Tuesday 1 November 2016

በልዩነት መውጣት ሥር ሀ ) ተጣልቶ መውጣት ሳይሆን ተጠልቶ መውጣት የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ለተከታታይ ሳምንታት የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ን እንማማራለን የምንማማርበት መንገድም ይህንኑ ምዕራፍ በተለያዩ ንኡሳን አርዕስቶች በመከፋፈል እና ለእናንተ ለአድማጮች እንደሚከተለው በማቅረብ ይሆናል ታድያ በዛሬው ዕለት ልነሳበት የወደድኩት የምንባቡ ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ቊጥር 34 ሲሆን ቃሉም እንዲህ የሚል ነው መልሰው አንተ በኃጢአት ተወለድህ አንተም እኛን ታስተምረናለህን ? አሉት ወደ ውጪም አወጡት ይለናል ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ የትምህርቱን ዋና አርዕስትና ንዑስ አርዕስቱን ለእናንተ ለወገኖች እሰጣለሁ የትምህርቱ ዋና አርዕስት 1ኛ ) በልዩነት መውጣት የሚል ሲሆን በልዩነት መውጣት ስል በምንባቡ መሠረት ይህ ዓይኑ የበራለት ወይንም የተፈወሰው ሰው ወደ ውጪ መውጣቱ ከልዩነት የተነሣ የመጣ መውጣት እንጂ ከጥላቻ የሆነ መውጣት አልነበረም እና የመልዕክቱ ንዑስ አርዕት ደግሞ ሀ ) ተጣልቶ መውጣት ሳይሆን ተጠልቶ መውጣት ፦ የሚለውን ሃሳብ ይዞአል ስለዚህ ተጣልቶ መውጣት ሳይሆን ተጠልቶ መውጣት ምን እንደሚመስል ከክፍሉ ሃሳብ ተነስቼ ለእናንተ ለአድማጮች የማብራራው ይሆናል ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ ተከታታይነት እና ቀጣይነት ያለው ስለሆነ ይኸው አንድ ብሎ ለእናንተ ጀምሮአል እናንተም ትወዱታላችሁ ትባረኩበታላችሁ ስለዚህ ሳያመልጣችሁ ሁሉንም ትምህርት ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ

No comments:

Post a Comment