Monday 29 February 2016

( ትምህርት አራት ) የትምህርቱ ርዕስ ፦ የተስፋን ቃል ስለ መቀበልና ስለ መጠበቅ ( ዕብራውያን 10 ፥ 23 ፤ ... የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ የተስፋን ቃል ስለ መቀበልና ስለ መጠበቅ ( ዕብራውያን 10 ፥ 23 ፤ ሮሜ 4 ፥ 18 ) 1ኛ ) እግዚአብሔር በመጀመርያ ለሰው ልጆች የሰጠው ተስፋን ነው በቲቶ መጽሐፍ ምዕራፍ 1 ፥ ቊጥር 1 እና 2 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥ ይለናል ቲቶ 1 ፥ 1 እና 2 ስለዚህ የተስፋን ቃል የምንቀበለው በቃሉ ተስፋን ከሰጠን ከማይዋሸው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ለምን ስንል ፦  ሀ ) የተስፋን ቃል የሰጠ የታመነ ነውና ዕብራውያን 10 ፥ 23  ለ ) የተስፋን ቃል መቀበል እንደሚያስፈልገንና ጥቅምም እንዳለው የዕብራውያን ጸሐፊ ነገረን ጥቅሙም በዚሁ የተስፋ ቃል የዘላለምን ርስት ማግኘት ነው ለዚህ ደግሞ ኢየሱስ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ሆነ ዕብራውያን 9 ፥ 15  ሐ ) እግዚአብሔር ተስፋን የሰጠ በመሆኑ የተስፋን ቃል በመቀበል ዙርያ አብርሃም ያደረገው ፦ ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ ይለናል ሮሜ 4 ፥ 18 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 5  መ ) ይህንኑ የተስፋን ቃል በመቀበል ጉዳይ አሁንም አብርሃም የተስፋን ቃል የተቀበለ የመጀመርያው የወንጌል ተሰባኪ አማኝ በመሆኑ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው ተባለ ሮሜ 4 ፥ 17 ፤ ገላትያ 3 ፥ 8 እና 9 ፤ ዘፍጥረት 17 ፥ 5 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 5 ፥ 21 2ኛ ) የዕብራውያን ጸሐፊ እንደተናገረው የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ይለናልና ዕብራውያን 10 ፥ 23 ታድያ የተስፋችንን ምስክርነት ፣ የተሰጠንንም የተስፋ ቃል የምንጠብቀው እንዴት ነው ? ስንል አሁንም የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠን መልስ አለ  ሀ ) በ2ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 20 ላይ እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው ይለናል በመሆኑም በእርሱ የተሰጡ ተስፋዎች አዎን የሚሆኑት በእርሱ ነውና እኛም በእርሱ አማካኝነት ለእግዚአብሔር ክብር አሜን የምንለው በእርሱ ምክንያት ነው  ለ ) አብርሃም ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት አሁንም አብርሃም አባት የሆነው አሜን ብሎ የተስፋውን ቃል ተቀብሎ ባመነበት አምላክ ምክንያት ነው ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ ይለናል ሮሜ 4 ፥ 18 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 5  ሐ ) ይሁን እንጂ አብርሃም ተስፋን ይዞ አምኖ ያልቀረ ነበረ የመቶ ዓመት ሰው ሆኖ ሳለ የራሱም ሰውነት ሆነ የሣራ ማኅፀን ምውት እንደነበረ እያወቀ በእምነቱ አልደከመም ይለናል ታድያ አብርሃም የራሱም ሰውነት ሆነ የሣራ ማኅፀን ምውት እንደነበረ ያወቀ ቢሆንም በእምነቱ ያለመድከሙ ጉዳይ ገሃዳዊውን እውነትና ነባራዊውን የራሱን ሰውነት እንደገናም የሣራን ምውት ማኅፀን ሁኔታ ከመካድ አንጻር አልነበረም ሮሜ 4 ፥ 19  መ ) ስለ አብርሃም የሮሜ መጽሐፍ በእርግጠኝነት በእምነቱ አልደከመም ያለን ቢሆንም በመጀመርያው የማመን ዘመኑ የተስፋው ቃል በጊዜው ወደ እርሱ በመጣ ሰዓት ግን በሕይወቱ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ እንደነበር የዘፍጥረት መጽሐፍ በቅድምና ይነግረናል ሚስቱ ሣራም እንደዚሁ በመጣላት የእግዚአብሔር መልዕክት ትልቅ የሆነ የእምነት ቀውስ ውስጥ ገብታ እንደነበር የክፍሉ ሃሳብ ያስተምራል ዘፍጥረት 17 ፥ 17 ፤ ዘፍጥረት 18 ፥ 11 - 15  ሠ ) ነገር ግን አብርሃም ብቻ ሳይሆን ሣራ ራሷ ደግሞ ከዚያ ትልቅ ከሆነ የእምነት ቀውስና ከፍተኛ ከሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ወጥታ ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች ዕብራውያን 11 ፥ 11 እና 12  ረ ) በዚህ ጉዳይ አሁንም አብርሃም በእምነቱ ያልደከመ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብር የሰጠ ፣ የእግዚአብሔርንም ተስፋ ቃል ያልተጠራጠረ ነበር ሮሜ 4 ፥ 20 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 1 _ 8  ሰ ) እንደገናም ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም በመሆኑም ከዚህ ሃሳብ በመነሳት ይኸው አብርሃም እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም በሙሉ ልብ እርግጠኛ ነበር የሚለውን እውነት ያስጨብጠናል ሮሜ 4 ፥ 21 ፤ ዘፍጥረት 18 ፥ 14 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 19 ፥ 26 የተወደዳችሁ ቅዱሳን የትምህርቱ ሃሳብ በአጭሩ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ከዚህም ባሻገር በቪዲዮ የተለቀቁ ተከታታይ ሃሳቦች ስላሉ እነዚህን የተለቀቁትን ትምህርቶች እየገባችሁ በመስማት ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉአቸው በአክብሮትና በትሕትና እጠይቃለሁ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ አሜን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

00005

00005

00004 ዮሴፍ ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት በእምነት ተናገረ ዕብራውያን 11 ፥ 22

Tuesday 23 February 2016

የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13 _ 15 ) የክፍሉ ሃሳብ ለምን ይህንን ተናገረ ? ስንል በተጻፈው ቃል መሠረት ከሕግ የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል ወደ ማለት ሃሳብ ሰዎች ሊመጡ የሚችሉ በመሆናቸው ይህንኑ ከሕግ የሆነ ወራሽነትን ይዘው ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄዱ ለአብርሃምና ለዘሩ በተነገረው የተስፋ ቃል መሠረት የምንጸድቀው ከእምነት በሆነ ጽድቅ እንጂ በሕግ አለመሆኑን ለይቶ በማወቅ አንድና ብቸኛ በሆነው በዚህ እውነት ላይ ብቻ ጸንተው እና እርግጠኞችም ሆነው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው ሕግን ከመጠበቅ በሆነ ጽድቅ ወራሽነት የለም ስለዚህ ጉዳይ አሁንም የገላትያ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል 1ኛ ) ሕግ ምንድነው ? ስንል ፦ ሕግ ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ ይለናል እና ስለዚህ ሕግ የተስፋው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል የተጨመረና መቅሠፍትን የሚያደርግ መተላለፍንም የሚገልጽ ነው ገላትያ 3 ፥ 19 ፤ ሮሜ 3 ፥ 20 ፣ ሮሜ 4 ፥ 15 2ኛ )ሕጉ መቅሰፍትን ያደርጋልና ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለምና የሚል የእግዚአብሔር ቃል ተጽፎልናል እንደገናም ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፦ አትግደል ብሎአልና ተብሎም የተጻፈልን በመሆኑ ከዚህ እውነት አንጻር ሕግን ጠብቆ ያልተሰናከለ ማንም ሰው የለም አናገኝምም ስለዚህ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ሆነ ሮሜ 4 ፥ 15 ፤ የያዕቆብ መልእክት 2 ፥ 10 ፤ ሮሜ 10 ፥ 4 3ኛ ) እንደገናም ይህንኑ ቃል አሁንም ሐዋርያው ይበልጥ ሊያጎለብተው አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና አለን ሮሜ 3 ፥ 19 እና 20 4ኛ ) በመሆኑም ሕግ የሰዎችን ከሕግ በታች መሆን እየተናገረ የዓለሙን አፍ በመዝጋት ዓለሙን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች እንዲቀመጡ ያደረገ ከላይ በገለጽኩት ሃሳብ መሠረትም ይህ ሕግ አሁንም የሰዎችን ኃጢአትና መተላለፍን ሁሉ ያለአንዳች ማቅማማት ሳይደብቅ እያጋለጠ ፣ በትክክለኛ ሁኔታም እየገለጸ የሚያኖርና የሚኖርም ነው ሮሜ 7 ፥ 7 _ 25 5ኛ ) ይህ ብቻ አይደለም ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎልናል ይሁን እንጂ ታድያ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎም የተጻፈ በመሆኑ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን ገላትያ 3 ፥ 10 ፣ 13 5ኛ )ሕያው ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእውነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ይሰጥ ዘንድ መጽሐፍ ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል ይለናል ገላትያ 3 ፥ 21 እና 22 6ኛ ) ከዚህም ሌላ ይሄው ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አይደለም ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላም የተሰጠው ይህ ሕግ አሁንም አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳንና የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ለምን ስንል ርስቱ በሕግ ቢሆንስ እንግዲያስ በተስፋ ቃል አይሆንም፤ በተስፋ ቃል ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰጥቶአል በማለት አብርሃም በእግዚአብሔርም የተረጋገጠ ኪዳንና የተሰጠ የተስፋን ቃል በእርግጠኝነት መያዙን የክፍሉ ሃሳብ በተገቢው መንገድ ይጠቁመናል ገላትያ 3 ፥ 17 እና 18 ለዚህም ነው እንግዲህ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 32 _ 39 ላይ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም ይላልና ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ያለን ስለዚህም የምኩራቡ አለቆች ወንድሞች ሆይ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ብለው በላኩባቸው ጊዜ ጳውሎስ ተነስቶና በእጁ ጠቅሶ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን በሚል ኃይለ ቃል ሊናገረው፣ በጽኑም ሊሰብከው የፈለገው ጥንት ለአባቶች የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው ተብሎ የተነገረለትን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው ታድያ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ዛሬ ዘመን ላይ ላለነው ለእኛ ብቻ የተሰጠ ተስፋና የምስራች ሳይሆን ለእነዚሁ ለእምነት አባቶች ለነአብርሃምም ጭምር አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የማይሻር የተስፋ ቃል ሆኖ የተሰጠ ተስፋና የምሥራች ነው ታድያ ይህንን የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው የእምነት አባቶች እነ አብርሃም የጠበቁትና የተቀበሉት በመሆኑም ዛሬ ላይ እኛ ተፈጥረን ፣ ወይም ተገኝተን ማለት ይቻላል በዚህ የአባቶቻችን ተስፋና የምስራች በሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ፍጹም ልናፍርበት አይገባም ያለዚያ ጌታ የሚሰጠን ለሁላችን የሚሆን ዕረፍትና መዳን የለም ከአባቶች ከነ አብርሃም ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ተስፋና የምስራች ሆኖ ለሁላችን ሲሰጥ እንዲሁም ሲሰበክ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሠጠውምና ተብሎ በቃሉ የተጻፈልን በመሆኑ መበስበስ በሌለበት በአዲስ ትንሣኤ የተነሣ ነውና መበስበስን አላየም ዳዊት ግን በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ካገለገለ በኋላ በአንቀላፋ ጊዜ መበስበስን አይቶአል ይህ እግዚአብሔር ያስነሳው ግን መበስበስን አላየም ይለናል ይህ እግዚአብሔር ያስነሣውና መበስበስንም ያላየው ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ጌታ እግዚአብሔር አስነስቶ ለእኛ ለልጆቹ የምስራችና ተስፋ ነው ብሎ የፈጸመልን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲነሣ ከዳዊት ዘር የተወለደና እንደ ቅድስና መንፈስ ከሙታን መነሣት የተነሳ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠ እንዲሁም የተነሣም ነው ይህንን ነው እንግዲህ ጳውሎስ ወንጌል የሚለን ወንጌል ማለት የልጁ ወንጌል ነውና ሮሜ 1 ፥ 1 _ 5 ፤ ሮሜ 16 ፥ 25 እና 26 የተወደዳችሁ ወገኖች በትምህርቴም ማጠቃለያ ልናገር የምወደው አንድ እውነት እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ተብሎ በእርግጠኝነት የተጻፈልን በመሆኑ እንግዲህ በሙሴ ሕግ ልንጸድቅበት ከማይቻለን ሁሉ ወጥተን በእርሱ በክርስቶስ በኩል የኃጢአትን ሥርየት በማግኘት ያልጸደቅንም ሰዎች መጽደቅ ፣ ያልዳንም ሰዎች እንዲሁ መዳን ይሁንልን ስል በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ መጽሐፉ እንዳንጠራጠር አስረግጦ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ብሎናልና እኔም የመጽሐፉን ቃል ተከትዬ ይህ በክርስቶስ እና በክርስቶስ ብቻ የተገኘ የኃጢአት ሥርየት እንዲሁም መጽደቅ ለሁላችን የታወቀ ይሁን በማለት ይህንኑ የመጽሐፉን ቃል ለእናንተ ለወገኖቼ በእምነትና በሥልጣን አውጃለሁ በመቀጠልም ከእነዚህ ማብራርያዎች ባሻገር ይህ ትምህርት ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው በማለት በሮሜ 9 ፥ 30 የተጠቀሰውን ሃሳብ አንስቶ ጽድቅ በእምነት እንጂ በሕግ አለመሆኑን ሊጠቁመን ወደ ሦስት የሚደርሱ ዓበይት ነጥቦችን በዝርዝር ያስቀምጣል ፦ 1ኛ ) ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው ዕብራውያን 11 ፥ 7 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 6 ፤ ፊልጵስዩስ 3 ፥ 2 _ 10 ፣ 8 እና 9 2ኛ ) እኛም የምንጸድቀው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 27 እና 28 ፤ ገላትያ 2 ፥ 16 ፣ 21 ፤ ገላትያ 5 ፥ 4 3ኛ ) እግዚአብሔርም የሚያጸድቀን በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 28 _ 30 ፤ ሮሜ 3 ፥ 25 እና 26 ፤ ሮሜ 4 ፥ 16 እና 17 ፤ ገላትያ 3 ፥ 8 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እነዚህን ዋና ዋና ሃሳቦች ለተጨማሪ በማብራርያነት አክዬበታለሁ በመሆኑም በዚሁ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ሳያመልጣችሁ በመስማት ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉ በማክበር ላሳስባችሁ እወዳለሁ በነገር ሁሉ ተባረኩ ሰላም ሁኑ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13... የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13 _ 15 ) የክፍሉ ሃሳብ ለምን ይህንን ተናገረ ? ስንል በተጻፈው ቃል መሠረት ከሕግ የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል ወደ ማለት ሃሳብ ሰዎች ሊመጡ የሚችሉ በመሆናቸው ይህንኑ ከሕግ የሆነ ወራሽነትን ይዘው ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄዱ ለአብርሃምና ለዘሩ በተነገረው የተስፋ ቃል መሠረት የምንጸድቀው ከእምነት በሆነ ጽድቅ እንጂ በሕግ አለመሆኑን ለይቶ በማወቅ አንድና ብቸኛ በሆነው በዚህ እውነት ላይ ብቻ ጸንተው እና እርግጠኞችም ሆነው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው ሕግን ከመጠበቅ በሆነ ጽድቅ ወራሽነት የለም ስለዚህ ጉዳይ አሁንም የገላትያ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል 1ኛ ) ሕግ ምንድነው ? ስንል ፦ ሕግ ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ ይለናል እና ስለዚህ ሕግ የተስፋው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል የተጨመረና መቅሠፍትን የሚያደርግ መተላለፍንም የሚገልጽ ነው ገላትያ 3 ፥ 19 ፤ ሮሜ 3 ፥ 20 ፣ ሮሜ 4 ፥ 15 2ኛ )ሕጉ መቅሰፍትን ያደርጋልና ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለምና የሚል የእግዚአብሔር ቃል ተጽፎልናል እንደገናም ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፦ አትግደል ብሎአልና ተብሎም የተጻፈልን በመሆኑ ከዚህ እውነት አንጻር ሕግን ጠብቆ ያልተሰናከለ ማንም ሰው የለም አናገኝምም ስለዚህ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ሆነ ሮሜ 4 ፥ 15 ፤ የያዕቆብ መልእክት 2 ፥ 10 ፤ ሮሜ 10 ፥ 4 3ኛ ) እንደገናም ይህንኑ ቃል አሁንም ሐዋርያው ይበልጥ ሊያጎለብተው አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና አለን ሮሜ 3 ፥ 19 እና 20 4ኛ ) በመሆኑም ሕግ የሰዎችን ከሕግ በታች መሆን እየተናገረ የዓለሙን አፍ በመዝጋት ዓለሙን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች እንዲቀመጡ ያደረገ ከላይ በገለጽኩት ሃሳብ መሠረትም ይህ ሕግ አሁንም የሰዎችን ኃጢአትና መተላለፍን ሁሉ ያለአንዳች ማቅማማት ሳይደብቅ እያጋለጠ ፣ በትክክለኛ ሁኔታም እየገለጸ የሚያኖርና የሚኖርም ነው ሮሜ 7 ፥ 7 _ 25 5ኛ ) ይህ ብቻ አይደለም ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎልናል ይሁን እንጂ ታድያ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎም የተጻፈ በመሆኑ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን ገላትያ 3 ፥ 10 ፣ 13 5ኛ )ሕያው ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእውነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ይሰጥ ዘንድ መጽሐፍ ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል ይለናል ገላትያ 3 ፥ 21 እና 22 6ኛ ) ከዚህም ሌላ ይሄው ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አይደለም ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላም የተሰጠው ይህ ሕግ አሁንም አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳንና የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ለምን ስንል ርስቱ በሕግ ቢሆንስ እንግዲያስ በተስፋ ቃል አይሆንም፤ በተስፋ ቃል ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰጥቶአል በማለት አብርሃም በእግዚአብሔርም የተረጋገጠ ኪዳንና የተሰጠ የተስፋን ቃል በእርግጠኝነት መያዙን የክፍሉ ሃሳብ በተገቢው መንገድ ይጠቁመናል ገላትያ 3 ፥ 17 እና 18 ለዚህም ነው እንግዲህ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 32 _ 39 ላይ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም ይላልና ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ያለን ስለዚህም የምኩራቡ አለቆች ወንድሞች ሆይ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ብለው በላኩባቸው ጊዜ ጳውሎስ ተነስቶና በእጁ ጠቅሶ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን በሚል ኃይለ ቃል ሊናገረው፣ በጽኑም ሊሰብከው የፈለገው ጥንት ለአባቶች የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው ተብሎ የተነገረለትን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው ታድያ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ዛሬ ዘመን ላይ ላለነው ለእኛ ብቻ የተሰጠ ተስፋና የምስራች ሳይሆን ለእነዚሁ ለእምነት አባቶች ለነአብርሃምም ጭምር አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የማይሻር የተስፋ ቃል ሆኖ የተሰጠ ተስፋና የምሥራች ነው ታድያ ይህንን የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው የእምነት አባቶች እነ አብርሃም የጠበቁትና የተቀበሉት በመሆኑም ዛሬ ላይ እኛ ተፈጥረን ፣ ወይም ተገኝተን ማለት ይቻላል በዚህ የአባቶቻችን ተስፋና የምስራች በሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ፍጹም ልናፍርበት አይገባም ያለዚያ ጌታ የሚሰጠን ለሁላችን የሚሆን ዕረፍትና መዳን የለም ከአባቶች ከነ አብርሃም ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ተስፋና የምስራች ሆኖ ለሁላችን ሲሰጥ እንዲሁም ሲሰበክ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሠጠውምና ተብሎ በቃሉ የተጻፈልን በመሆኑ መበስበስ በሌለበት በአዲስ ትንሣኤ የተነሣ ነውና መበስበስን አላየም ዳዊት ግን በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ካገለገለ በኋላ በአንቀላፋ ጊዜ መበስበስን አይቶአል ይህ እግዚአብሔር ያስነሳው ግን መበስበስን አላየም ይለናል ይህ እግዚአብሔር ያስነሣውና መበስበስንም ያላየው ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ጌታ እግዚአብሔር አስነስቶ ለእኛ ለልጆቹ የምስራችና ተስፋ ነው ብሎ የፈጸመልን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲነሣ ከዳዊት ዘር የተወለደና እንደ ቅድስና መንፈስ ከሙታን መነሣት የተነሳ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠ እንዲሁም የተነሣም ነው ይህንን ነው እንግዲህ ጳውሎስ ወንጌል የሚለን ወንጌል ማለት የልጁ ወንጌል ነውና ሮሜ 1 ፥ 1 _ 5 ፤ ሮሜ 16 ፥ 25 እና 26 የተወደዳችሁ ወገኖች በትምህርቴም ማጠቃለያ ልናገር የምወደው አንድ እውነት እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ተብሎ በእርግጠኝነት የተጻፈልን በመሆኑ እንግዲህ በሙሴ ሕግ ልንጸድቅበት ከማይቻለን ሁሉ ወጥተን በእርሱ በክርስቶስ በኩል የኃጢአትን ሥርየት በማግኘት ያልጸደቅንም ሰዎች መጽደቅ ፣ ያልዳንም ሰዎች እንዲሁ መዳን ይሁንልን ስል በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ መጽሐፉ እንዳንጠራጠር አስረግጦ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ብሎናልና እኔም የመጽሐፉን ቃል ተከትዬ ይህ በክርስቶስ እና በክርስቶስ ብቻ የተገኘ የኃጢአት ሥርየት እንዲሁም መጽደቅ ለሁላችን የታወቀ ይሁን በማለት ይህንኑ የመጽሐፉን ቃል ለእናንተ ለወገኖቼ በእምነትና በሥልጣን አውጃለሁ በመቀጠልም ከእነዚህ ማብራርያዎች ባሻገር ይህ ትምህርት ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው በማለት በሮሜ 9 ፥ 30 የተጠቀሰውን ሃሳብ አንስቶ ጽድቅ በእምነት እንጂ በሕግ አለመሆኑን ሊጠቁመን ወደ ሦስት የሚደርሱ ዓበይት ነጥቦችን በዝርዝር ያስቀምጣል ፦ 1ኛ ) ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው ዕብራውያን 11 ፥ 7 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 6 ፤ ፊልጵስዩስ 3 ፥ 2 _ 10 ፣ 8 እና 9 2ኛ ) እኛም የምንጸድቀው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 27 እና 28 ፤ ገላትያ 2 ፥ 16 ፣ 21 ፤ ገላትያ 5 ፥ 4 3ኛ ) እግዚአብሔርም የሚያጸድቀን በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 28 _ 30 ፤ ሮሜ 3 ፥ 25 እና 26 ፤ ሮሜ 4 ፥ 16 እና 17 ፤ ገላትያ 3 ፥ 8 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እነዚህን ዋና ዋና ሃሳቦች ለተጨማሪ በማብራርያነት አክዬበታለሁ በመሆኑም በዚሁ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ሳያመልጣችሁ በመስማት ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉ በማክበር ላሳስባችሁ እወዳለሁ በነገር ሁሉ ተባረኩ ሰላም ሁኑ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Sunday 21 February 2016

የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13 _ 15 ) የክፍሉ ሃሳብ ለምን ይህንን ተናገረ ? ስንል በተጻፈው ቃል መሠረት ከሕግ የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል ወደ ማለት ሃሳብ ሰዎች ሊመጡ የሚችሉ በመሆናቸው ይህንኑ ከሕግ የሆነ ወራሽነትን ይዘው ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄዱ ለአብርሃምና ለዘሩ በተነገረው የተስፋ ቃል መሠረት የምንጸድቀው ከእምነት በሆነ ጽድቅ እንጂ በሕግ አለመሆኑን ለይቶ በማወቅ አንድና ብቸኛ በሆነው በዚህ እውነት ላይ ብቻ ጸንተው እና እርግጠኞችም ሆነው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው ሕግን ከመጠበቅ በሆነ ጽድቅ ወራሽነት የለም ስለዚህ ጉዳይ አሁንም የገላትያ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል 1ኛ ) ሕግ ምንድነው ? ስንል ፦ ሕግ ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ ይለናል እና ስለዚህ ሕግ የተስፋው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል የተጨመረና መቅሠፍትን የሚያደርግ መተላለፍንም የሚገልጽ ነው ገላትያ 3 ፥ 19 ፤ ሮሜ 3 ፥ 20 ፣ ሮሜ 4 ፥ 15 2ኛ )ሕጉ መቅሰፍትን ያደርጋልና ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለምና የሚል የእግዚአብሔር ቃል ተጽፎልናል እንደገናም ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፦ አትግደል ብሎአልና ተብሎም የተጻፈልን በመሆኑ ከዚህ እውነት አንጻር ሕግን ጠብቆ ያልተሰናከለ ማንም ሰው የለም አናገኝምም ስለዚህ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ሆነ ሮሜ 4 ፥ 15 ፤ የያዕቆብ መልእክት 2 ፥ 10 ፤ ሮሜ 10 ፥ 4 3ኛ ) እንደገናም ይህንኑ ቃል አሁንም ሐዋርያው ይበልጥ ሊያጎለብተው አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና አለን ሮሜ 3 ፥ 19 እና 20 4ኛ ) በመሆኑም ሕግ የሰዎችን ከሕግ በታች መሆን እየተናገረ የዓለሙን አፍ በመዝጋት ዓለሙን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች እንዲቀመጡ ያደረገ ከላይ በገለጽኩት ሃሳብ መሠረትም ይህ ሕግ አሁንም የሰዎችን ኃጢአትና መተላለፍን ሁሉ ያለአንዳች ማቅማማት ሳይደብቅ እያጋለጠ ፣ በትክክለኛ ሁኔታም እየገለጸ የሚያኖርና የሚኖርም ነው ሮሜ 7 ፥ 7 _ 25 5ኛ ) ይህ ብቻ አይደለም ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎልናል ይሁን እንጂ ታድያ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎም የተጻፈ በመሆኑ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን ገላትያ 3 ፥ 10 ፣ 13 5ኛ )ሕያው ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእውነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ይሰጥ ዘንድ መጽሐፍ ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል ይለናል ገላትያ 3 ፥ 21 እና 22 6ኛ ) ከዚህም ሌላ ይሄው ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አይደለም ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላም የተሰጠው ይህ ሕግ አሁንም አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳንና የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ለምን ስንል ርስቱ በሕግ ቢሆንስ እንግዲያስ በተስፋ ቃል አይሆንም፤ በተስፋ ቃል ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰጥቶአል በማለት አብርሃም በእግዚአብሔርም የተረጋገጠ ኪዳንና የተሰጠ የተስፋን ቃል በእርግጠኝነት መያዙን የክፍሉ ሃሳብ በተገቢው መንገድ ይጠቁመናል ገላትያ 3 ፥ 17 እና 18 ለዚህም ነው እንግዲህ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 32 _ 39 ላይ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም ይላልና ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ያለን ስለዚህም የምኩራቡ አለቆች ወንድሞች ሆይ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ብለው በላኩባቸው ጊዜ ጳውሎስ ተነስቶና በእጁ ጠቅሶ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን በሚል ኃይለ ቃል ሊናገረው፣ በጽኑም ሊሰብከው የፈለገው ጥንት ለአባቶች የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው ተብሎ የተነገረለትን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው ታድያ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ዛሬ ዘመን ላይ ላለነው ለእኛ ብቻ የተሰጠ ተስፋና የምስራች ሳይሆን ለእነዚሁ ለእምነት አባቶች ለነአብርሃምም ጭምር አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የማይሻር የተስፋ ቃል ሆኖ የተሰጠ ተስፋና የምሥራች ነው ታድያ ይህንን የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው የእምነት አባቶች እነ አብርሃም የጠበቁትና የተቀበሉት በመሆኑም ዛሬ ላይ እኛ ተፈጥረን ፣ ወይም ተገኝተን ማለት ይቻላል በዚህ የአባቶቻችን ተስፋና የምስራች በሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ፍጹም ልናፍርበት አይገባም ያለዚያ ጌታ የሚሰጠን ለሁላችን የሚሆን ዕረፍትና መዳን የለም ከአባቶች ከነ አብርሃም ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ተስፋና የምስራች ሆኖ ለሁላችን ሲሰጥ እንዲሁም ሲሰበክ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሠጠውምና ተብሎ በቃሉ የተጻፈልን በመሆኑ መበስበስ በሌለበት በአዲስ ትንሣኤ የተነሣ ነውና መበስበስን አላየም ዳዊት ግን በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ካገለገለ በኋላ በአንቀላፋ ጊዜ መበስበስን አይቶአል ይህ እግዚአብሔር ያስነሳው ግን መበስበስን አላየም ይለናል ይህ እግዚአብሔር ያስነሣውና መበስበስንም ያላየው ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ጌታ እግዚአብሔር አስነስቶ ለእኛ ለልጆቹ የምስራችና ተስፋ ነው ብሎ የፈጸመልን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲነሣ ከዳዊት ዘር የተወለደና እንደ ቅድስና መንፈስ ከሙታን መነሣት የተነሳ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠ እንዲሁም የተነሣም ነው ይህንን ነው እንግዲህ ጳውሎስ ወንጌል የሚለን ወንጌል ማለት የልጁ ወንጌል ነውና ሮሜ 1 ፥ 1 _ 5 ፤ ሮሜ 16 ፥ 25 እና 26 የተወደዳችሁ ወገኖች በትምህርቴም ማጠቃለያ ልናገር የምወደው አንድ እውነት እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ተብሎ በእርግጠኝነት የተጻፈልን በመሆኑ እንግዲህ በሙሴ ሕግ ልንጸድቅበት ከማይቻለን ሁሉ ወጥተን በእርሱ በክርስቶስ በኩል የኃጢአትን ሥርየት በማግኘት ያልጸደቅንም ሰዎች መጽደቅ ፣ ያልዳንም ሰዎች እንዲሁ መዳን ይሁንልን ስል በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ መጽሐፉ እንዳንጠራጠር አስረግጦ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ብሎናልና እኔም የመጽሐፉን ቃል ተከትዬ ይህ በክርስቶስ እና በክርስቶስ ብቻ የተገኘ የኃጢአት ሥርየት እንዲሁም መጽደቅ ለሁላችን የታወቀ ይሁን በማለት ይህንኑ የመጽሐፉን ቃል ለእናንተ ለወገኖቼ በእምነትና በሥልጣን አውጃለሁ በመቀጠልም ከእነዚህ ማብራርያዎች ባሻገር ይህ ትምህርት ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው በማለት በሮሜ 9 ፥ 30 የተጠቀሰውን ሃሳብ አንስቶ ጽድቅ በእምነት እንጂ በሕግ አለመሆኑን ሊጠቁመን ወደ ሦስት የሚደርሱ ዓበይት ነጥቦችን በዝርዝር ያስቀምጣል ፦ 1ኛ ) ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው ዕብራውያን 11 ፥ 7 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 6 ፤ ፊልጵስዩስ 3 ፥ 2 _ 10 ፣ 8 እና 9 2ኛ ) እኛም የምንጸድቀው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 27 እና 28 ፤ ገላትያ 2 ፥ 16 ፣ 21 ፤ ገላትያ 5 ፥ 4 3ኛ ) እግዚአብሔርም የሚያጸድቀን በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 28 _ 30 ፤ ሮሜ 3 ፥ 25 እና 26 ፤ ሮሜ 4 ፥ 16 እና 17 ፤ ገላትያ 3 ፥ 8 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እነዚህን ዋና ዋና ሃሳቦች ለተጨማሪ በማብራርያነት አክዬበታለሁ በመሆኑም በዚሁ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ሳያመልጣችሁ በመስማት ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉ በማክበር ላሳስባችሁ እወዳለሁ በነገር ሁሉ ተባረኩ ሰላም ሁኑ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

