Thursday 18 February 2016

( ትምህርት ሦስት ) የትምህርት ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 )...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ይህ የተስፋ ቃል ልጅ የሚያደርግ ነው እኛም ወንድሞች ሆይ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን ( ገላትያ 4 ፥ 29 _ 31 ) ይህ ትምህርት በውስጡ ፦ 1ኛ ) ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጅ ሆኖ የተወለደበትን ምስጢር ወደ ስድስት ያህል በሚደርሱ ነጥቦች በዝርዝር ያቀርባል 2ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች የሥጋ ልጆች አይደሉምና የአብርሃም ልጆች የተባሉት በተስፋው ቃል የተወለዱ ልጆች መሆናቸውን በሰፊው ከማስረጃ ጋር ያትታል ገላትያ 3 ፥ 16 ፣ ገላትያ 4 : 23 ፣ ሮሜ 9 ፥ 6 _ 9 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 3 ፥ 8 _ 11 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 8 : 11 – 13 ፣ ሮሜ 8 ፥ 14 3ኛ ) የተስፋው ልጅ ጊዜው ሲደርስ የተወለደ ነው ሮሜ 9 ፥ 9 ፣ ገላትያ 4 ፥ 23 ፣ ዘፍጥረት 21 ፥ 2 ፣ ያዕቆብ 1 ፥ 18 ፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 4ኛ ) የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ብለናልና ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረለት ከመገረዙ በፊት በመሆኑ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙ ጽድቅ ይቆጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው ሮሜ 4 ፥ 9 _ 12 5ኛ ) በዚህም ምክንያት አሕዛብ ከአይሁድ ጋር በክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት አንድ አካል የሚሆኑበትን በዚሁም የተስፋ ቃል ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ አብረው ተካፋይ የሚሆኑበትን ምስጢር እናይበታለን ኤፌሶን 3 ፥ 5 _ 6 ፣ ኤፌሶን 4 ፥ 4 _ 6 ፣ ሮሜ 16 ፥ 26 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ትምህርቱ በእነዚህ ዋና ዋና ነጥቦችና አርዕስተ ጉዳዮች የተጠቃለለ ነው ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል በቪዲዮ የሚለቀቁትን ተከታታይና ቀጣይነት ያላቸውን ትምህርቶች እንደሚገባ ተከታትላችሁ በመጠቀም ለሌሎችም መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር እንድታደርጉት በታላቅ አክብሮት ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment