Friday 2 December 2016

የትምህርት ርዕስ :---- እግዚአብሔርን መከተል ( 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 እና 11 ) ክፍል አንድየተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት ዛሬ ጀምረናል በመሆኑም ይህ ትምህርት በተከታታይነት በተለያዩ ንዑሳን አርዕስቶች ዙርያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ በመሆኑ እንዳያመልጣችሁ ስል ለማሳሰብ እወዳለሁ የክፍል አንድ ትምህርታችን እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ የጀመረ ሲሆን የተነሳሁበት የመጽሐፍቅዱስ መነሻ ክፍል 1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 10 እና 11 ነው የዚህ መልዕክት ዋና ሃሳብ እግዚአብሔር ከሕይወታችን የሚፈልገው እርሱን መከተላችንን እንጂ ንግሥናችንን አገልግሎታችንን እና ለእርሱ የምናደርገውን ነገር አይደለም የሚል ነው እግዚአብሔርን መከተል ማለት ደግሞ ለቃሉ ታዞ ቃሉ የሚለውን ነገር ማድረግ ነው የሚለውንና ሌሎችንም ሃሳቦች ያካትታል ትምህርቱ በክፍል አንድ ይጀምር እንጂ ክፍል ሁለትና ክፍል ሦስት እያለ ይቀጥላል ቅዱሳን ወገኖች እንግዲህ ትምህርቱን ተከታተሉ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment