Friday 27 January 2017

የመልዕክት ርዕስ ፦ የእግዚአብሔርን ቃል በሰዎች ሕይወት ውስጥ ማጽናት ( እርግጠኛ ማድረግ ) ዕብራውያን 2 ፥ 3...የመልዕክት ርዕስ ፦ የእግዚአብሔርን ቃል በሰዎች ሕይወት ውስጥ ማጽናት ( እርግጠኛ ማድረግ )ዕብራውያን 2 ፥ 3 እና 4 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ መልዕክት ለሁላችንም በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ የሆነ መልዕክት በመሆኑ በብዙ ልታደምጡት ይገባል ስል ላሳስባችሁ እወዳለሁ ከቪዲዮው መልዕክት እንደምትሰሙት በአጭሩ ከጌታ የሰማነውን የእግዚአብሔርን ቃል ማጽናት በምንጀምርበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል በሰሙና ሊሰሙ ባሉ ፣ በሚሰሙም አማኞች ሕይወት ውስጥ ቃሉ እውነት ይሆናል እውነትም ሆኖ ይቀራል ከዚህም የተነሳ ቃሉን የሰሙ አማኝ ክርስቲያኖች የሕይወት አካሄድ እና የኑሮ ሥርዓት የአመለካከትም ለውጥ ያደርጋሉ ከጌታ የሰማነውን ቃል ማጽናት በማንችልበት ጊዜ ደግሞ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል እውነት አይሆንም ከዚህ የተነሳም ሰዎች ከክፉ መንገዳቸው አይመለሱም እንደውም እኛ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለእነርሱም ጭምር ይሆናል ብለን የጀመርነውን የእግዚአብሔር ነገር አቋም ኖሮንና በአቋማችንም ጸንተን ቃሉን በራሳችን ሕይወትም ሆነ በሰሚዎች ሕይወት ካለማጽናታችን የተነሳ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሰሚዎቻችንም ጭምር ነገሩ ይበልጥ መሰናከያና ኃጢአት ይሆንባቸዋል እንደገናም እርግጠኝነትና የእግዚአብሔርንም ቃል ማጽናት ከሌለ ሰዎች የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር እስከ መቁጠር ይደርሳሉ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋሉ ስለዚህ እኛ በእውነት የጌታ አገልጋዮች ከሆንን ከጌታ የሰማነውን የእግዚአብሔርን ቃል በሰዎች ሕይወት ውስጥ ማጽናትና ማረጋገጥ አለብን ይህን በምናደርግበት ጊዜ ጌታም ከእኛ ጋር ሆኖ ይሰራል በሚከተሉትም ምልክቶችና ተአምራቶች ቃሉን ያጸናል በማለት ነበር የተነጋገርነው ታድያ ይህቺን አጭር መልዕክት የጻፍኩት ከዚህ በመቀጠል ለምትሰሙት ቪዲዮ እንደ መንደርደርያ ይሆናችኋል ብዬ ስላሰብኩ ነው ተባረኩልኝ በጌታ ፍቅር እወዳችኋለሁ እጸልይላችኋለሁ የቪዲዮውን መልዕክት ብትችሉ ያልሰሙ እንዲሰሙ ሼር አድርጉት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 19 January 2017

የመልዕክት ርዕስ ፦ ያልተለመደ ነገር ያደርጋልና የእግዚአብሔርን ነገር ተረኛ እግዚአብሔርንም ወረፈኛ አታድርገው (...አንኳር የሆኑ የመልዕክቱ ዋና ዋና ሃሳቦች እግዚአብሔር ተገለጡ የሚለን በአክአብና በመንግሥቱም የሚያስፈልገን በኤልያስ ዘመን እንደመጣው ዝናብ ዝናብን አምጥቶ ተደናቂ ባርያዎች መሆናችንን ሊያስመሰክርልን ወይም ሊያረጋግጥልን ሳይሆን እንደዚሁ እንደ ኤልያስ አሁንም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠውያ እንድናበጅ ሊያደርገንና ጉልበትም ሊሆነን ነው ኤልያስ ተገለጥ ዝናብ እሰጣለሁ ስለተባለ በአክአብ መንግሥትና ሕዝብም ሳይቀር ስለተፈለገ እንዲሁ በቀላሉ ሄዶ ከበዓል ነቢያትና ከመሥዋዕቶቻቸው መልስ መሠውያን ያቀረበ አልሆነም ይህንን ያደረገ ቢሆንማ እግዚአብሔርን ተረኛና ተራውም የደረሰ ወረፈኛ ባደረገው ነበር ነገር ግን ኤልያስ አምላኩን ለወረፋ የተዘጋጀ ከበዓልም ነቢያት አገልግሎት ለጥቆ የሚሠራ ተረኛ አላደረገውም ይህንንም የምናውቀው ከኤልያስ ከንግጝሩ፣ ከሰጣቸው መልሶቹና ከድርጊቱ ተነስተን ነው ይህንንም ለማወቅ እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡአቸው 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 15 ፣ 16 _ 29 ፣ 30 _ 46 ይህ ኤልያስ ታድያ ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠውያ ሲያበጅ በሌላኛው ገጽታ ወይም በተዘዋዋሪ የበዓልን ነቢያት መሠውያቸውንም ሆነ መሥዋዕታቸውን ሙሉ ለሙሉ እያፈረሰውና ዋጋም እያሳጣው መሆኑን ሁላችንም በይበልጥ የምንገነዘበው ጉዳይ ሊሆን ይገባል እርሱ ገና ሕያው እግዚአብሔርን ለእርሱ እገለጣለሁ ሲል የበዓል ነቢያት መሠውያቸውም ይሁን መስዋዕታቸው እንዲሁም ትንግርታቸውና ሟርታቸውም ጭምር ፈርሷል አሁንም እስከ ለዘለዓለሙ የፈረሰ ይሁን ሙሉ ትምህርቱን ለማግኘት ቪዲዮውን ይከታተሉ ጌታ እግዚአብሔር ዘመንዎን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry አገልጋይና የአገልግሎቱ ባለአደራ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ተባረኩ

Friday 13 January 2017

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የጾምና የጸሎት ጥሪ ለቅዱሳን ወገኖችሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ጸጋና...

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: የጾምና የጸሎት ጥሪ ለቅዱሳን ወገኖች





ሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ጸጋና...
: የጾምና የጸሎት ጥሪ ለቅዱሳን ወገኖች ሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry...

የጾምና የጸሎት ጥሪ ለቅዱሳን ወገኖች


Image result for prayer





ሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ይህ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው በነገው ዕለት በካናዳ ኦታዋ የሰዓት አቆጣጠር 10 30 In the Morning  የሚጀምር የጾምና የጸሎት ጊዜ ይኖረናል ይህንንም የማስተላልፈው እንደተለመደው በፌስ ቡክ ላይቭ ስለሆነ በዚሁ በነገው ዕለት በሰዓቱ ተገኝታችሁ አብረን እንድንጸልይና በጌታም ፊት እንድንወድቅ ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ 


የኔ ምስጋና ዝናብ እንደ ሌለው ደመና አይደለም የኔ ምስጋና 



  


ከተባረከችዋ ዘማሪት ሶፍያ ሽባባው መዝሙር  ጋር በመሆን የሚቀጥል የጽሞና ጸሎት 


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ 




እግዚአብሔርን ስንከተል ወይንም ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ዘፍጥረት 39 ፥ 20 _ ፍ ጻሜ ( ክፍል አስር ) ቊጥር 2

Friday 6 January 2017

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 11እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 11 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አረጋውያን አባቶች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሕዝበ እግዚአብሔር ምዕመናን በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ከዚህ በመቀጠል በ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry በኩል የተዘጋጀ የልደት መልዕክት ስላለ እርሱን እንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ እና ተከታተሉ መልዕክቱም በቪድዮ ጭምር የተዘጋጀ ስለሆነ ተባረኩበት እግዚአብሔርንም በቃሉ አክብሩት በዳዊት ከተማ የተወለደልን መድኃኒት ክርስቶስ ጌታ የሆነ ነው የተወለደው ለእኛ ስለሆነ ተወልዶላችኋል ተባልን ወይቤሎ መልአክ ኢትፍርሁ እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኲሉ ዓለም እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት ወደ አማርኛው ስተረጉመው መልአኩም እንዲህ አላቸው እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ይለናል የሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 10 እና 11 በመሆኑም ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች መባሉ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ስለተወለደ ነው መድኃኒትነቱ ለሕዝቡ ሁሉ ነውና ስለዚህ ይሄ መድኃኒት ለእኔ አያስፈልገኝም የሚል ከሰው ወገን ማንም የለም ሊኖርም አይችልም ለምን ስንል ሁሉ ኃጢአትን ሠርቷል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል የሚል የእግዚአብሔር ቃል ተጽፎልናልና እንደገናም የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው በመሆኑም ኃጢአት ሰዎችን ሁሉ ከክብር ያጎደለ ብቻ ሳይሆን ክፍያ ወይም ደሞዝም ጭምር ሆኖ ሰዎችን የገደለ ነው ሮሜ 3 ፥ 23 ፤ ሮሜ 6 ፥ 23 ይሁን እንጂ ኢየሱስ የኃጢአትና የሞት መድኃኒት ሆኖ ተወለደ ለዚህም ነው ወትወልድ ወልደ ወትሰምዮ ስሞ ኢየሱስሃ እስመ ውእቱ ያድህኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ ያለው ወደ አማርኛው ስተረጉመው ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ በማለት የሚናገር ነው የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 የሞት መድኃኒት ስለመሆኑ ደግሞ ወይቤላ እግዚእ ኢየሱስ አነ ውእቱ ትንሣኤ ወሕይወት ዘየአምን ብየ እመኒ ሞተ የሐዩ ወኩሉ ዘሕያው ወየአምን ብየ ኢይመውት ለዓለም ተአምኒኑ ዘንተ በማለት ተናግሮአል አሁንም ይህንን ወደ አማርኛው ስተረጉመው ኢየሱስም ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል ሕያው የሆነ የሚያምንብኝ ሁሉ ለዘላለም አይሞትም ይህን ታምኛለሽን አላት እያለ ይነግረናል የዮሐንስ ወንጌል 11 ፥ 25 _ 27 ይህ ጌታችን መድኃኒት ሆኖ የተወለደልን ጌታ በመሆኑ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች ነው ስለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው በማለት ከኃጢአተኞችም ዋናው እርሱ መሆኑን ከነገረን በኋላ ባለማወቅ ስላደረግሁ በዚሁ ጌታ ምሕረትን አገኘሁ አለን 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 12 _ 17 ውድ ወገኖቼ ሆይ ይህ የተወለደልን ጌታ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን መድኃኒት ስለሆነ በዚሁ ጌታ ምሕረትን ያገኘው ጳውሎስ ብቻ ሳይሆን ቃሉ እንደሚነግረን የሰው ዘር በሙሉ ማለት ሁላችንም ልንቀበለው የተገባ መሆኑን በግልጽ ያሳውቀናል ኢየሱስ የመጣውም ጻድቃንን ሊጠራ ሳይሆን ኃጢአተኛችን ሊያድን ነው ስለዚህ በስሙ ንስሐና የኃጢአት ሥርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል እስከ አሁኑ እስከዚች ሰዓት ድረስም እየተሰበከ ይገኛል አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