( ትምህርት ሦስት ) የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደ...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም ( ሮሜ 4 ፥ 13 _ 15 ) የክፍሉ ሃሳብ ለምን ይህንን ተናገረ ? ስንል በተጻፈው ቃል መሠረት ከሕግ የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል ወደ ማለት ሃሳብ ሰዎች ሊመጡ የሚችሉ በመሆናቸው ይህንኑ ከሕግ የሆነ ወራሽነትን ይዘው ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄዱ ለአብርሃምና ለዘሩ በተነገረው የተስፋ ቃል መሠረት የምንጸድቀው ከእምነት በሆነ ጽድቅ እንጂ በሕግ አለመሆኑን ለይቶ በማወቅ አንድና ብቸኛ በሆነው በዚህ እውነት ላይ ብቻ ጸንተው እና እርግጠኞችም ሆነው እንዲቆሙ ለማድረግ ነው ሕግን ከመጠበቅ በሆነ ጽድቅ ወራሽነት የለም ስለዚህ ጉዳይ አሁንም የገላትያ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል 1ኛ ) ሕግ ምንድነው ? ስንል ፦ ሕግ ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ ይለናል እና ስለዚህ ሕግ የተስፋው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል የተጨመረና መቅሠፍትን የሚያደርግ መተላለፍንም የሚገልጽ ነው ገላትያ 3 ፥ 19 ፤ ሮሜ 3 ፥ 20 ፣ ሮሜ 4 ፥ 15 2ኛ )ሕጉ መቅሰፍትን ያደርጋልና ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለምና የሚል የእግዚአብሔር ቃል ተጽፎልናል እንደገናም ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፦ አትግደል ብሎአልና ተብሎም የተጻፈልን በመሆኑ ከዚህ እውነት አንጻር ሕግን ጠብቆ ያልተሰናከለ ማንም ሰው የለም አናገኝምም ስለዚህ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ሆነ ሮሜ 4 ፥ 15 ፤ የያዕቆብ መልእክት 2 ፥ 10 ፤ ሮሜ 10 ፥ 4 3ኛ ) እንደገናም ይህንኑ ቃል አሁንም ሐዋርያው ይበልጥ ሊያጎለብተው አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና አለን ሮሜ 3 ፥ 19 እና 20 4ኛ ) በመሆኑም ሕግ የሰዎችን ከሕግ በታች መሆን እየተናገረ የዓለሙን አፍ በመዝጋት ዓለሙን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች እንዲቀመጡ ያደረገ ከላይ በገለጽኩት ሃሳብ መሠረትም ይህ ሕግ አሁንም የሰዎችን ኃጢአትና መተላለፍን ሁሉ ያለአንዳች ማቅማማት ሳይደብቅ እያጋለጠ ፣ በትክክለኛ ሁኔታም እየገለጸ የሚያኖርና የሚኖርም ነው ሮሜ 7 ፥ 7 _ 25 5ኛ ) ይህ ብቻ አይደለም ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎልናል ይሁን እንጂ ታድያ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎም የተጻፈ በመሆኑ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን ገላትያ 3 ፥ 10 ፣ 13 5ኛ )ሕያው ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእውነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን የሆነው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ይሰጥ ዘንድ መጽሐፍ ከኃጢአት በታች ሁሉን ዘግቶታል ይለናል ገላትያ 3 ፥ 21 እና 22 6ኛ ) ከዚህም ሌላ ይሄው ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አይደለም ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላም የተሰጠው ይህ ሕግ አሁንም አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳንና የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ለምን ስንል ርስቱ በሕግ ቢሆንስ እንግዲያስ በተስፋ ቃል አይሆንም፤ በተስፋ ቃል ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰጥቶአል በማለት አብርሃም በእግዚአብሔርም የተረጋገጠ ኪዳንና የተሰጠ የተስፋን ቃል በእርግጠኝነት መያዙን የክፍሉ ሃሳብ በተገቢው መንገድ ይጠቁመናል ገላትያ 3 ፥ 17 እና 18 ለዚህም ነው እንግዲህ በሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 32 _ 39 ላይ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም ይላልና ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ያለን ስለዚህም የምኩራቡ አለቆች ወንድሞች ሆይ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ብለው በላኩባቸው ጊዜ ጳውሎስ ተነስቶና በእጁ ጠቅሶ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን በሚል ኃይለ ቃል ሊናገረው፣ በጽኑም ሊሰብከው የፈለገው ጥንት ለአባቶች የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው ተብሎ የተነገረለትን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው ታድያ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ዛሬ ዘመን ላይ ላለነው ለእኛ ብቻ የተሰጠ ተስፋና የምስራች ሳይሆን ለእነዚሁ ለእምነት አባቶች ለነአብርሃምም ጭምር አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የማይሻር የተስፋ ቃል ሆኖ የተሰጠ ተስፋና የምሥራች ነው ታድያ ይህንን የተሰጠ ተስፋና የምስራች ነው የእምነት አባቶች እነ አብርሃም የጠበቁትና የተቀበሉት በመሆኑም ዛሬ ላይ እኛ ተፈጥረን ፣ ወይም ተገኝተን ማለት ይቻላል በዚህ የአባቶቻችን ተስፋና የምስራች በሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ፍጹም ልናፍርበት አይገባም ያለዚያ ጌታ የሚሰጠን ለሁላችን የሚሆን ዕረፍትና መዳን የለም ከአባቶች ከነ አብርሃም ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ተስፋና የምስራች ሆኖ ለሁላችን ሲሰጥ እንዲሁም ሲሰበክ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሠጠውምና ተብሎ በቃሉ የተጻፈልን በመሆኑ መበስበስ በሌለበት በአዲስ ትንሣኤ የተነሣ ነውና መበስበስን አላየም ዳዊት ግን በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ካገለገለ በኋላ በአንቀላፋ ጊዜ መበስበስን አይቶአል ይህ እግዚአብሔር ያስነሳው ግን መበስበስን አላየም ይለናል ይህ እግዚአብሔር ያስነሣውና መበስበስንም ያላየው ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ጌታ እግዚአብሔር አስነስቶ ለእኛ ለልጆቹ የምስራችና ተስፋ ነው ብሎ የፈጸመልን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲነሣ ከዳዊት ዘር የተወለደና እንደ ቅድስና መንፈስ ከሙታን መነሣት የተነሳ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠ እንዲሁም የተነሣም ነው ይህንን ነው እንግዲህ ጳውሎስ ወንጌል የሚለን ወንጌል ማለት የልጁ ወንጌል ነውና ሮሜ 1 ፥ 1 _ 5 ፤ ሮሜ 16 ፥ 25 እና 26 የተወደዳችሁ ወገኖች በትምህርቴም ማጠቃለያ ልናገር የምወደው አንድ እውነት እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ተብሎ በእርግጠኝነት የተጻፈልን በመሆኑ እንግዲህ በሙሴ ሕግ ልንጸድቅበት ከማይቻለን ሁሉ ወጥተን በእርሱ በክርስቶስ በኩል የኃጢአትን ሥርየት በማግኘት ያልጸደቅንም ሰዎች መጽደቅ ፣ ያልዳንም ሰዎች እንዲሁ መዳን ይሁንልን ስል በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ መጽሐፉ እንዳንጠራጠር አስረግጦ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ብሎናልና እኔም የመጽሐፉን ቃል ተከትዬ ይህ በክርስቶስ እና በክርስቶስ ብቻ የተገኘ የኃጢአት ሥርየት እንዲሁም መጽደቅ ለሁላችን የታወቀ ይሁን በማለት ይህንኑ የመጽሐፉን ቃል ለእናንተ ለወገኖቼ በእምነትና በሥልጣን አውጃለሁ በመቀጠልም ከእነዚህ ማብራርያዎች ባሻገር ይህ ትምህርት ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው በማለት በሮሜ 9 ፥ 30 የተጠቀሰውን ሃሳብ አንስቶ ጽድቅ በእምነት እንጂ በሕግ አለመሆኑን ሊጠቁመን ወደ ሦስት የሚደርሱ ዓበይት ነጥቦችን በዝርዝር ያስቀምጣል ፦ 1ኛ ) ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ነው ዕብራውያን 11 ፥ 7 ፤ ዘፍጥረት 15 ፥ 6 ፤ ፊልጵስዩስ 3 ፥ 2 _ 10 ፣ 8 እና 9 2ኛ ) እኛም የምንጸድቀው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 27 እና 28 ፤ ገላትያ 2 ፥ 16 ፣ 21 ፤ ገላትያ 5 ፥ 4 3ኛ ) እግዚአብሔርም የሚያጸድቀን በእምነት ነው ሮሜ 3 ፥ 28 _ 30 ፤ ሮሜ 3 ፥ 25 እና 26 ፤ ሮሜ 4 ፥ 16 እና 17 ፤ ገላትያ 3 ፥ 8 የተወደዳችሁ ቅዱሳን በቪዲዮ የተለቀቀው ትምህርት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እነዚህን ዋና ዋና ሃሳቦች ለተጨማሪ በማብራርያነት አክዬበታለሁ በመሆኑም በዚሁ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ሳያመልጣችሁ በመስማት ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉ በማክበር ላሳስባችሁ እወዳለሁ በነገር ሁሉ ተባረኩ ሰላም ሁኑ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Thursday 18 February 2016

