Thursday 29 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስምንትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስምንት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ናችሁ በክፍል ስምንት ትምህርታችን የምንመለከተው የመምህራንና የሊቃውንትን አሳሳልና የሥዕሉን ትርጉም ነው ሃሳቡን እንዲህ በማለት ያስቀምጡታል መምህራንና ሊቃውንት ካባ ለብሰው ወንጌል ይዘው ይሣላሉ ይህም ክብራቸውን ለማሳየት ነው በዚህ ዓለም ዞረው ወንጌል ለማስተማራቸው ፣ መናፍቃንን ተከራክረው ስለመርታታቸው እውነተኛዋን እምነት ስለማስተማራቸው ነው ይላሉ በመሠረቱ ለሥዕል መስገድ እንደሌለና የተቀረጸ ምስልንም ማምለክ እንደማይገባን መጽሐፍቅዱሳችንን መሠረት አድርገን በተደጋጋሚ መነጋገራችን ይታወሳል ዘጸአት 20 ፥ 3 _ 6 ፤ ዘዳግም 4 ፥ 15 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 24 ን እንመልከት ይሁን እንጂ ከዚህ ከማብራርያው ሃሳብ በመነሳት ሰዎች በሞያቸው ምክንያት ካባ ፣ ቀሚስ ፈርጅያ ፣ ጃኖ ፣ ጥንግ ድርብ በወንጌላውያንም አብያተክርስቲያናት ደረጃ ሱፍ ክራቫትና የመሳሰሉትን ቢያደርጉ የለበሱት የማዕረግ ልብስ ከወዴት እንደሆኑ የሚያሳይ ባሕላዊ አለባበስንም የሚጠቁም በመሆኑ ያን ያህል ችግር የሚያመጣ ነው ብዬ አላስብም ሰዎችም ከአንድ የትምህርት ተቋም ተምረው ሲጨርሱ የመመረቅያ ገዋን ይለብሳሉ ይህ ለሰዎቹ የሞያቸውን ምንነትና ማንነት የሚያሳይ በመሆኑ የሚያስመሰግንና እጅግም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው ነገር ግን ልብሱ እንዲህ ሊሆን ሲገባው ትርጉሙን ቀይሮና በምትኩ ሌላ ትርጉም ይዞ ሲመጣ ግን እጅግ ይከብዳል ይህንንም በትረካው እንደተመለከትነው መምህራንና ሊቃውንት ካባ ለብሰው ወንጌል ይዘው ይሳላሉ ይህም ክብራቸውን ለማሳየት ነው የሚለው አባባል ፍጹም ከወንጌል እውነት የወጣና ስሕተት የሆነ ነገር ነው ካባ ፣ ቀሚስ ፣ ፈርጅያ ፣ ጃኖም ሆነ ሱቶችንና ክራቫቶችን ለክብራችን የምንለብስ ከሆነ የጌታ አገልጋዮችና ወንጌል ሰባኪዎች መሆናችን ቀርቶ በሉቃስ ወንጌል 20 ፥ 45 _ 47 በተጻፈው ቃል መሠረት ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ በገበያም ሰላምታ በምኩራብም የከበሬታ ወንበር በምሳም የከበሬታ ሥፍራ ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ ይለናልና እኛም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እየሆንን ስለሆነ በዚህ በእኛም ዘመን ሰዎች ከእኛም ሊጠበቁ ይገባል እያልናቸው መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ የኖሩት ኑሮ ምን እንደሚመስል ለእኛ ምሳሌ እንዲሆነንና እኛም እንድንማርበት ትምህርቱ በሰፊው ይተነትናል አያይዞም ተከራክሮ መርታትን አስመልክቶ ኦርቶዶክሳውያኑ ሊቃውንት ከአዋቂነታቸው ጋር አያይዘው ስለሆነ የሚተረጎሙት መጽሐፍቅዱሳችን እውቀትን የማይጠላና የሚያበረታታ ፣ ካህን መሆን የሚፈልግ ሰውም እውቀት ሊኖረው እንደሚገባ ቢያስተምረንም ትንቢተ ሆሴዕ 4 ፥ 6 እኔ አዋቂ ነኝ ፣ ከኔ ወዲያ ለአሳር የሚለውንና ተከራክሬም ረታለሁ ፣ አሸንፋለሁ ፣ ማን ይችለኛል ? ሲሉ ለራስ የከፍታ ሥፍራንና የሊቅነትን ቦታ ሰጥቶ ሌላውን መናፍቅ ፣ አላዊና ከሐዲ ነህ ሲሉ በድፍኑ ማንጓጠጥን ፣ ማቃለልን ግን እጅግ ጸያፍ ፣ በልግና የኃጢአትም ሥራ መሆኑን እያስገነዘበን እንደገናም የሌላውን ሳይሆን የራስን አላዋቂነትና ኋላቀርነትንም ጭምር የሚያሳይ ሽፍን አስተሳሰብ መሆኑንም ትምህርቱ ሰፊ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃና ማብራርያር በመስጠት ከዚህ ዓይነቱ ደካማና የተናቀ አስተሳሰብም ሆነ አመለካከት እንድንወጣ ግልጽ አድርጎ በመናገር በጉልህ ያስተምረናል ይመክረናል ለበለጠ ግንዛቤ ቪዲዮውን ተመልከቱ ጌታም በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday 27 June 2017

የማይሸረሸር ዓለቴ የማይናናጋው መሠረቴ የዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረ ጻድቅ ሰምታችሁ ተባረኩበትየተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ስለ ሥዕል በመማማር ላይ እንገኛለን ጌታ እግዚአብሔር ይህቺን የኦርቶዶክስ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ወደ ተመሠረተችበት የወንጌል እውነት ለመመለስ ጌታ በብዙ እየሰራ ያለበት ጊዜ በመሆኑ አምላኬን ከፍ ባለ ምስጋና ልባርከው እወዳለሁ ከዚህ በመቀጠል ግን የዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረ ጻድቅን የማይሸረሸር ዓለቴ የማይናናጋው መሠረቴ የሚለውን መዝሙር ልጋብዛችሁ እወዳለሁ ስለ ሥዕል ፣ ስለታቦትም ሆነ በሌሎች አርዕስቶች ላይ ስላሉ ሃሳቦች ብንማማርም ሕዝባችንን ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ወደ ዘመረለት የማይሸረሸር ዓለት አምጥተን ለመመስረት በመሆኑ ይህን መዝሙር ስዘምረው ብውል የማልጠግበው ነውና ወደ እናንተም ይድረስ ብያለሁ ተባረኩ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ሰባትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ሰባት በክፍል ሰባት ትምህርታችንም ድንግል ማርያምን መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ይሏታልና ወደ አማርኛው ስተረጉመው ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሚለውን ሃሳብ የሚይዝልን በመሆኑ ከዚህ በመነሳት ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሰዓላ በዕዱ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ ወደ አማርኛው ስተረጉመው ከወንጌላውያን አንዱ ሉቃስ በእጁ ለሳላት ለማርያም ሥዕል ምስጋና ይገባል የሚል ሃሳብ ይዘው ብዙዎች የኦርቶዶክሳውያን አማኞች በማርያም ሥዕለ አድኅኖ ፊት ይጸልያሉ ፣ ይሰግዳሉ ፣ አምልኮተ እግዚአብሔርም ያደርጋሉ ታድያ ይህ ትክክለኛ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ እውነትነት ያለው ነው ወይ ? ወንጌላዊ ሉቃስስ በእርግጠኝነት የማርያምን ሥዕል ስሏል ወይ ? ስንል ለዚህ ያገኘነው መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃ ባለመኖሩ ወንጌላዊ ሉቃስ የማርያምን ሥዕል ስሏል ለማለት አንችልም ድንግል ማርያምም መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ሲተረጎም ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሚል ነውና በመጽሐፍቅዱሳችን ውስጥም ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ናት የሚል ቃል ተጽፎ አላገኘንም ይልቁንም የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ነው የሚለን የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 27 ስለዚህ ከዚህ ከመጽሐፍቅዱሱ እውነት የተነሳ ማርያም ሰው የሆነች ድንግል መሆንዋን ነው ከቃሉ የምንረዳው ነገር ግን መጽሐፍቅዱሳችን ትክክለኛውን እውነት ነግሮን ሳለ ድንግል ማርያምም ሰው መሆንዋ ተረስቶ ተአምረ ማርያም በሚለው መጽሐፍ ላይ ለሥዕሏ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ ፣ ማርያም ማለት መንግስተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው የሚሉት እና የመሣሠሉት ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ከዚህም ሌላ አሁንም ለድንግል ማርያም መልክአ ሥዕል ተደርሶላት በአምላክነት ወይም በመለኮት ኃይል ልክ እንድትመለክ የሚያደርግ ድርሰትና ምስጋና እስካሁን ድረስ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እየተዘመረ ፣ እየተመሰገነ ፣ እየተጸለየ ይገኛል ይህ ግን መጽሐፍቅዱሳዊ አለመሆኑን ከተአምረ ማርያም መጽሐፍ ጀምሮ ባለው ሃሳብ ተነስቼ እያንዳንዱን የተደረሰ መልክ በመዘርዘርና በመተንተን እንደ እግዚአብሔር ቃል ትክክል አለመሆኑን ገልጬ በዚህ የቪዲዮ ትምህርት አቅርቤዋለሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንግዲህ ትምህርቱ እንዳያመልጣችሁ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ በብዙ ትባረኩበታላችሁ እንደገናም ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ በክፍል ስምንት እስከምንገናኝ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ በማለት የምሰናበታሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 22 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስድስትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስድስት የክፍል ስድስት ትምህርት ከክፍል አምስት ትምህርት ጋር በተያያዥነት የቀረበ ነው የቅድስት ሥላሴን ሥዕል በተመለከተ በቀረበው ሥዕላዊ ማብራርያ መሠረት ሥላሴ እንዲህ ስለሆኑ አምልኮ ይገባቸዋል ስንል ሥዕልን ስለንና ሥዕላዊ ማብራርያ ሰጥተን ማምለክ አንችልም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ነገር ጥልቅና ሊመረመር የማይቻል ሲሆን የእግዚአብሔር ምስጢር ግን ክርስቶስ ስለሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ በእርሱ ነውና በማለት የእግዚአብሔር የሦስትነትና የአንድነት ምስጢር እንዴት እንደተገለጠ ትምህርቱ በሰፊው ያብራራልናል አያይዞም የድንግል ማርያምን የአለባበስ ሁኔታ በሰፊው ከዘረዘረ በኋላ የልብስዋ ቀለም አቀባብም ከላይ ሰማያዊ ከውስጥ ደግሞ ቀይ ሆኖ ይሣላል ቀይ ከውስጥ መሆኑ እሳተ መለኮትን በማኅጸንዋ መሸከምዋን ለማስረዳት ነው ሰማያዊት ናትና ከላይ ያለው ሰማያዊ ቀለም ይደረጋል አንድም ከላይ ሰማያዊ ከውስጥ ቀይ መሆኑ ክብሯ ሰማያዊ ያውም መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፈጣሪ በታች እንደሆነች ተደርጎ ይነገራል የሚል ትረካ ሰምተናል ይሁን እንጂ ሥዕሉም ሆነ የሥዕሉ የታሪክ ገጽታ ትክክል ያልሆነና ኢመጽሐፍቅዱሳዊም በመሆኑ ፍጹም አንቀበለውም ለበለጠ መረጃ ቀይና ሰማያዊ የለበሰችበትን ሥዕሏን ከዚህ ትምህርት መልስ እለቀዋለሁና ተከታተሉ መጽሐፍቅዱሳችንን ስናጠና ድንግል ማርያም ኢየሱስን የወለደችው በሥጋ ነው ለምን ስንል ኢየሱስ በሥጋ የተወለደ መሆኑን ለማመልከት የእግዚአብሔር ቃል በዕብራውያን 2 ፥ 16 ላይ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላዕክትን አይደለም ይለናል የቤተክርስቲያን መጽሐፍም ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርዓ ብዕሲ ወአድሃነነ አለን ወደ አማርኛው ስተረጉመው ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ ተወልዶም አዳነን " በሥጋ አለ በመለኮት አትወልደውምና " አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትስብዕቱ እንዲል ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ትርጓሜ ) ከዚህ የተነሳ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በሥጋ የወለደችው በመሆኑ ወላዲተ ኢየሱስ ትባላለች እንጂ ወላዲተ አምላክ ብለን እንድንጠራት መጽሐፍ አያስተምረንም እንደገናም ወላዲተ አምላክ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ አለማመን ስለሆነ ትልቅ ስሕተትና የኑፋቄ ትምህርት ነው 1ኛ ዮሐንስ 4 ፥ 1 _ 6 ፤ ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 የኃጢአት ሥርየት ያገኘነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ስለተወለደ ነው እንደገናም ወንድሞቼ ሊለን ያላፈረብንና በነገር ሁሉ እንደኛ የተፈተነ ፣ የሚፈተኑትንም የሚረዳ ፣ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህን የሆነው ፣ ኃጢአትን ስለመተውም በእግዚአብሔር ችሎት ፊት ጽድቁን ያሳይ ዘንድ የኃጢአት ማስተሥረያ ሆኖ የቆመልን ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፣ በሥጋ የመጣ ፍጹም ሰውም ስለሆነ ነው ዕብራውያን 2 ፥ 13 _ 18 ፤ ሮሜ 3 ፥ 21 _ 26 ከዚህም ሌላ ኢየሱስ የሰው ልጅ በመሆኑ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ ለአይሁድ በውል ሳይገባቸው ኢየሱስን እንደጎሰሙትና ፊቱንም ሸፍነው ኢየሱስ ሆይ ማነው የመታህ ? ትንቢት ተናገር ያሉት ፣ ኢየሱስ በሥጋ የመጣበትን ምስጢር በውል ስላልተረዱና ስላልተገነዘቡ እንደሆነ ሁሉ ለእኛም ለኦርቶዶክሳውያን አማኞች ያለው ነገር ይኸው ነው ታድያ ኢየሱስ የሰው ልጅ ሆኖና በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ የማይቀር ፣ ተመልሶም በደመና በብዙ ክብር እንደሚመጣ እየነገረን ኢየሱስ በአብ ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ፈራጅ ነው እንጂ የሚያማልድ አይደለም ማለታችን ኢየሱስን በሥጋ እንደመጣ አለማመንንን የሚያሳይ ነውና መረዳታችንን በእግዚአብሔር ቃል እውቀት ከፍ ልናደርግ ልናስተካክልም ይገባል እላለሁኝ ማቴዎስ 26 ፥ 63 _ 68 ፤ ሉቃስ 22 ፥ 66 _ 71 ሌላው ድንግል ማርያምን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ማለት ሰው የሆነችበትን እውነት መካድ ስለሚሆንብን ፍጹም ስሕተት ነው ለምን ስንል መጽሐፍቅዱሳችን ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ይለናል የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 26 _ 38 የተወደዳችሁ ወገኖች የትምህርቱ ሃሳብ እንግዲህ በአጭሩ ይህንን ይመስል ነበረ ቪዲዮውን ተከታተሉ ሰምታችሁም ለሌሎች ሼር አድርጉ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ተባረኩ የክፍል ሰባት ትምህርት ይቀጥላል ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Monday 19 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል አምስትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል አምስት ሥዕልን መሳል መልካም የሆነና በዚህ ጉዳይ ላይም የሰዓልያንን ሞያ ከፍ በማድረግ የምናደንቅላቸውና ሳናመሰግንም የማናልፈው ጉዳይ ቢሆንም ሥዕልን ስለን እንድናመልክና ልናመልክ ለወደድነው ሥዕልም ትርጉም እንድንሰጥ ግን መጽሐፍቅዱስ አይነግረንም ፣ አያስተምረንም ዘጸአት 20 ፥ 3 _ 6 ፤ ዘዳግም 4 ፥ 15 _ 24 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 16 _ 26 ከታሪክ እንደምንረዳው የቅዱሳን ሥዕላት አሳሳል በሁለት መልኩ ተከፍሎ ሊታይ ይችላል የቢዛንታይን የአሳሳል ትውፊትና የላቲን ወይም የሮማ ትውፊት አለ የኢትዮጵያውያን የቅዱሳን ሥዕላት አሳሳል ትውፊትም ከእነዚህ የአሳሳል ትውፊቶች የመጣ ሆኖ የራሱ የሆነ ልዩ የሚያደርገው መለያ ባሕርያት አሉት የኢትዮጵያ የአሳሳል ጥበብ ከሌላው የሚለይባቸው ነገሮችም የቀለሙ አቀባብ ፣ የሚሳሉበት ቦታ ፣ ለሥዕሉ የሚሰጠው ክብር ፣ ሥዕላቱን በጥንቃቄ ቦታ የማስቀመጥ ሁኔታና የመሳሰሉት ነገሮች ልዩ ያደርገዋል የኢትዮጵያውያን የሥዕል አሳሳል ዘዴና ትውፊት ከሌላው ዓለም አሳሳል ሁሉ ልዩ ባሕርያትን የተላበሰ ነው ተብሎ ይነገርለታል በኢትዮጵያ የአሣሣል ዘዴ ሥዕላቱ የሚሳልበት ጥበብ ከሌሎች ሀገራት የአሣሣል ትውፊት ይለያል ይኸውም 1ኛ ) በኢትዮጵያ አሳሳል ጥበብ የቅዱሳኑም ሆነ የመላዕክቱ የፊት ቅርጻቸው ጎልቶ ይሳላል ይባላል ይህም የሚሆንበት ምክንያት የጐላች የተረዳች ሃይማኖት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ባለቤቶች መሆናቸውን ለማጠየቅ ነው ይለናል ታሪኩ ታድያ ከዚህ በመነሳት መጽሐፍቅዱሳችን ጎላ ብሎ ሊታይም ሆነ በቀለምም ሆነ በብራናና በሰሌዳ ሳይሆን በሰው ልብ ውስጥ በጉልህ ሊሳል የሚገባው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራርያ በመስጠት ያስረዳናል በመሆኑም ይህንን እውነት