Thursday 4 May 2017

ርዕስ፦ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተከፈተ አስፈላጊም ሆኖ  የሚቀጥልና በጉጉትም የሚጠበቅ  



ታላቅ የውይይት መድረክ  





የተወደዳችሁ የዚህ ፕሮግራም ተከታታዮች በቄስ ዶክተር ዘበነ ለማና በፓስተር ዶክተር ቶሎሳ ጉዲና በእኔም በባርያው በኩል  ታቦትን በተመለከተ በተደረገው ውይይትና  በተላለፈው መልዕክት የእኛ የአድማጮች ግንዛቤ ምንድነው ትላላችሁ ? ምንስ ተረድታችኋል ? መልሳችሁስ ምንድነው  ? ይህን በተመለከተ እንግዲህ  በእኔ በኩል ብቻ ሳይሆን በቄስ ዶክተር ዘበነ ለማም ሆነ በፓስተር ዶክተር ቶሎሳ ጉዲና እንደገናም ከእናንተ ከአድማጮች ሳይቀር  የሚሰጥ ተጨማሪ ማብራርያና  የተለየ የሚባል  አስተያየት ካለም  በናፍቆትና በተስፋ የምንጠብቀው ይሆናል ማለት ነው መልሱንም ሆነ አስተያየቱን ሌላም ሊባል የተፈለገ ነገር ካለ  በፌስ ቡክ ፔጆችና ድህረ ገጾች ላይ  ማስቀመጥ ይቻላል  ተባረኩ 


ይህንን የተቀደሰ ውይይት እናዳብረው ይልመድብን እላለሁኝ 


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን 

















5 ) የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት ሆኗል


                               ክፍል አስር




የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት የመሆኑን ምስጢር በክፍል አስር ትምህርታችን ዛሬ ተማምረናል የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት የመሆኑ ምስጢር ጌታ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ዓመጻችንን ከማረ በኋላ ኃጢአታቸውን ደግሜ አላስብም በማለቱ የተገለጸ ነው ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ የተገለጠ በመሆኑም ኃጢአታችንን ደግሞ አያስብም መስዋዕት በማቅረብ ዙርያም እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት ስለ ራሱም ሆነ ስለሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መስዋዕት ሊያቀርብ ያላስፈለገው በመሆኑ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህንን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓል ከዚህ የተነሳ ዛሬ በእኛ ዘመን በሐዲስ ኪዳን የኢየሱስ መስዋዕት በቂ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ስለኃጢአት የምናቀርበው መስዋዕት የለም እን ደገናም ኢየሱስ ለእኛ ለመታረቃችን መሉ መስዋዕት ሆኖ ሙሉ የሆነ መዳንን ያመጣልን በመሆኑ ለምህረታችን የምናዘጋጀው መስዋዕትም ሆነ የምናቆመው ሊቀካህን እንደገናም የምንሰራው መቅደስም ሆነ በቅድስተቅዱሳን የምናኖረው ታቦት ለእኛ የለንም የዘላለም መስዋዕታችንም ሆነ አስታራቂያችን ኢየሱስ ሲሆን ለኢየሱስ ማደርያ ልንሆን ቅድስተ ቅዱሳን ወይም መቅደስ ተብለን የተጠራን ደግሞ እኛ ነን ከዚህም ሌላ ኢየሱስ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ በሰማይ ወዳለው ቅድስተቅዱሳን ሲገባ በምትበልጠውና በምትሻለው በሰው እጅም ባልተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን መልካም ሊቀካህን ሆኖ ነው ስለ እኛ የገባው ውድ ወገኖቼ የትምህርቱ ይዘት በአጭሩ ይህን ሲመስል ከዚሁ ጋራ አያይዤ በቀሲስ ዶክተር ዘበነ ለማ እና በቄስና ፓስተር ዶክተር ቶሎሳ ጉዲና መካከል የብሉይ ኪዳኑ ታቦትም ሆነ ሊቀካህኑና መቅደሱ አንድ ነው ? ወይስ ከአንድ በላይ ? እንደገናም የብሉይ ኪዳኑ የመቅደሱ የመስዋዕቱ የሊቀካህኑና የታቦቱ ሥርዓት ዛሬ በሐዲስ ኪዳን መልኩን ሳይለውጥ እንደነበረ ቀጥሎአል ? ወይስ የተለወጠ ነገር አለ ? በሚሉት ሃሳቦች ዙርያ የተወያዩበትን ወደ መድረኩ በማምጣት ሕዝቡ ይበልጥ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን እውነት በማከል ለሕዝቡ ማስጨበጥ ወድጃለሁ ወገኖች የተዘጋጀውን ትምህርት ሰምታችሁ ሼር አድርጉ በተጨማሪም እነዚህ ሁለት አባቶች የተወያዩበትን በዩቲዩብ የተለቀቀውን ቪዲዮ ከዛሬው ትምህርት ጋር በማቀናጀት እየሰማችሁ እንደ ቃሉ የተነገረው እውነተኛው ትምህርት የቱ እንደሆነ አውቃችሁ ትክክለኛውን መረዳት እንድትይዙና በእውነትም ላይ እንድትቆሙ ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ





Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ





yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment