Saturday 31 December 2016

የአዲሱ ዓመት መግቢያ የጸሎት ጊዜና የመሪ ጥቅስ ቃል መቀበያ ጊዜ ቃልህ ተገኘቷል ……..ኤርምያስ 15 ፥ 16 ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ ትንቢተ ኤርምያስ 15 ፥ 16 ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን አሁንም በድጋሜ እንኳን ለሁለት ሺህ አስራ ሰባት ዓመተ ምሕረት አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ Happy new year 2017 All People of God ይህ ዓመት የበረከት የመጽናናት እና የምስጋና የድል ዓመት ይሁንላችሁ እያልኩ በትላንትናው ዕለት ማለትም ዓርብ ታህሳስ 30 2016 Friday December 30 2016 የአዲስ ዓመት መቀበያ የጸሎት ጊዜና መሪ ጥቅስ የምንወስድበት ጊዜ በመሆኑ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ማስታወቅያ በመስራት በፌስ ቡክ ድኅረ ገጼ ላይ በለጠፍኩት መሠረት እናንተም ቅዱሳን ዛሬ Saturday December 31 10 : 30 A.M በሰዓቱ መጥታችሁ የዚሁ የጸሎቱና የዓመቱ መሪ ጥቅስ በረከት ተካፋይ ስለሆናችሁ ጌታ ይባርካችሁ ልላችሁ እወዳለሁ ይህ የምትቀበሉት አዲስ ዓመትም ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ የምትሻገሩበት ዓመት ስለሆነላችሁ ጌታን ከልብ እባርከዋለሁ በመቀጠልም ከላይ በመግቢያዬ በጠቀስኩት ቃል መሠረት ይህ አዲስ ዓመት የእግዚአብሔር ቃል ለቅዱሳኑ የሚገኝበት ዓመት ቅዱሳኑም በጸሎትና በእግዚአብሔር መንፈስ ጉልበት የተገኘውን ቃል የሚበሉበት ዓመት ከዚህ ፈቅደውና ገብቷቸው ከበሉት ቃል የተነሣም ሐሴታቸውና የልባቸውም ደስታ የሚመለስበት ዓመት ነው ታድያ ነገሩ ገብቶት ፈቅዶና ወዶ ይህን የጌታውን ቃል ሊበላ የተዘጋጀና የበላ ሁሉ ይሄ ይሆንለታል ይሁን እንጂ ይሄ መብል እንዲሁ ከጌታ ቸርነት የተነሳ በምህረቱና በጸጋው የተገኘ መብል ስለሆነ ብቻ ማንም ከሜዳ ተነስቶ የሚበላው አይሆንም ይህንን መብል ለመብላት ሕጻንነትን መሻርና የወተቱንም ወራት ማለፍን ይጠይቃል 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 1 _ 4 ይህንን መብል የሚበሉ ሰዎች ደግሞ እንደ ወተቱ ዘመንና እንደ ለጋነቱም የዕድሜ ክልል ደረጂ የሚጋቱ ሰዎች ሳይሆኑ የምግቡን ጥቅም አውቀውና እንደ ሕጻንም ከመጋት ወጥተው እራሳቸውንም ችለው የሚመገቡ የተመገቡትንም የሚያጣጥሙ በማጣጣምም ላይ የሚገኙ ሰዎች ናቸው እንደገናም እነዚህ ሰዎች የተመገቡትን ዓይነት መልክ በተመገቡበት መጠንና ልክ ያወጣሉ ያም መልክ ኢየሱስን ሊመስሉ የተወሰነባቸው መልክ በመሆኑ የኢየሱስን ዓይነት መልክ ያሳያሉ ሮሜ 8 ፥ 29 ፤ 1ኛ ዮሐንስ 3 ፥ 2 ታድያ ይህንኑ ምግብ ተመግቦ ይህንን የኢየሱስን ዓይነት መልክ ለመያዝ ግን እንዲሁ በቀላሉ የሚሆን ነገር አይደለም ስለዚህም በሕዝቅኤል 2 ፥ 8 _ 10 ላይ አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ የምነግርህን ስማ እንደዚያ አመጸኛው ቤት አመጸኛ አትሁን አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ ሲል ቃሉ የመከረን በዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ ጴጥሮስና ደቀመዛሙርቱ ዓሣ ልናጠምድ እንሄዳለን ሲሉ ወደ ጌንሳሬጥ በሄዱበት ዘመን በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የተላለፉበት ጊዜ ስለነበር የወጡትም ያለ ቃል ነበረና ማለትም በተገኘ ቃል ስላልነበረ ሌሊቱን ሙሉ ሲደክሙ ከማደር በስተቀር ምንም ያገኙትም ሆነ ያጠመዱት ዓሣ አልነበረም ከዚህ የተነሣ ተስፋ ቆርጠው መረቦቻቸውን እያጠቡ ባሉበት ሰዓት ወደ ማለዳው ላይ ኢየሱስ መጥቶ ከታንኳቸው በአንዲቱ ተቀምጦ በማስተማር የሚበሉትን ቃል አስገኘላቸው ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ታሪክ የተለወጠው የእግዚአብሔር ቃል ጥማተኛውና ፈጣኑ ጴጥሮስ እውነቱን በመናገር አቤቱ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም አሁን ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላሉ ሲል ወስኖ ባገኘው ቃል አማካኝነት መረቦቹን ከጣለበት ጊዜ ጀምሮ መረቦቻቸውን በመቅደድ ሊጎትቱት ሳይቀር ያቃቷቸው ዓሦች ከባሕሩ መካከል ተገኙ የሚበላ ቃል በተገኘበት ቦታ ሁሉ የኑሮ ለውጥና የሕይወት ለውጥ ጭምር ይሆናል ምርኮ ይመለሳል አሸናፊነትና ድልን መቀዳጀት ሁሉ ይመጣል የጌታና የጌታ ብቻ መሆንም ይቻላል ደቀመዛሙርቱ የሆኑት እንደዛ ነበረ ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው የጌታና የጌታ ብቻ ሊሆኑ ሁሉን ትተው ተከተሉት የሉቃስ ወንጌል 5 ፥ 1 _ 11 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 21 ፥ 1 _ 14 ስለዚህ ይሄ አዲስ ዓመት በተገኘው ቃልና እኔም በልቼዋለሁ በምንለው ቃል ለነጴጥሮስ የመጣው በረከት ለሁላችንም ይሆናል ቅዱሳን ዘመናችሁ የተባረከ ይሁን በማለት አዲሱ ዓመት ለሁላችሁም የተገኘውን የጌታን ቃል የምትበሉበትና እርሱኑ የምትመስሉበት እንደገናም ለጌታና የጌታ ብቻ የምትሆኑበት ዓመት እንዲሆንላችሁ የዘወትር ምኞቴም ጸሎቴም ነው መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ ተባረኩ ሰላም ሁኑ ከአዕላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል መዝሙር 118 : 72 ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፍህ ጣፈጠኝ መዝሙር 118 : 103 ፤ ሕዝቅኤል 3 ; 1 - 3 ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment