Saturday 24 December 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ ለአምልኮ የሆነ የጌታ መገለጥ ለእረኞች ( የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፥ 20 )ወተመይጡ ኖሎት እንዘ ይሴብሕዎ ወየአኩትዎ ለእግዚአብሔር በእንተ ኵሉ ዘርእዩ ወሰምዑ ዘከመ ይቤልዎሙ ትርጉም ፦ እረኞችም እንደተባለላቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እያከበሩ ተመለሱ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፥ 20 የመልዕክት ርዕስ ፦ ለአምልኮ የሆነ የጌታ መገለጥ ለእረኞች ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን በመጀመርያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የመታሰብያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይህ በዓል ለሁላችሁም የበረከት የደስታና የሰላም በዓል እንዲሆንላችሁ ጸሎቴም ምኞቴም ነው በዛሬው ዕለት እረኞችም እንደተባለላቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እያከበሩ ተመለሱ በሚለው የምንባብ ኃይለ ቃል የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ፥ 8 _ 20 መሠረትለአምልኮ የሆነ የጌታ መገለጥ ለእረኞች በሚል ርዕስ አጭር መልዕክት ይኖረኛል በዚህ መልዕክት ጌታ ሁላችንንም ይባርከናል መልዕክቱን ከሰማችሁ በኋሏ ለሌሎች ሼር በማድረግ ተባበሩ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለእጓለ እመሕያው ሥምረቱ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment