን አመለካከት ይሰርቀናል ሲሉ የሰጉበትና ያለቀሱበት ትልቁ ወሬ ፣ በኢየሱስ ምክንያት የመጣ የኢየሱስ ወሬ ነው :: ታድያ ይሄ ትልቁ በኢየሱስ የተገኘ የኢየሱስ ወሬ የብዙዎችን ሕይወት የሠረቀ ነው ብለን ባናስብም ኢየሱስ ሕይወት ሊሆነን ሊበዛልንም የመጣ ጌታ በመሆኑ የብዙ ሰዎችን ሕይወት የለወጠ ነው :: በመሆኑም ታድያ ብዙዎቹ ብፁዕ አባታችን እንዳሉት ፣ በኢየሱስ ተሠርቀው ሳይሆን ተለውጠው ወደ ኢየሱስ የመጡ ናቸው :: ኢየሱስ እንደዚያ እንደ ክፉው ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የመጣ ጌታ ሳይሆን ሕይወት ሊሆንልንና ሊበዛልን የመጣ ጌታ ነው የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 10 :: ኢየሱስ እውነተኛ የበጎች በር ፣ በበሩም የሚገባ ጌታና መልካምም እረኛ ስለሆነ መስረቅ ወይንም ስርቆት የሚባል ነገር በእርሱ ዘንድ አይታሰብም :: ለዚህ ጌታ አንድ እውነት እንደ ቃሉ የምንናገርለት ነገር ቢኖር ፣ ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምጼንም ይሰማሉ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ በማለቱ ፣ ከዚህ ወርቃማ እና አምላካዊ ቃል የተነሳ ስርቆት ብለን ብናስብ ኃጢአት ይሆንብናል :: ነገር ግን አንድና አንድ እውነት ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ያለው ኢየሱስ ነውና እርሱ ሁሉን የሚችል ጌታ በመሆኑ ማምጣቱ አይቀርም የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 16 :: ስለዚህ ከዚህ መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት አንጻር ብጹዕ አባታችን በመሪር እንባቸው ፣ ኢየሱስን ይሰርቀናል ሲሉ ሳይሆን ይለውጠናል ሲሉ የሰጉ አስመስሏቸዋል :: ይህ ብቻ አይደለም ይሄ ጀግና ኢየሱስ መለወጥ ከጀመረ ማንንም የማይምር በመሆኑ ፣ በኢየሱስ ምክንያት እንደ ሰደድ እሳት የተቀጣጠለው የወንጌሉ እውነት በመለወጥ ጉዳይ ከያዘ በቀላሉ የማይለቅ በመሆኑ ፣ ጳጳሱ ብፁዕ አባታችን ጨንቋቸው እንዳትሠረቁ ራሳችሁንም እንዳታሰርቁ ሲሉ ሕዝቡን በእንባ ተማጸኑ :: ታድያ ይህንን የብፁዕነታቸውን ጽኑ ልቅሶ አይቼ ወዲያው እኔም ለእኚህ አባት ካዘንኩበት ሰመመኔ ፈጥኜ ነቃሁና አንድ ነገር አሰብኩ :: ያዘንኩላቸው ስለማውቃቸው ፣ አረጋዊ አባትና ብፁዕ አባታችንም ስለሆኑ በመንፈሴ ሳይሆን በሥጋዬ ነው ብዬ አስተዋልኩ :: አስከትዬም የለውጥ ያለህና በአባቶቻችን አፈርን ሲሉ በመጽሐፎቻቸው ወደ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ፣ እንዲሁም ወደ ሕዝባቸውም ጭምር የጮሁትን ጠንካራ የመጽሐፉ አዘጋጆችና የለውጥ አራማጆች የሆኑ የተሃድሶ አገልጋዮችን ጽሑፍ ሳስታውስ ፣ የብጹዕ አባታችን ልቅሶ ፣ ሹሉዳው እንደተነካ እንደ ያዕቆብ ለመለወጥ የሆነ ልቅሶ እንደ ሆነ ገባኝ እና እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመርኩኝ :: ታድያ ይህ ልቅሶ ያዕቆብ ጋ የቀረ ብቻ ሳይሆን ፣ ተንከባሎ መጥቶ ብፁዕነታቸው ጋር የደረሰ ፣ በዚህም ሳያቆም ብዙዎች ቤት ውስጥ ሳይቀር ሳይታሰብ በድንገት የገባ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ጌታን ለማመስገን ነፍስም አልቀረልኝ :: ለምን ብትሉ በአባቶቻችን