በሰፊው በትምህርቱ ዳሰነዋልና ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ 2ኛ ) በሥዕላቱ ላይ ተስለው ያሉ ቅዱሳን ዓይናቸውም ጐላ ተደርጎ ይሣላል ዓይናቸው የሚመጣውን ያለፈውንም ዓለም በትንቢት መነጽርነት ይመለከታሉና የጐላ ዓይን ሁሉን የሚመለከት ንጹሕ ዓይን እንዳላቸው ለማሳየት ዓይናቸው ጎልቶ ይሳላል ይለናል ይሁን እንጂ መጽሐፍቅዱሳችንን በዚህ ጉዳይ ላይ ስንመለከት የክርስትና ምስጢር ያለው የተፈጥሮ ዓይን ጐላ ብሎ በመታየት ዙርያ እንዳልሆነ አበክሮ ያስተምረናል የክርስትና ምስጢር የውስጥ ዓይን የመከፈት ጉዳይ ነው ታድያ በዚህ ጉዳይ ዳዊት ዓይኖቼን ክፈት ከሕግህም ተአምራትን አያለሁኝ አለ መዝሙር 119 ፥ 18 ዳዊት ይህንን ሲጸልይ ዓይን አጥቶና ዓይኖቼን ክፈት ሲል የጸለየው አይደለም ቀይ ብላቴና መልኩም ያማረ እንደነበረ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 22 ሐዋርያው ጳውሎስም በዚህ ጉዳይ ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው እያለ በክርስቶስ ያገኘነውን ከፍታ ፣ ክርስቶስ ኢየሱስም ለቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን የተሰጠና ቤተክርስቲያንም አካሉ ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ መሆንዋን ይጠቁመናል ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 23 ስለ ዓይን መከፈት ከዚህም ሌላ ብዙ የተማማርንባቸው ሃሳቦች ስላሉ ቪዲዮውን መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው የክፍል ስድስት የዚሁ ተከታይ ሃሳብ ይቀጥላል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 15 June 2017

ሥዕል በቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረ ክፍል አራት ሥዕል በቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረ ክፍል አራት የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል አራት ትምህርታችን ሥዕል በቤተክርስቲያን የተጀመረበትን ጊዜ ትምህርቱ በሰፊው ከተረከልንና ካብራራው በኋላ ከመከራው ጽናት የተነሳ በዚያን ዘመን የነበረው ክርስቲያን በዋሻ ወይም በግበበ ምድር ውስጥ ጌታን ያመልክ ስለነበር የክርስትናን ትምህርት አስፋፍቶ ለመስጠት በቂ መጻሕፍት አልነበሩም ፣ እንደ ልብ ወጥቶ ለመፈለግና ለማዘጋጀትም ነጻነት ስላልነበረቸው በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ከመጽሐፍቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ምሳሌዎችን በሥዕል እያሰፈሩ ማስተማር ጀመሩ ብለናል አያይዘንም በዚህ ሁኔታ ሥዕል ማስተማርያ ሆኖ የቆየ መሆኑንም ተናግረናል ሥዕሎችም የሚሳሉት በምሳሌነት Symbol ( ሲምቦል )ሲሆን የሚሳሉትም በአመድና በከሰል በዋሻ ዙርያ እንደሆነ ታሪክ ይናገራል ወደ ዋናው ሃሳብ ስመጣ ሥዕሎች መጽሐፍቅዱሱን ተመስርተው በዋሻ ውስጥ በመሳል ትምህርት ሲሰጥባቸው የቆዩ ቢሆንም እስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመርያ ድረስ ሥዕል በቤተክርስቲያን እንደተጠበቀ ቆይቶ በዚሁ በሥዕል ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛት በሚኖሩ ምዕመናን መካከል አለመግባባት ተፈጠረ በዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ አንዳንድ ክርስቲያኖች ሥዕልን ከመውደዳቸው የተነሳ ሥዕሎችን አማልክት ናቸው እስከ ማለት መድረሳቸውን ትምህርቱ የሚጠቁመን የትምህርቱ ሃሳብ በይበልጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ያጠነጠነ ነው ትምህርቱን ደረጃ በደረጃ ለማየት ቢያስፈልግ ፦ 1ኛ ) ከእግዚአብሔር በላይ የምንወደው ነገር ሊኖር አይገባም የሚል ማብራርያ የያዘ ነው የሉቃስ ወንጌል 10 : 27 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 10 ; 37 ፣ የማርቆስ ወንጌል 12 : 30 ፣ 33 2ኛ ) ኢያሱ እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተ ግን የምታመልኩትን ምረጡ ያለ ነበር ኢያሱ 24 ፥ 15 3ኛ ) ኤልያስም ደግሞ እስከመቼ በሁለት ሃሳብ ታነክሳላችሁ ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ በአል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ አለ ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 20 _ 22 4ኛ ) ከእግዚአብሔር ጋር የምንጣበቀው በ2ኛ ነገሥት 18 ፥ 1 _ 8 በተጻፈው ቃል መሠረት እንደ ሕዝቅያስ በኮረብታ ያሉትን መስገጃዎች አስወግደን ፣ ሐውልቶችንም ቀለጣጥመን ፣ የማምለክያ አጸዶችንም ቆራርጠን ብቻ አይደለም የእስራኤልም ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ እንደ ሰራው ዓይነት የናስ እባብ የመሰለን ነገር ሰባብረን ፣ ስሙንም ነሑሽታን ብለን ነው ከእግዚአብሔር ጋር የምንጣበቀው በማለት ይህንን ሃሳብ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 19 ፥ 19 ከተጻፈው ቃል ጋር በማያያዝ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር በማለት የጌታ ቃል ያሸነፋቸው ሰዎች የወሰዱትን እርምጃና ከእግዚአብሔር ጋር በሐዲስ ኪዳን ሳይቀር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የተጣበቁበትን እውነተኛ የሕይወት ትስስርና ዘላለማዊ የሆነን መጣበቅ ተመልክተናል ቪዲዮውን ደጋግማችሁ ስሙት ትባረኩበታላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የክፍል አምስት ትምህርት ይቀጥላል ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday 13 June 2017

