Thursday 10 November 2016

3ኛ ) ዮሴፍ እኔ እሞታለሁ የማለቱ ምሥጢር ዘፍጥረት 50 ፥ 15 _ 26 ፣ ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 1 በሙሉበሰዎች እውቅና ሥር አትቀመጡ ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው እርግጥ ነው በሕይወታችን የሚመጡ ወይም የመጡ እግዚአብሔርም የሚያመጣቸው አንዳንድ ሰዎች ለመባረካችን ለመብዛታችን ለመግቦታችን ለመጽናናታችን ደስ ለመሰኘታችን ምክንያቶች ናቸው ዮሴፍ ለእስራኤል ከፍርሃታቸው ለመላቀቃቸው ለመግቦታቸው ለመጽናናታቸውና ደስ ለመሰኘታቸው በጌሣም ምድር ለመቀመጣቸው ለመግዛታቸው ለመርባታቸው እየተጨመሩም ለመብዛታቸው ምክንያት ነበር ይህ ሁሉ የሆነው ግን ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ እስኪነሣ ነበር የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 18 አንዳንድ ሰዎች ሰዎችንና ነገሮቻቸውን ተስፋ አድርገው ይቀመጣሉ ለዚህም ነው በሕይወታቸው የበዛ ልቅሶና ጩኸት ውስጥ የሚገቡት ሰማይ ይከደንባቸዋል ምድሩም ናስ ይሆንባቸዋል ከዚህም ሌላ ትምህርቱ በዚህ ሳይጠቃለል በመቀጠል ለእግዚአብሔር እውቅና ሰጥታ ኑሃሚንን ስለተጠጋቻት ከእርስዋም ጋር ለመሄድ ስለቆረጠችው ስለ ሩት ይናገራል በእግዚአብሔር እውቅና ሥር ስንቀመጥ እንደ ሩት እግዚአብሔር አያሳፍረንም ሩት ለእግዚአብሔር እውቅና ሰጥታ ኑሃሚንን ተከትላ በሄደችበት ነገር ሁሉ አላፈረችም ታድያ መከተላችን ከጥቅምና ሥጋዊ ፍላጐታችንን ከማሟላት አንጻር ሊሆን አይገባም ሩት ኑሃሚንን ስትጠጋ ያየችው ምንም ዓይነት ጥቅም የለም ይህንንም እንድታይ የሚያደርጋት በኑሃሚን ዘንድ ያለ ምንም ዓይነት ጥቅማጥቅምም ሆነ አንድ ሁለት ተብሎ የሚቆጠር ሃብት የለም ምክንያቱም ኑሃሚን ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑሃሚን አትበሉኝ በሙላት ወጣሁ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ እያለች ባዶ እጇን መሆንዋን እያወጀች ያለችበት ጊዜ በመሆኑ ኑሃሚን ባዶ እጇን የሆነች የምታሳዝን ሴት ናት ስለዚህ ሩት ያደረገችው አንድና አንድ ነገር ቢኖር አምላክሽ አምላኬ ሕዝብሽ ሕዝቤ …………… በማለት በቁርጥ ውሳኔ እርሱን እግዚአብሔርን መከተል ብቻ ነው በመጨረሻም የትምህርቱ ማጠቃለያ በዮሴፍ ሃሳብ የተቋጨ ነው ዮሴፍ እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔር መጎብኘትን ይጐበኛችኋል ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል ብሏቸው ነበርና ዮሴፍ እኔ እሞታለሁ ማለቱ እስራኤል በእግዚአብሔር እውቅና ሥር እንዲቀመጡ ለማድረግ ነው እነዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን ከሸጡበትና ዮሴፍ ሞቶአል አውሬም በልቶታል ብለው ከዋሹበት ጊዜ ጀምሮ የአባቶችን ተስፋ የጣሉ በያዕቆብም ተስፋ ሥር ሆነው እንዲሁ ተስፋ በሌለው ሕይወት ሲንከባለሉ ግብጽ የደረሱና በዮሴፍ እጅ የወደቁ ናቸው ይህንንም የምናውቀው ለዮሴፍ አማላጅ በላኩበት ጊዜ እና እኛ ለአንተ ባርያዎችህ ነን ሲሉ በሰገዱበት ሰዓት ነው ዘፍጥረት 50 ፥ 15 _ 18 የአባቶች የነአብርሃም ተስፋ ግን የጀመረው ከአባታችን ከአብርሃም ስለሆነ አባታችን አብርሃም የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራ በአመነበት የሁላችን አባት ነው ስለሚል አብርሃም ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ስለ እስራኤልም ሆነ ስለ አሕዛብ በእምነት የተቀበለው ተስፋ ነበርና አብርሃም የእነዚህ የውሸተኞች የዮሴፍ ወንድሞችም አባት ነው ዘፍጥረት 15 ፥ 12 _ 21 ፣ ሮሜ 4 ፥ 16 _ 21 አባታቸው ያዕቆብ ብቻ ነው ይህንን ተስፋ ያልጣለው ዘፍጥረት 46 ፥ 1 _ 4 ይሁን እንጂ ይህ ተስፋ በሐዲስ ኪዳን አካል ይዞአል ቆላስያስ 2 ፥ 16 _ 19 ፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 20 ስለዚህ አሁን ላይ ያለን እኛ ተስፋ ኪዳን መሐላ አካል ወደ ያዘበት ሕይወት መጥተናል ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ትጐበኛላችሁ ሳይሆን የሚለን ተጐብኝታችኋል ነው የሚለን የተወደዳችሁ ቅዱሳን እንግዲህ በእግዚአብሔር እውቅና ሥር ተቀመጡ በሚል ዋና አርዕስት 1ኛ ) በሰዎች እውቅና ሥር አትቀመጡ 2ኛ ) ለእግዚአብሔር እውቅና ሰጥታ ኑሃሚንን ልትከተል የቆረጠችዋ ሩት 3ኛ ) ዮሴፍ እኔ እሞታለሁ የማለቱ ምሥጢር የሚሉትን ንኡሳን አርዕስቶች ይዘን እንማማራለን ወገኖቼ ቅዱሳን ቪዲዮውም እንግዲህ በዚህ መልኩ የተለቀቀ በመሆኑ እንድትከታተሉ አበረታታለሁ ትባረካላችሁ የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛላችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ የዚህን ቪዲዮ ሙሉ መልዕክት ከፌስቡክ ድኅረ ገጼ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ተባረኩ

No comments:

Post a Comment