አፈርን ፣ የለውጥ ያለህንና ሌላም ሌላም ሲሉ የጻፉ ሰዎች በመጽሐፎቻቸው የጮሁትን ጩኸት እግዚአብሔር ስለሰማ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለውጥን ፈልጋው ሳይሆን ሳትፈልገውም ቢሆን የግድ ጉያዋና መቅደስዋ ፣ ካቴድራሎችዋና መንበረ ጵጵስናዎችዋ ድረስ ሳይቀር እየገባ ፣ ከክብር ወደ ክብርም እየለወጣት ይገኛል :: ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁንለት :: ከዚህም ሌላ ይህንን ለውጥ እያደረገ ያለው እግዚአብሔር ስለሆነ ፣ ይህን እግዚአብሔርን ማንም አያቆመውም :: ይህ የለውጥ ውሽንፍር ደግሞ ወንጌላውያን አማኞች ቤተክርስቲያን ድረስ በመግባት ፣ በለውጥ ያልተቃኙ አማኞችንና አንዳንድ ሥጋውያን ፓስተሮችን ሳይቀር መለወጡ አይቀርም ብዬ አምናለሁ :: ለውጥ ደግሞ ለውጥ ነውና ፣ አንድ ጊዜ በምድሪቱ ላይ ይምጣ እንጂ ሰዎችን አይመርጥም ፣ በዚህ ጉዳይ ፣ እኔም በዘመኔ ለእግዚአብሔር እውነት ያልተገኙና በመንፈስቅዱስ ያልተሞሉ ፣ የመንፈስቅዱስም ተቃራኒዎች የሆኑ ትልልቅ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ፣ ጊዜያቸው መጥቶ መንፈስቅዱስ ሲያንደባልላቸው ፣ በመንፈስቅዱስም ሲሞሉ በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ :: ይህ ብቻ አይደለም ከዚሁ ከመንፈስቅዱስ ሙላት የተነሳም በብዙ አገልጋዮች ሕይወት ተለጥፎ ያለ አቡዋራና ጥቀርሻ እንዲሁም ያልተገራ ባሕርዮቻቸው ጭምር በዚሁ በመጣው በመንፈስቅዱስ ሙላት ከውስጣቸው ተራግፎላቸውና ተቀይረው ተመልክቻለሁ :: ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ስለዚህ ይህ እውነት የገባን ክርስቲያኖች ሁሉ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ፣ ክርስቶስ ለራሱ ሊያደርጋት ለሚፈልጋት ቤተክርስቲያን ሳይቀር በትጋት እንጸልይ በማለት መልዕክቴን በዚሁ እደመድማለሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry የተሃድሶ አገልጋይ

ያበሳጨን ፣ ጠበኛም ያደረገን ፣ ሕይወታችንንም ያታገለና ያስለቀሰን ወንጌል ሌባ ሆኖ የሚሰርቀን ሳይሆን ሕይወት ...ያበሳጨን ፣ ጠበኛም ያደረገን ፣ አልፎም በሕይወታችን ያታገለንና ያስለቀሰን ወንጌል ፣ ሌባ ሆኖ የሚሰርቀን ሳይሆን ሕይወት ሆኖ ሊያድነን የመጣ ነው ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ። መዝሙረ ዳዊት 119 : 71 ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። ትንቢተ ሆሴዕ 12 : 5 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኦርቶዶክሳውያን እናቶችና አባቶች እንዲሁም ይህን ትምህርት የተከታተላችሁ ወገኖች በሙሉ እንደምን ሰንብታችኋል ከተወደደው የእግዚአብሔር አገልጋይ ቢንያም ወርቅነህ ጋር የለቀቅነው የዛሬው መልዕክት በጣም ወሳኝና አስፈላጊ የሆነ የጊዘው መልዕክት ነውና ደግማችሁ በማዳመጥ እንድትጠቀሙ እንድትባረኩበትም ለማስተላለፍ እወዳለሁ:: በነገው ዕለት ቅዳሜም የምንነጋገርበት ትምህርት በተለመደው ሰዓት ይቀጥላል ::ስለዚህ ለማናችሁም መቅረት አይፈቀድም :: የዛሬው መልዕክት ግን በመረጥኩት የትምህርት አርዕስትና አስረጂ ጥቅሶች መሠረት የቀጠለ ነው :: ይሁን እንጂ ታድያ ይህንንም እንድል የሆንኩበት