የሥዕልን ትርጉም ፣ ሥዕሎች Symbolic ( ሲምቦሊክ ) በመሆናቸው መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘታቸውንና ዘይቤያቸውን የምና...የሥዕልን ትርጉም ፣ ሥዕሎች Symbolic ( ሲምቦሊክ ) በመሆናቸው መጽሐፍቅዱሳዊ ይዘታቸውንና ዘይቤያቸውን የምናይበት የክፍል ሦስት ትምህርት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ከርማችኋል ዛሬ በቪዲዮ በለቀኩት ትምህርትና በርዕሱ መሠረት በግዕዙ ዲክሺነሪ ሥዕል ማለት በቁሙ መልክ ፣ የመልክ ጥላ ፣ አምሳል ፣ ንድፍ ፣ በውሃ በመጽሔት ፣ በጥልፍ ፣ በሥፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር ፣ ከዕብን ፣ ከዕፅ ፣ ከማዕድን ታንጾ ፣ ተቀርጾ ፣ ተሸልሞ አጊጦ የሚዳሰስ መሆኑን አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ መዝገበ ቃላት ባዘጋጁት መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል ሥዕለ ኪሩብ ፣ ሥዕለ ጣኦት ፣ ሥዕላት ወምስላት ፣ አስተረየ በአየረ ሰማይ ሥዕለ መስተጽዕና በአፍራስ እሳት ወደ አማርኛ ስተረጉመው በሰማይ አየር ላይ በእሳት ፈረስ የተጫነ ሥዕል ታየ ማለትን የሚያመለክት ነው በመሆኑም Figurative language በመስጠት እንግዲህ ኤልሳዕም አይቶ አባቴ አባቴ ሆይ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች ብሎ ጮኸ በማለት ይህንን ቃል ነው ጸሐፊው ሊጠቅስልን የፈለገው 2ኛ ነገሥት 2 ፥ 10 _ 12 እነዚህ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች የእስራኤል ደኅንነት ናቸው እስራኤል በደኅንነት ተጠብቀው የሚኖሩት ከእነዚህ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች የተነሳ ነው በዚህም ምክንያት የግያዝ መንፈሳዊ ዓይን የተያዘ በመሆኑ በሥጋዊ ዓይኑ የሶርያ ፈረሶችና ሰረገሎችን አይቶ በጮኸ ጊዜ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥለት ብሎ ጸለየ እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ ይለናል 2ኛ ነገሥት 6 ፥ 1 _ 23 ስለዚህ በምድር ላይ ዛሬም Symbolic ( ሲምቦሊክ ) ሆነው የቀረቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች አሉ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ናቸው ባንላቸውም ሲምቦሊክ ሆነው በመሰራታቸው ሰዎች በእነዚህ ፈረሶችና ሰረገሎች ዛሬም ይጓዛሉ የመጽሐፍቅዱስ ቋንቋ ሃብታምና ዘይቤያዊ አነጋገር ያለው በመሆኑ የመጽሐፍቅዱስ ጸሐፊዎች ማንኛውንም መንፈሳዊ እውነቶችን Symbolized ( ሲምቦላይዝድ ) ሲያደርጉ ቤተሰባዊ ሆነው ነው Symbols ( ሲምቦልስ ) ብዙ ጊዜ ውብና አስደሳች የሆነ Figurative Language አላቸው ይህንን ሃሳብ ለማጠናከር መክብብ 2 ፥ 2 ፣ ኢሳይያስ 10 ፥ 18 _ 19 ፤ ኢሳይያስ 32 ፥ 19 ፤ ዘጸአት 19 ፥ 4 ኢሳይያስ ሁልጊዜ የሚጠቀመው ዛፎችንና ጫካዎችን እንዲሁም ደኖችን ለጥንካሬ ነው ነገር ግን እነዚህ ደኖችና ጫካዎች የሊባኖስም ዝግባ ጭምር እንደሚቆረጡና እንደሚገለጡ ዳዊት በመዝሙሩ ተናግሯል መዝሙር 28 ( 29 ) ፥ 3 _ 9 ጫካው ደኑ ዱሩና በሊባኖስ ዝግባ የተመሠለው ጠንካራው የሰው ልብ ነው ዘላለማዊና ኃይለኛ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ግን ይመነጠራል ይገለጣል ኢያሱንም ተራራማው ሀገር ለአንተ ይሆናል ዱር እንኳ ቢሆን ትመነጥረዋለህ ያለው ለዚህ ነው ኢያሱ 17 ፥ 17 እና 18 የንስር ክንፍንም በተመለከተ በፊደላዊ ትርጉሙ ስንመለከተው እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ ለማውጣት እውነተኛውን ንስር ሕዝቡን በዓየር ለመሸከም አልተጠቀመም ይህ ዓረፍተ ነገር በግልጽነት ሲምቦሊክ ነው እግዚአብሔር አጉልቶና አጋኖ በጣምም አሳስቦ ሊነግረን የወደደው እስራኤልን ነጻ በማውጣት ዙርያ ፍጥነትንና ጥንካሬን ለማሳየት ነው ኢየሱስም ሰዎችን ያስተማረው ሙሉ በሆነ ሲምቦሊዝም ነው ራሱንም ያቀረበው በእረኛ ፣ በሙሽራ ፣ በበር ፣ በማዕዘን ራስ ድንጋይ ፣ በወይን ፣ በብርሃን ፣ በእንጀራና በውሃ ነው ሲምቦል ሁልጊዜ ምልክቶች ብቻ አይደሉም ሲምቦል ትንንሽ ሥዕሎች በኮምፒውተር ውስጥ እንዳለ አይከን ቀለል ያሉ ማብራርያዎችን የሚሰጡን ናቸው ይህንን ሁሉ ያብራራሁበት ምክንያት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን የራስዋ የሆነ ፊደል ፣ ስነ ጽሑፍ ፣ ዜማ ፣ ኪነ ሕንጻና የመሣሠሉት እንዳሏት ሁሉ የራሱ የሆነ የስነ ሥዕል ጥበብም ያላት ስንዱ እመቤት እንደሆነች ለመጠቆም ነው ከዚህ የተነሳ በትውፊታዊ መልክ የተቀበለችውን ሥዕሎችዋን በአብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ ፣ በሸራ ፣ በብራና በወረቀትና በመስቀሎች ላይ በቀለም ወይም በጭረት ባለ ሁለት ጎን ሆነው የሚሰሩ የተደራሲውን ማንነት የሚገልጥ መንፈሳዊ ጥበቦች ናቸው ይሁን እንጂ በሥዕሉ ላይ የሚታዩትን መንፈሳዊ ጥበቦችን ብናደንቅም ስግደትንና አምልኮትን ግን በፍጹም አንሰጠውም በሥዕሉም ፊት በመጸለይና በመስገድ ከሥዕሉ ባለቤት መንፈሳዊ በረከቶችን እናገኛለን ብለን አናምንም ሥዕልን በትክክለኛው መንገድ እንደ መጽሐፍቅዱሱ ቃል ተስሎ ካገኘነው ለማስተማርያነት ልንጠቀምበት እንችላለን ከዚያ ያለፈ ትርጉም ግን አንሰጠውም በክፍል አራት ትምህርት እስክንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 8 June 2017

እግዚአብሔር ሙሴን ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ማለቱ ክፍል ሁለትእግዚአብሔር ሙሴን ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ማለቱ ክፍል ሁለት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የክፍል ሁለት ትምህርታችንን ጀምረናል ጌታ እግዚአብሔር ሦስት ታላላቅ መመርያዎችን ለሙሴ ነግሮት ነበር 1ኛ ) ከግራር እንጨት ታቦትን ይሥሩ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን …………………..ዘጸአት 25 ፥ 10 _ 17 2ኛ ) ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ በሥርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ ……………….. ዘጸአት 25 ፥ 18 እና 19 3ኛ ) በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ እኔ እንደማሳይህ ሁሉ እንደ ማደርያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ እንዲሁ ሥሩት አለ ዘጸአት 25 ፥ 8 እና 9 ተመልከቱ ውድ ወገኖቼ ሆይ ታድያ ጌታ እግዚአብሔር ለምን ይሆን ? ታቦት ሥሩልኝ ፤ ኪሩብ ሥሩልኝና መቅደስ ስሩልኝ ሲል መናገሩ ? እኛም እነዚህ ሦስት ዓበይት ሃሳቦች በቃሉ ላይ ስለተጻፉ ዛሬም ሆነ ከዚህ በኋላ በቀረው ዘመናችን ታቦትን ፤ ኪሩብንም ሆነ መቅደስን መስራት እንዳለብን ከእኛ ይጠበቃል ? ለዚህ መልሱ አንድና አንድ ነው እርሱም ጌታ እግዚአብሔር ታቦት ሥሩልኝ ፤ ኪሩብ ሥሩልኝና መቅደስ ስሩልኝ ሲል የተናገረውና መመርያንም የሰጠው ለእነ ሙሴ ነው እኛን አይደለም ስለዚህ ታቦትንም ሆነ መቅደስንና ኪሩብን እንድንሰራ ለእኛ የተፈቀደ ነገር አይደለም እኛም እንድንሰራ አልታዘዝንም ሌላው ደግሞ እግዚአብሔር ታቦትን ፤ መቅደስን ፤ ኪሩብን ሥሩልኝ ማለቱ እስከ ዛሬ ድረስም ሆነ ከዛሬ በኋላ ባለው ለወደፊቱም ይህንኑ ታቦት ፤ መቅደስና ኪሩብ እየሠራችሁ በነዚህ ነገሮች አምልኩኝ ፤ ስገዱልኝ ፤ አክብሩኝ ለማለት አይደለም እንደውም በዚህ ነገር ውስጥ ኖረው የሚያመልኩት ሰዎች አምልኮአቸው አስጸያፊና የጣኦት አምልኮ እንደሆነ ነው ቃሉ የሚነግረን ትንቢተ ሕዝቅኤል 8 ፥ 7 _ 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር መቅደስን ፤ ታቦትንና ኪሩብን ሥሩልኝ ሲል መናገሩ በዘጸአት 25 ፥ 21 እና 22 ፤ በዘኁልቁ 7 ፥ 89 መሠረት ታቦቱ ላይ ካለው ከሥርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል አምላካችን የሆነው እግዚአብሔር ድምጹን ለማሰማት ነው በአጠቃላይ ለግንኙነትና ለኅብረት ነው ስለዚህ እነዚህ ሦሰት ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ታቦቱ ኪሩቡና መቅደሱ የተፈለጉት ለእግዚአብሔር የግንኙነቱ መስመር መንገድ እንዲሆኑ ነው ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ የግንኙነት መንገዱም ሆነ መስመሩ ክርስቶስ ሲሆን እግዚአብሔርም በዚህ ጌታ አማካኝነት ከእኛ ጋር ሆኖአል ክብር ለስሙ ይሁንለት ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 14 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 23 ፣ ራዕይ 21 ፥ 3 እና 4 ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 16 እና 17 ፣ የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 47 _ 50 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንን የተቋረጠውን ግንኙነት መቀጠል የፈለገው የመጀመርያው ሰው አዳም በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ካበላሸበት ጊዜ ጀምሮ ነበር ታድያ አዳም ሆይ ወዴት ነህ ? ሲል በገነት ውስጥ መፈለጉ እግዚአብሔር የነፍስን ጥፋት አይወድምና ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ ማሰቡን የሚያመለክተን በመሆኑ አምላካችንን በብዙ እንድናመሰግነው እንሆናለን በሐዲስ ኪዳንም ኢየሱስን የላከልን ከጠፋንበት ፈልጎ ሊያገኘንና ከራሱ ጋር ኅብረት እንድናደርግ ሊያደርገን ነው የሉቃስ ወንጌል 15 ፥ 4 _ 9 ፣ የሉቃስ ወንጌል 19 ፥ 1 _ 10 እንመልከት ስለዚህ የእግዚአብሔር መሠረታዊ ሃሳቡ ተዘጋጅተው የቀረቡለት ሥዕልና ታቦት እንዲሁም ቤተመቅደስ ሳይሆን በእነዚህ በተፈለጉትና ይሠሩልኝ በተባሉት ነገሮች በኩል ከሰዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ ነው በሐዲስ ኪዳን ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ በኢየሱስ በኩል ዘለዓለማዊ ሆኖአል በመሆኑም ስለ ኅብረት ስናስብ ብዙ የሆኑ አዳማዊና አሮጌ የሆነ አስተሳሰባችንን እንድንለውጥ ትምህርቱ ይጠቁማል ጌታ የጠራን ለኅብረት ነውና ታድያ ውድ ወገኖቼ ሆይ ጌታ ለኅብረት ሲጠራን በማርቆስ ወንጌል 3 ፥ 14 መሠረት ከእርሱ ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው ስለሚል ………………….. ከአገልግሎታችንና ከስሞቻችን በፊት በቅድሚያ ከእርሱ ጋር መኖርን መውደዳችንን እንድናስቀደም ነው እንደገናም የተጠራነው ለአገልግሎት ሳይሆን በመጀመርያ ለኅብረት ስለሆነ ከእርሱ ጋር የሚኖረን ኅብረት ትክክለኛ የሚሆነው በአገልግሎት ጉዞ ውስጥ ሳይሆን ከእርሱ ጋር በመኖር ውስጥ ነው ስለሆነም ከእርሱ ጋር በመኖራቸው ምክንያት ደቀመዛሙርት የትላንት አሮጌ አስተሳሰባቸውን ማለትም ከመካከላችን ማነው ታላቅና አንዳችን በግራ አንዳችን በቀኝ መቀመጥን ስጠን የሚሉትን ፣ ሌሎችንም ምድራዊ አስተሳሰባቸውን ጥለው ጌታን አይተነዋል ለማለት የበቁት ቅድሚያውን ይዘውና የኃላፊነቱንም ቦታ ተረክበው ስላገለገሉ ሳይሆን ከሕይወት ጅማሬያቸው አንስተው ከጌታ ጋር መኖርን ስላስቀደሙ ነው አያይዘውና ቀጥለውም በዓይኖቻቸን ያየነውን የተመለከትነውን እጆቻችንም የዳሰሱትን ይህንን ጌታ እናወራላችኋለን ሕይወት ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን አሉን 1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 1 ፥ 1 _ 4 ለእኛም እንዲህ ይሁንልን የክፍል ሦስት የሥዕል ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩ ሰላም ሁኑ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

ሥዕል ከክርስትና በፊት የነበረው ገጽታ ( ዘጸአት 25 ፥ 18_ 21 ) ክፍል አንድ ሥዕል ከክርስትና በፊት የነበረው ገጽታ ( ዘጸአት 25 ፥ 18_ 21 ) ክፍል አንድ ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ በሥርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ ከሥርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደላይ ይዘረጋሉ የሥርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ ፊታቸውም እርስ በእርስ ይተያያሉ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ሥርየት መክደኛው ይመለከታሉ ዘጸአት 25 ፥ 18_ 21 የተወደዳችሁ ወገኖች የዚህ ትምህርት ተከታታዮች በሙሉ ይህንን የሥዕል ትምህርት በዛሬው ዕለት አንድ ብለን ጀምረናል የእግዚአብሔር ስም ብሩክ ይሁን ወደ ሃሳቡ ስገባ ሥዕል ከክርስትና በፊት በቤተ አሕዛብም ሆነ በቤተ አይሁድ የታወቀና ከአምልኮት ጋር የተያያዘ ነበር በቤተ አሕዛብ እንጨት ጠርቦ ደንጊያ አለዝቦ ማምለክ የተለመደ ነበር እንዲያውም የሮማ ነገሥታት አማልክት ተብለው ከመመለካቸው በላይ ከሞቱ በኋላ ሥዕላቸው በደንጊያ እና በእንጨት እየተቀረጸ ሲመለኩ መኖራቸው በታሪክ ይታወቃል ክርስትና በመጣ ጊዜ ከክርስትና ጋር ያጣላቸው ይኸው ልማዳቸው ነው በክርስትና ትምህርት ሲታይ ግን ይህ አምልኮ ጣኦት ነው ይህንን የሥዕል ትምህርት በምናጠናቅቅበት ጊዜ እንግዲህ በቤተ አሕዛብ እንጨትና ድንጋይ ጠርቦና አለዝቦ የሚደረገውን አምልኮ በሰፊው የምናየውና የምንዳስሰውም ይሆናል አሁን ግን የምናልፈው ወደ ሥዕል አገልግሎት ነው ሥዕል በቤተ አይሁድ እንደ አሕዛብ ሳይሆን በታቦተ ሕጉ በጽላተ ኪዳኑ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲሰራ ራሱ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት ነበር ታድያ እነዚህ የኪሩቤል ሥዕሎች ከታቦቱ አይለዩም ምክንያቱም ታቦት የእግዚአብሔር መገለጫ ዙፋን ስለሆነ የመንበረ ጸባኦት አምሳል ናቸውና የሚሳሉትም እንደሚናተፍ አውራ ዶሮ ሆነው ነው የንጉሥ አንግቻ ንጉሡ በተቀመጠበት በዙፋኑ ፊት ነቃ ቆጣ ብሎ እንደሚቆም እነዚህም ኪሩቤል በታቦቱ ላይ ባለው የእግዚአብሔር መገለጫ ዙፋን እንዲሁ ናቸው ከዚህ በመቀጠል የኪሩቤልን አገልግሎት ማወቅ ለምትፈልጉ ኪሩቤል የእግዚአብሔር መቀመጫዎችና የእግዚአብሔርንም መኖርያ የሚጠብቁ ምሳሌዎች መሆናቸውን የሚገልጹ ጥቅሶችን እሰጣችኋለሁ ፣ መጽሐፍቅዱሳችሁን ከፍታችሁ አንብቧቸው 1ኛ ሳሙኤል 4 ፥ 4 ፤ 2ኛሳሙኤል 6 ፥ 2 ፤ 2ኛ ነገሥት 19 ፥ 15 ፤ መዝሙር 99 ፥ 1 ከዚህ የተነሳ ሙሴ ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ፣ ኪሩቤልን በታቦቱ ላይ እንዳሉ አድርገህ ሳላቸው ወይንም ቅረጻቸው ስለተባለ ብቻ እኛም ተነስተንና ይህንኑ ቃል መነሻ አድርገን በእግዚአብሔር ስምም ይሁን በሰዎች እንዲሁም በመላዕክት ስም የምንስለውና የምንቀርጸው ምስልም ሆነ ሥዕል የለም ሙሴ ሥራልኝ የተባለበትን ምክንያት ተነጋግረናል እኛ ግን ሥዕልን የምንስልበትም ሆነ የምንቀርጽበት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደገናም መጽሐፍቅዱሳዊ የሆነ መረጃ የለንም እንደውም የተባልነው ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሆኑልህ በላይ በሰማይ ካለው ከምድርም በታች በውሃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም………….. ነው ዘጸአት 20 ፥ 1 _ 6 ፤ ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ እንዳትረክሱ የማናቸውንም ነገር ምሳሌ……………. እንዳታደርጉ ነው የተባልነው እንደውም እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ጸሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ ነው ያለን ዘዳግም 4 ፥ 15 _ 20 ወደ አዲስ ኪዳኑ የአምልኮ ሥርዓት ሄደን ስንመለከት ደግሞ በሐዲስ ኪዳንም አብ የሚሻው አምልኮ የእውነትና የመንፈስ አምልኮ ነው እንጂ በሥዕልና በምስል ላይ የተመረኮዘ አምልኮ አይደለም ስለዚህም እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚያመልኩትም በእውነትና በመንፈስ ያመልኩታል አብም እንዲህ ያለውን ይሻልና ተብሎ ነው የተጻፈልን ዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 23 እና 24 የብሉይ ኪዳኑ የእሥራኤል መሪ ሙሴ ሁለት ኪሩብ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ወይም ቅረጽ ፣ ሣል ቢለውም እንኳ ሙሉ የሆነ አምላካዊ መረጃ አግኝቶ የእግዚአብሔርንም ዓላማ መሠረት አድርጎ ሙሉ የሆነ ነገር ነው የሠራው ከዚህ የተነሳ ሥዕለ ኪሩብን ሥሎ ወይንም ቀርጾ ታቦትን ሳይሠራ አልቀረም የኪዳኑን ታቦት ሰርቶ ደግሞ መቅደሱንና ማደርያውን አልሰራም አላለም ሁሉንም ለእግዚአብሔር ዓላማ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሠራ ትምህርቱን ወደፊት የምንመጣበትና በሰፊው የምንዳስሰውም ጉዳይ ስለሆነ እያብራራነው እንሄዳለን ስለዚህ ሙሴ ገና ለገና ኪሩብን ቅረጽ ፣ ሣል ወይንም ስራ ተብሏልና እኛም እንዲሁ ተነስተን ሥዕልን እየሳልንና እየቀረጽን ካልቻልንም ደግሞ ከየገበያው ፈረንጅ ለልዩ ልዩ ዓላማ የሳላቸውን ሥዕሎችና ፎቶዎች እየሰበሰብን የአምላካችን የእግዚአብሔር ፣ የቅዱሳን መላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕለ አድህኖ ነውና ምሥጋናና ስግደት ልንሰጣቸው ይገባል ስንል የተለየ ቦታ አስቀምጠንና መጋረጃ ጋርደን የምንሰግድለት ምንም ዓይነት ሥዕልና ምስል ለእኛ የለንም እንዲህ ማድረግ ደግሞ ጣኦትን ማምለክ ስለሆነ እነዚህ ሰው ሰራሽ የሆኑ ምስልና ሥዕሎችን ከፊታችን ማራቅና ገለል ማድረግም ያስፈልገናል ስግደትም ለእግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ የምንሰግደው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ስለማንሰግድ ይህ ሲገባን ደግሞ ያን ጊዜ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ማምለክ እንጀምራለን በተደባለቀው ነገር ውስጥ ግን እግዚአብሔርን ብንጠራው እግዚአብሔር በዚያ አይገኝም እግዚአብሔር ብቻውን አምላክ ስለሆነ እኛም የምናመልከው ብቻውን ለሆነ አምላክ ክብር በመስጠት ነው 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1 : 17 ፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 16 : 25 _ 27 ፣ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6 : 16 እንደገናም ስሩ ወይንም አድርጉ ያልተባልነውን መስራት የለብንም ፣ መስራትም ሆነ ማድረግም አንችልም ትምህርቱ የሚያስተምረን እንግዲህ ይህንን እውነት ነው የክፍል ሁለት ትምህርት ይቀጥላል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 1 June 2017

የጸምና የጸሎት ጥሪ የመልዕክት ርዕስ ፦ የከበረውን ከተዋረደው ብትለይ….. ( ኤርምያስ 15 ፥ 19 _ 21 )የጸምና የጸሎት ጥሪ የመልዕክት ርዕስ ፦ የከበረውን ከተዋረደው ብትለይ….. ( ኤርምያስ 15 ፥ 19 _ 21 ) አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ ( ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 ፥ 21 ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን እግዚአብሔር አምላክ በዛሬው የጸሎት ክፍለ ጊዜ በብዙ ረድቶን ነበር የጸለይነውም እስከዛሬ በተማማርንባቸው የትምህርት አርዕስቶች ላይ ተመስርተን ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክስ እናት ቤተክርስቲያናችን በእነዚህ እውነቶች ልክ ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ተመልሳ ይህንኑ እንድትሰብክና እንድታስተምር ለመርዳት ነው ታድያ በዚህ ሁሉ የረዳንን ጌታ በቅድሚያ ላመሰግነው እወዳለሁ ከዚህ በተጨማሪም በዚህ የጸሎት ፕሮግራም ላይ የዚሁ ራዕይ ሸክም ኖሯችሁና ለመጸለይ የመጣችሁ ፣ አብራችሁን የጸለያችሁ ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር በብዙ ኃይል ይባርካችሁ ብድራታችሁንም ይክፈል በማለት ላመሰግናችሁና ልባርካችሁም እወዳለሁ ዘመናችሁ ይባረክ ከዚህ በመቀጠል ግን እንደተለመደው የሰኞና የሐሙሱ የፌስ ቡክ ላይቭ አገልግሎት ይቀጥላል ሰኞ ላይ የሚጀምር አዲስ ትምህርት ሥዕል በመጽሐፍቅዱስ እንዴት ይታያል ፣ ሥዕል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መቼ ተጀመረና የመሣሠሉትን ሃሳቦች በማንሳት መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶችን የምንማማርበት ጊዜ ይሆናል አሁንም መቅረት በብዙ የተከለከለና የማይፈቀድም በመሆኑ አትቅሩ ለማለት እወዳለሁ በተረፈ በሰኞ ፕሮግራማችን እስከምንገናኝ የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ በማለት የምሰናበታችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com