( ትምህርት ሦስት ) የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 )...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው እኛም ወንድሞች ሆይ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 ) ይህ ትምህርት በውስጡ ፦ 1ኛ ) ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጅ ሆኖ የተወለደበትን ምስጢር ወደ ስድስት ያህል በሚደርሱ ነጥቦች በዝርዝር ያቀርባል 2ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች የሥጋ ልጆች አይደሉምና የአብርሃም ልጆች የተባሉት በተስፋው ቃል የተወለዱ ልጆች መሆናቸውን በሰፊው ከማስረጃ ጋር ያትታል ገላትያ 3 ፥ 16 ፣ ገላትያ 4 : 23 ፣ ሮሜ 9 ፥ 6 _ 9 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 3 ፥ 8 _ 11 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 8 : 11 – 13 ፣ ሮሜ 8 ፥ 14 3ኛ ) የተስፋው ልጅ ጊዜው ሲደርስ የተወለደ ነው ሮሜ 9 ፥ 9 ፣ ገላትያ 4 ፥ 23 ፣ ዘፍጥረት 21 ፥ 2 ፣ ያዕቆብ 1 ፥ 18 ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 4ኛ ) የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ብለናልና ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረለት ከመገረዙ በፊት በመሆኑ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙ ጽድቅ ይቆጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው ሮሜ 4 ፥ 9 _ 12 5ኛ ) በዚህም ምክንያት አሕዛብ ከአይሁድ ጋር በክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት አንድ አካል የሚሆኑበትን በዚሁም የተስፋ ቃል ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ አብረው ተካፋይ የሚሆኑበትን ምስጢር እናይበታለን ኤፌሶን 3 ፥ 5 _ 6 ፣ ኤፌሶን 4 ፥ 4 _ 6 ፣ ሮሜ 16 ፥ 26 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ትምህርቱ በእነዚህ ዋና ዋና ነጥቦችና አርዕስተ ጉዳዮች የተጠቃለለ ነው ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል በቪዲዮ የሚለቀቁትን ተከታታይና ቀጣይነት ያላቸውን ትምህርቶች እንደሚገባ ተከታትላችሁ በመጠቀም ለሌሎችም መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር እንድታደርጉት በታላቅ አክብሮት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 17 February 2016