ዋነኛ ጉዳይ ከብዙዎቻችን ሕይወት ውስጥ ከሚወጣው ብስጩነት ፣ ንዴት ፣ ቁጣ ፣ መሳደብ አልፎም ሄዶ ከውስጣችን ፈንቅሎ ከወጣው ልቅሶና ምሬት የተነሳ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ስለገባን ውጤቱ ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ ምን ሊሆን እንደሚችል ከመረዳትና ከመገንዘብ አንጻር ነው :: ለዚህም ሁኔታ አንድ ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልገኝ አባት ማለትም ጳጳስ ናቸው በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ መሠረት ተቆርቁረው ሲያለቅሱ ሰማናቸው :: እኔም የማከብራቸውና የምወዳቸው ቀደምት አባታችን እንደመሆናቸው መጠን ፣ ልቅሶአቸው ከንክኖኝ ብፁዕ አባታችንን ምን ሆድ የሚያስብስ ነገር ቢገጥማቸው ነው እንዲህ ተንሰቅስቀው ማልቀሳቸው ? ብዬ በጉዳዩ በማዘን የተለቀቀውን የቪዲዮ መልዕክት ፍጻሜ ለማየት ስሞክር ለካስ የብጹዕ አባታችን ትልቁ ስጋታቸውና ልቅሶአቸው እንደገናም ፣ በልቅሶአቸውም ለሕዝባቸው ሊነግሩትና ሊያስተላልፉት የፈለጉት መልዕክት ፣ እንዳትሠረቁ ፣ ራሳችሁንም እንዳታሰርቁ ተጠንቀቁ የሚል ነው :: እንደ ብፁዕ አባታችን አመለካከት ይሰርቀናል ሲሉ የሰጉበትና ያለቀሱበት ትልቁ ወሬ ፣ በኢየሱስ ምክንያት የመጣ የኢየሱስ ወሬ ነው :: ታድያ ይሄ ትልቁ በኢየሱስ የተገኘ የኢየሱስ ወሬ የብዙዎችን ሕይወት የሠረቀ ነው ብለን ባናስብም ኢየሱስ ሕይወት ሊሆነን ሊበዛልንም የመጣ ጌታ በመሆኑ የብዙ ሰዎችን ሕይወት የለወጠ ነው :: በመሆኑም ታድያ ብዙዎቹ ብፁዕ አባታችን እንዳሉት ፣ በኢየሱስ ተሠርቀው ሳይሆን ተለውጠው ወደ ኢየሱስ የመጡ ናቸው :: ኢየሱስ እንደዚያ እንደ ክፉው ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የመጣ ጌታ ሳይሆን ሕይወት ሊሆንልንና ሊበዛልን የመጣ ጌታ ነው የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 10 :: ኢየሱስ እውነተኛ የበጎች በር ፣ በበሩም የሚገባ ጌታና መልካምም እረኛ ስለሆነ መስረቅ ወይንም ስርቆት የሚባል ነገር በእርሱ ዘንድ አይታሰብም :: ለዚህ ጌታ አንድ እውነት እንደ ቃሉ የምንናገርለት ነገር ቢኖር ፣ ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምጼንም ይሰማሉ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ በማለቱ ፣ ከዚህ ወርቃማ እና አምላካዊ ቃል የተነሳ ስርቆት ብለን ብናስብ ኃጢአት ይሆንብናል :: ነገር ግን አንድና አንድ እውነት ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ያለው ኢየሱስ ነውና እርሱ ሁሉን የሚችል ጌታ በመሆኑ ማምጣቱ አይቀርም የዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 16 :: ስለዚህ ከዚህ መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት አንጻር ብጹዕ አባታችን በመሪር እንባቸው ፣ ኢየሱስን ይሰርቀናል ሲሉ ሳይሆን ይለውጠናል ሲሉ የሰጉ አስመስሏቸዋል :: ይህ ብቻ አይደለም ይሄ ጀግና ኢየሱስ መለወጥ ከጀመረ ማንንም የማይምር በመሆኑ ፣ በኢየሱስ ምክንያት እንደ ሰደድ እሳት የተቀጣጠለው የወንጌሉ እውነት በመለወጥ ጉዳይ ከያዘ በቀላሉ የማይለቅ በመሆኑ ፣ ጳጳሱ ብፁዕ አባታችን ጨንቋቸው እንዳትሠረቁ ራሳችሁንም እንዳታሰርቁ ሲሉ ሕዝቡን በእንባ ተማጸኑ :: ታድያ ይህንን የብፁዕነታቸውን ጽኑ ልቅሶ አይቼ ወዲያው እኔም ለእኚህ አባት ካዘንኩበት ሰመመኔ ፈጥኜ ነቃሁና አንድ ነገር አሰብኩ :: ያዘንኩላቸው ስለማውቃቸው ፣ አረጋዊ አባትና ብፁዕ አባታችንም ስለሆኑ በመንፈሴ ሳይሆን በሥጋዬ ነው ብዬ አስተዋልኩ :: አስከትዬም የለውጥ ያለህና በአባቶቻችን አፈርን ሲሉ በመጽሐፎቻቸው ወደ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ፣ እንዲሁም ወደ ሕዝባቸውም ጭምር የጮሁትን ጠንካራ የመጽሐፉ አዘጋጆችና የለውጥ አራማጆች የሆኑ የተሃድሶ አገልጋዮችን ጽሑፍ ሳስታውስ ፣ የብጹዕ አባታችን ልቅሶ ፣ ሹሉዳው እንደተነካ እንደ ያዕቆብ ለመለወጥ የሆነ ልቅሶ እንደ ሆነ ገባኝ እና እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመርኩኝ :: ታድያ ይህ ልቅሶ ያዕቆብ ጋ የቀረ ብቻ ሳይሆን ፣ ተንከባሎ መጥቶ ብፁዕነታቸው ጋር የደረሰ ፣ በዚህም ሳያቆም ብዙዎች ቤት ውስጥ ሳይቀር ሳይታሰብ በድንገት የገባ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ጌታን ለማመስገን ነፍስም አልቀረልኝ :: ለምን ብትሉ በአባቶቻችን አፈርን ፣ የለውጥ ያለህንና ሌላም ሌላም ሲሉ የጻፉ ሰዎች በመጽሐፎቻቸው የጮሁትን ጩኸት እግዚአብሔር ስለሰማ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለውጥን ፈልጋው ሳይሆን ሳትፈልገውም ቢሆን የግድ ጉያዋና መቅደስዋ ፣ ካቴድራሎችዋና መንበረ ጵጵስናዎችዋ ድረስ ሳይቀር እየገባ ፣ ከክብር ወደ ክብርም እየለወጣት ይገኛል :: ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁንለት :: ከዚህም ሌላ ይህንን ለውጥ እያደረገ ያለው እግዚአብሔር ስለሆነ ፣ ይህን እግዚአብሔርን ማንም አያቆመውም :: ይህ የለውጥ ውሽንፍር ደግሞ ወንጌላውያን አማኞች ቤተክርስቲያን ድረስ በመግባት ፣ በለውጥ ያልተቃኙ አማኞችንና አንዳንድ ሥጋውያን ፓስተሮችን ሳይቀር መለወጡ አይቀርም ብዬ አምናለሁ :: ለውጥ ደግሞ ለውጥ ነውና ፣ አንድ ጊዜ በምድሪቱ ላይ ይምጣ እንጂ ሰዎችን አይመርጥም ፣ በዚህ ጉዳይ ፣ እኔም በዘመኔ ለእግዚአብሔር እውነት ያልተገኙና በመንፈስቅዱስ ያልተሞሉ ፣ የመንፈስቅዱስም ተቃራኒዎች የሆኑ ትልልቅ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ፣ ጊዜያቸው መጥቶ መንፈስቅዱስ ሲያንደባልላቸው ፣ በመንፈስቅዱስም ሲሞሉ በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ :: ይህ ብቻ አይደለም ከዚሁ ከመንፈስቅዱስ ሙላት የተነሳም በብዙ አገልጋዮች ሕይወት ተለጥፎ ያለ አቡዋራና ጥቀርሻ እንዲሁም ያልተገራ ባሕርዮቻቸው ጭምር በዚሁ በመጣው በመንፈስቅዱስ ሙላት ከውስጣቸው ተራግፎላቸውና ተቀይረው ተመልክቻለሁ :: ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ስለዚህ ይህ እውነት የገባን ክርስቲያኖች ሁሉ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ፣ ክርስቶስ ለራሱ ሊያደርጋት ለራሱ ሊያደርጋት ለሚፈልጋት ቤተክርስቲያን ሳይቀር በትጋት እንጸልይ በማለት መልዕክቴን በዚሁ እደመድማለሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry የተሃድሶ አገልጋይ