( ትምህርት ሁለት ) የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 )...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው እኛም ወንድሞች ሆይ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 ) ይህ ትምህርት በውስጡ ፦ 1ኛ ) ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጅ ሆኖ የተወለደበትን ምስጢር ወደ ስድስት ያህል በሚደርሱ ነጥቦች በዝርዝር ያቀርባል 2ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች የሥጋ ልጆች አይደሉምና የአብርሃም ልጆች የተባሉት በተስፋው ቃል የተወለዱ ልጆች መሆናቸውን በሰፊው ከማስረጃ ጋር ያትታል ገላትያ 3 ፥ 16 ፣ ገላትያ 4 : 23 ፣ ሮሜ 9 ፥ 6 _ 9 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 3 ፥ 8 _ 11 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 8 : 11 – 13 ፣ ሮሜ 8 ፥ 14 3ኛ ) የተስፋው ልጅ ጊዜው ሲደርስ የተወለደ ነው ሮሜ 9 ፥ 9 ፣ ገላትያ 4 ፥ 23 ፣ ዘፍጥረት 21 ፥ 2 ፣ ያዕቆብ 1 ፥ 18 ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 4ኛ ) የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ብለናልና ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረለት ከመገረዙ በፊት በመሆኑ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙ ጽድቅ ይቆጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው ሮሜ 4 ፥ 9 _ 12 5ኛ ) በዚህም ምክንያት አሕዛብ ከአይሁድ ጋር በክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት አንድ አካል የሚሆኑበትን በዚሁም የተስፋ ቃል ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ አብረው ተካፋይ የሚሆኑበትን ምስጢር እናይበታለን ኤፌሶን 3 ፥ 5 _ 6 ፣ ኤፌሶን 4 ፥ 4 _ 6 ፣ ሮሜ 16 ፥ 26 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ትምህርቱ በእነዚህ ዋና ዋና ነጥቦችና አርዕስተ ጉዳዮች የተጠቃለለ ነው ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል በቪዲዮ የሚለቀቁትን ተከታታይና ቀጣይነት ያላቸውን ትምህርቶች እንደሚገባ ተከታትላችሁ በመጠቀም ለሌሎችም መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር እንድታደርጉት በታላቅ አክብሮት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው እኛም ወንድሞች ሆይ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 ) ይህ ትምህርት በውስጡ ፦ 1ኛ ) ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጅ ሆኖ የተወለደበትን ምስጢር ወደ ስድስት ያህል በሚደርሱ ነጥቦች በዝርዝር ያቀርባል 2ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች የሥጋ ልጆች አይደሉምና የአብርሃም ልጆች የተባሉት በተስፋው ቃል የተወለዱ ልጆች መሆናቸውን በሰፊው ከማስረጃ ጋር ያትታል ገላትያ 3 ፥ 16 ፣ ገላትያ 4 : 23 ፣ ሮሜ 9 ፥ 6 _ 9 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 3 ፥ 8 _ 11 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 8 : 11 – 13 ፣ ሮሜ 8 ፥ 14 3ኛ ) የተስፋው ልጅ ጊዜው ሲደርስ የተወለደ ነው ሮሜ 9 ፥ 9 ፣ ገላትያ 4 ፥ 23 ፣ ዘፍጥረት 21 ፥ 2 ፣ ያዕቆብ 1 ፥ 18 ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 4ኛ ) የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ብለናልና ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረለት ከመገረዙ በፊት በመሆኑ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙ ጽድቅ ይቆጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው ሮሜ 4 ፥ 9 _ 12 5ኛ ) በዚህም ምክንያት አሕዛብ ከአይሁድ ጋር በክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት አንድ አካል የሚሆኑበትን በዚሁም የተስፋ ቃል ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ አብረው ተካፋይ የሚሆኑበትን ምስጢር እናይበታለን ኤፌሶን 3 ፥ 5 _ 6 ፣ ኤፌሶን 4 ፥ 4 _ 6 ፣ ሮሜ 16 ፥ 26 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ትምህርቱ በእነዚህ ዋና ዋና ነጥቦችና አርዕስተ ጉዳዮች የተጠቃለለ ነው ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል በቪዲዮ የሚለቀቁትን ተከታታይና ቀጣይነት ያላቸውን ትምህርቶች እንደሚገባ ተከታትላችሁ በመጠቀም ለሌሎችም መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር እንድታደርጉት በታላቅ አክብሮት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29...

የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 )

Friday 12 February 2016

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: ክፍል ሁለት የመልዕክት ርዕስ ፦ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ...

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry: ክፍል ሁለት የመልዕክት ርዕስ ፦ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ...: 2 Samuel 13 Amnon and Tamar   Juda and Jesus   ክፍል ሁለት የመልዕክት ርዕስ ፦ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ እርሱም ...

ክፍል ሁለት የመልዕክት ርዕስ ፦ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ

2 Samuel 13 Amnon and Tamar
 Juda and Jesus



 ክፍል ሁለት


የመልዕክት ርዕስ ፦

የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ



እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ   የዮሐንስ ወንጌል 13 30





በክፍል አንድ መልዕክቴ ላይ የደሊላን የሥራ ጅማሬ ያላወቀው ሶምሶን የወደደችውና ከእርሱም ጋር የሆነች መስሎት እንዴት ባለ ውድቀት ውስጥ ተላልፎ እንደተሰጠ በሰፊው ተማምረንበታል ደሊላ ግን ሥራዋን አንድ ብላ የጀመረችው ኃይሉ ከእርሱ በሄደ ጊዜ ስለሆነ ልታዋርደውም ጀመረች እያለ የክፍሉ ሃሳብ ይናገራልና በእነዚህና በመሳሰሉት ዙርያ ነበር በስፋት የተነጋገርነው የክፍል ሁለት መልዕክቴም ከዚሁ የቀጠለ ነው በክፍል ሁለት መልዕክት የምናየው የተቀባው መሲሃችን ኢየሱስን ነው ጌታችን ኢየሱስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን በትክክል የሚያውቅ ነው በመሆኑም ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው ይለናል የዮሐንስ ወንጌል 13 1 ይሁን እንጂ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር በምክንያት ያልሆነና እንዲሁ የሆነ ፍቅር በመሆኑ ከማንም ጋር ልናነጻጽረውም ሆነ ልናወዳድረው አንችልም እንደገናም በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ገደብ የሌለውና እስከመጨረሻውም የሆነ ፍቅር ነው ለዚህም ነው ሐዋርያውና ወንድማችን የሆነው ጳውሎስ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ያለን ኤፌሶን 3 16 _ 19 ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንወቅህ ብንለው እንኳ አውቀነው የማንጨርሰው ፍቅር ልናውቀውም የማንችለውና ከመታወቅም የሚያልፍ ፍቅር ነው የፍቅሩ ልክ ደግሞ  ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር የሙላቱን መጨረሻ  የሚገልጽ ነው ታድያ ይሄ ደቀመዛሙርቱን እስከመጨረሻው የወደደ ከክርስቶስ የወጣ ፍቅር ዝም ብሎና ተራ በሆነ ወረታዊ የመንደር ፍቅር ዓይነት  እውር ሆኖ  አበድኩልህ ከነፍኩልህ ስለዚህ ምኔን ልስጥህ የሚል ሰዋዊ ተቀያያሪ ሶምሶናዊም ሆነ አምኖናዊ ዓይነት ፍቅር አይደለም 2 ሳሙኤል 13 1 _ 15 መሣፍንት 14 1 _ 4 10 _ 20 መሣፍንት 16 1 _ 22 ይሄ ፍቅር እስከመጨረሻው የወደደና የሚወድ የክርስቶስ ፍቅር ሲሆን ነፍስን እስከመስጠት ድረስ የወደደም ፍቅር ነው የዮሐንስ ወንጌል 15 13 በዚያው መጠን ደግሞ አሳልፎ የሚሰጠውንና የሚክደውንም ጭምር የሚያውቅ  ነው የዮሐንስ ወንጌል 13 11 36 _ 38 ወገኖቼ ታድያ ይህ የክርስቶስ ፍቅር ምንም እንኳ እስከመጨረሻው የሚወድ ፍቅር እና  ነፍስንም እስከመስጠት ድረስ የወደደ ፍቅር ቢሆንም ማየት   ማጣራትና መለየትም የሚችል ፍቅር በመሆኑ እስከመጨረሻው ይውደድ እንጂ ሁሉንም አይቶ አጣርቶና ለይቶ ያውቃል ይህ ማለት ደግሞ የሚሸጠውንም ሆነ የሚክደውን ለይቶ ያውቃል ማለቴ ነው ለእኛም እንዲህ ሊሆንልን ይገባል የተወደዳችሁ ቅዱሳን ዛሬ በዘመናችን መንፈሳዊ በሚመስል እህታዊና ወንድማዊ የፍቅር የአገልግሎት የአብሮነትና የመሳሰሉት ግንኙነቶች  ጀርባ አስተውለን አጢነንና ተጠንቅቀንም ጭምር ካልተመላለስን  ወዳልተፈለገ የግንኙነት መስመር ውስጥ በመግባት የጌታን ስም እስከማሰደብ ልንደርስ እንችላለን ግንኙነቶች ሁሉ መንፈሳዊ ስለሆኑና መንፈሳዊም ግንኙነቶች ናቸው ስለተባሉ ሙሉ የሆነ አመኔታን ሰጥተን መልካምና ጥሩ ናቸው ልንል አንችልም ቅድስናን ንጽሕናን የተሞሉ ፍርሃተ እግዚአብሔርንም ገንዘብ ያደረጉ  ግንኙነቶች ካልሆኑ ፍጻሜያቸው መንፈሳዊና ክርስቶሳዊ ፍቅር መሆኑ ቀርቶ ይሁዳዊ ፣ ደሊላዊና አምኖናዊ  ፍቅር ይሆኑና  የአምላካችንን ስም የሚያሰድቡ ብቻ ሳይሆኑ የክርስቶስ  ቤተክርስቲያንን ሳይቀር አንገት የሚያስደፉ ይሆናሉ ስለዚህ በግንኙነቶቻችን ዙርያ በብዙ ልናስብበትና ጥንቃቄም ልናደርግ ይገባል ግንኙነቶቻችንንም እንደ እግዚአብሔር ቃል በሆነ የግንኙነት መንገድ ልናስኬደው ፣ ልናስተካክለውም ያስፈልጋል መጽሐፋችን ለርኩሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና ነው የሚለን 1 ተሰሎንቄ 4 3 _ 8 ቅድስና ዋነኛውና ቀዳሚው የእግዚአብሔር ጥሪ ፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ ነው ስለዚህ  ደግሞ እኛም ልንፈልገው ይገባል ያለእርሱ እግዚአብሔርን ማየት አንችልምና ዕብራውያን 12 14 ቅድስና ከሌለ  አገልግሎት አብሮነት፣ ኅብረት ግንኙነትም ሆነ መሰባሰብ ሌላም ሌላም መንፈሳዊ ተግባሮችን  ያካተቱ ናቸው የምንላቸው ነገሮች ሁሉ የሉም ስለዚህ ቅድስና በሕይወታችን ቀዳሚውን ቦታ ሊይዝ ይገባል እንደገናም በዕብራውያን 10 23 _ 25 ላይ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ይለናል ወገኖቼ የተስፋውን  ምስክርነት የሚጠብቅ ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የተነቃቃ ነው መሰባሰቡን አይተውም ይመካከራል ይተያያል ቀን ሲቀርብ እያየም ዝም ብሎና እጁን አጣጥፎ በግዴለሽነት አይቀመጥም የሃላፊነቱን ድርሻም ለመወጣት አብልጦ ይህንን ያደርጋል ታድያ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በመልካም ሁኔታ በሕይወታችን እንዲካሄዱና እንዲጠናቀቁ የሚያስችል የተስፋን ምስክርነት መጠበቅ ነው ጌታ እግዚአብሔርም የተስፋን ቃል የሰጠና የታመነ ስለሆነ ከእኛ የተስፋን ምስክርነት መጠበቃችንን በብዙ ይፈልገዋል የተስፋን ምስክርነት መጠበቅ ከሌለ ግን እግዚአብሔር የሰጠው የተስፋ ቃል ቢኖርም  ለእኛ ግን እግዚአብሔር  ሰጠን የምንለው የተስፋ ቃል አይኖረንም ፣ ለፍቅርም ሆነ ለመልካም ሥራ መነቃቃት ፣ መሰባሰብ መመካከር ፣ መተያየት የሚባሉ ነገሮች  ሁሉ አይታሰቡም   የተስፋችንን ምስክርነት መጠበቅ  እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለማከናወንና ለመፈጸም ዋነኛ ነገር ነው ቅዱሳን ወገኖቼ እንግዲህ በምልልሳችንም ዙርያ እንዴት እንድንመላለስ በጥንቃቄ መጠበቅ አለብን  ኤፌሶን 5 15 _ 20 ዘመኑም ይህንን የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር እውነት ለብሰን እንድንራመድ የሚገፋን   ስለሆነም ለእነዚህ ከእግዚአብሔር ለተሰጡን መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች  መፈጸም ራሳችንን  በዚሁ በእግዚአብሔር ቃል ማዘጋጀትና ማሳደግ አለብን ኢየሱስ ጌታችን እስከመጨረሻው በሚወድ ፍቅር ውስጥ ቢሆንም የሚሸጠውንም ሆነ የሚክደውን ያውቃልና  ይሁዳን እንዲህ አለው እንግዲህ የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦ ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥ ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ  ይለናል ስለዚህ ኢየሱስ ይሁዳን ያወቀው ገና ሌሊት ሳለ ቁራሽ ሲሰጠው ነው ታድያ ጌታችን ኢየሱስ ይሁዳን ሊያውቀው ሌሊቱ አልነጋበትም ወይም አልረፈደበትም ሶምሶን ደሊላን ሊያውቃት ጊዜው ረፍዶበት ነበር ኢየሱስ ግን ይሁዳን ያወቀው ገና ሌሊት ሳለና ቁራሽ ሲሰጠው ነው ይሁዳም ከዚያ በኋላ ከኢየሱስ ጋር ብዙ መጓዝ አልቻለም ለዚህም ነው እንግዲህ እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ የሚለን ዮሐንስ 13 21 _ 30  ደሊላ ግን ከሶምሶን ጋር እውነት በሚመስል የሽንገላ ፍቅር  በብዙ ተጉዛለች አብራም በልታለች ጠጥታለች መብላት መጠጣት ብቻ አይደለም ከዚህም አልፋ አጠጥታና ጠጥታ አስክራለች ተሳክራለች  ጸጉርም አስላጭታ የዚሁ የሶምሶንን ጸጋ አስወስዳለች ልታዋርደውም ጀምራና ጨርሳ  በፍልስጥኤማውያን በኩል የተሰጣትን ተልዕኮ በሶምሶን ላይ  ሙሉ  ለሙሉ አሳክታለች ለይሁዳ ግን ይሄ ሁሉ አልሆነም ይሁዳ የታወቀበት ገና በሌሊቱ ቁራሽ ከተቀበለ በኋላ ስለነበረ በዚያው ሌሊት ይሁዳ ወጣ ስለዚህም  ኢየሱስ እንዲህ አለ አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ከበረ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል ወዲያውም ያከብረዋል አለ  እንግዲህ ይህ ይሁዳ ቁራሽ ተቀብሎ የወጣበት ሌሊት ለኢየሱስ የመክበር ሌሊት ነበር እንደገናም ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን አባቱ እግዚአብሔርም ሳይቀር የከበረበት ሌሊት ነበር ይሁዳ ማንም ሳያውቅብኝ በሚደብቀኝ ሌሊት ውስጥ ሆኜ ኢየሱስን አሳልፌ አሰጣለሁ ያለበት ሌሊት ለኢየሱስም ሆነ ለአባቱ ለእግዚአብሔር የመክበር ሌሊት ሆነ ታድያ ሌሊቱ ሌሊት ሆኖ የቀረው ለይሁዳ ነው ለኢየሱስ ግን ጨለማ በእርሱ ዘንድ ከቶ የለምና ሌሊቱ ሌሊት ቢሆንም ኢየሱስ  ከአባቱ ጋር ሆኖ  መክበሩን ያወቀበት   ያረጋገጠበትም ሌሊት ሆኖለታል   1 ዮሐንስ 1 ታድያ ይሄ ሁሉ የይሁዳ ሁኔታ ለደቀመዛሙርቱ ግልጽ ሳይሆን ቀርቶ ግር እንዲላቸው የሆነበት  ጉዳይ ቢሆንም  ለኢየሱስ ግን የታወቀና የተረጋገጠ የመክበርያ ጊዜ ነበረ ወገኖቼ ይህ ነው እንግዲህ የሥራን ጅማሬ ማውቅ የይሁዳ የሥራ ጅማሬ ሳይውል ሳያድር በዚያው ሌሊት በራሱ በኢየሱስ የታወቀ ሆኖ ነበረ ከጌታችን ከኢየሱስ ሊሰወር የሚችል አንዳች ነገር የለምና እንደውም ኢየሱስ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር ብሎ ነበር እርሱም ምንድነው ስንል   የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው ይለናል ከዚህም ሌላ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን ?  ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መልሶላቸውም ነበር  የማርቆስ ወንጌል 14 21 የማቴዎስ ወንጌል 26 24 የሉቃስ ወንጌል 20 21 _ 23 የዮሐንስ ወንጌል 6 70 ስለዚህ ኢየሱስ ባላወቃት በይሁዳ ተንኮል ተጠላልፎና ተላልፎ የተሰጠ ሳይሆን ከይሁዳ ይልቅ የይሁዳን ተንኮል በብዙ ያወቀ ስለሆነ እንደ ይሁዳ ተንኮል ሳይሆን እንደተጻፈለት የሄደ ነው ለዚህም ነው በይሁዳ ላይ ይህንን  አሳዛኝ ነገር የተናገረው ወገኖቼ እኛም ታድያ መንፈሳውያን ስንሆን እንደዚሁ ነን እኛ ሁሉን እንመረምራለን እንጂ እኛ ግን በማንም አንመረመርም 1 ቆሮንቶስ 2 15 ውድ የቃሉ እና የበረከቱ ተካፋዮች ቅዱሳን ወገኖቼ ሆይ ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ሁላችንንም ይጥቀመን እነዚህን ሁለት ተከታታይ የሆኑ መልእክቶችን ተጠቀሙበት   እላችኋለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ በማለት የምሰናበታችሁ


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ  ነኝ

God bless u all People of God

Amen and Amen