Tuesday 9 February 2016

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ



የመልእክት ርዕስ



የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ


ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 9 )




ክፍል አንድ














የመልእክት ርዕስ



የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ


ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 9 )



ክፍል አንድ



የተወደዳችሁ ወገኖች በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ዛሬ በዚህ መልዕክት ወደ እናንተ  መጥቻለሁ  ይህንን መልዕክት አንብባችሁ እንድትጠቀሙበትና ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ተባረኩልኝ ይህንን መልዕክት በደሊላና በሶምሶን ታሪክ ጀምሬዋለሁ እንደምትመለከቱትና ከላይም በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ደሊላ ሶምሶንን ልታዋርደው ጀመረች ኃይልም ከእርሱ ሄደ ይለናል ይህ እንግዲህ ደሊላ በትክክል ሥራዋን የጀመረችበት ጊዜ ነው ለማለት እንችላለን ታድያ ይህንን የጅማሬ ጊዜ ነው ሶምሶን በውል ያላወቀው ደሊላ ከሶምሶን ጋር በቆየችባቸው ጊዜያት ለሶምሶን ደሊላ ትክክለኛውን ሥራ የጀመረችበት ጊዜ መስሎታል አይደለም ለሶምሶን ለሁላችንም ቢሆን ደሊላ ከሶምሶን ጋር በተገናኘችባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ከድርጊቶችዋና ከሁኔታዎችዋም የተነሳ በሰላም አብራ ስለምትወጣ ስለምትገባ ከአንደበትዋ ልስላሴና አነጋገር ከምታሳየውም አቀራረብና የአነጋገር ዘዬ ሥራዋን በትክክል የጀመረች ብቻ ሳይሆን በአግባብ ሥራዋን በመስራት ላይ ያለችና የሚገባትንም ሥራ በትክክል እየተወጣች ያለች ሴት መሆንዋንም በቅርብ ርቀት ለምናያት ተጠግተንም ላልተረዳናትና ላላስተዋልናት ሁሉ ሊመስለን ይችላል ብዬ እገምታለሁ የእግዚአብሔር ቅባት በላዩ ላይ ያለ ሶምሶን የደሊላን የሥራ ጅማሬ ያላወቀ  በቅርብ ርቀት ያለን ሰዎችማ ባናውቅ የሚገርም አይሆንም ነገር ግን ደሊላ ሶምሶንን ልታዋርደው የጀመረችበት የሥራ ጅማሬ ዋናውና  አንገብጋቢው ቀዳሚውም የሥራ ጅማሬ ነው በዚህ ውስጥ ልንረዳው የሚገባ አንድ እውነት የተጀመሩ ጅማሬዎች ሁሉ ትክክለኛ የሥራ ጅማሬዎች ናቸው ማለት እንዳልሆኑ ሁላችንም ልናውቀው የሚገባ እውነት እንደሆነ አበክሬ መናገር እፈልጋለሁ ይህን ካልተረዳን የተጀመሩ ጀማሬዎች  ሁሉ ትክክለኛ የሥራ ጅማሬዎች   ሳይሆኑ ቀርተው ፍጻሜያቸው የተበላሹ እንደሚሆኑ ውለን አድረን በዓይኖቻችን ልናያቸው ከእኛ ሩቅ አይሆኑም ስለዚህ በዚህ ነገር መጠንቀቅ ከሁላችን የሚጠበቅ ጉዳይ ሊሆን ይገባል እላለሁ የብዙዎች የሥራ ጅማሬ በተለይ በዚህ ዘመን የደሊላ ዓይነት የሥራ ጅማሬ በመሆኑ አይታወቅም የተጀመሩ ጅማሬዎች ሁሉ ካላስተዋልናቸውና ሃሌሉያ ብለን ከገባንባቸው ሃሌሉያ ብለን እንደገባን ሃሌሉያ ብለን ለመውጣት የማንችልባቸው አሳሳቢ ነገሮች ውስጥ ይከቱናል ደሊላ ከሶምሶን ጋር በጀመረችባቸው የፍቅር የወዳጅነትና የጓደኝነት ጊዜያቶች ጊዜ ለደሊላም ባይሆን ለሶምሶን ግን የሃሌሉያ ጊዜ ነበር ለዚህም ነው በመሣፍንት 14 1 _ 4   በተጻፈው ቃል ላይ  የሶምሶን ድምጽ ከቤተሰቡ ይልቅ ከፍ ብሎ መሰማትን የወደደው በአጠቃላይ ሶምሶን ለቤተሰቡ ያለው ደሊላ ተመችታኛለችና እርስዋን አጋቡኝ ነው ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን ላይ ምክንያት ይፈልግ ነበርና ነገሩ ከእርሱ ሆነ አባትና እናቱ ግን አላወቁም በዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን በእስራኤል ላይ ገዦች ነበሩ ይለናል ሌላው የሶምሶን የሃሌሉያ ጊዜ ወደ ከተማው በመግባቱ ምክንያት በጠላት መከበቡን እና ጠላቶቹም እንደሸመቁበት ሊገደልም እንደተፈለገ ያላወቀው ሶምሶን ጋለሞታዋን ሴት አይቶ ወደ እርስዋ በመግባት እስከ እኩለ ሌሊት መተኛቱ ነው እነዚህንና ከዚያም በኋላ ያለው የደሊላ ያልታወቀው ሽንገላዋ ለሶምሶን የሃሌሉያ ጊዜ የደሊላንም ፍቅሯን ጭምር የማጣጣምያ ጊዜያት የመሰሉ ነበሩ ነገር ግን ሃሌሉያ ብሎ የደሊላ የፍቅር እቅፍ ውስጥ በመግባት መኝታ አግኝቶ እስከ እኩለ ሌሊት የተኛው ሶምሶን የነቃና አንዳንድ ነገሮችን ያደረገ እንኳ ቢመስል ከእቅፏ ግን ወጥቶ ለማምለጥ ያልቻለ በመሆኑ እዚያው በተኛበት ነው ለጠላት የተገኘው ፍቅሯን አጣጣምኩት ተመችታኛለች  እና እርሷን አጋቡኝ ሲል  ደሊላን ለሚስትነት አጭቶ የገባበትን ፍቅር   ለሞትና ለውርደት ሆኖ  አገኘው ከዚያው ከደሊላ እቅፍ ሳይወጣም  የሚደክምበትን ጉዳይ ለደሊላ ተናግሮና የልቡን አጫውቶም  ደከመ ጠላቶች ፍልስጥኤማውያን መጥተው ጸጉሩን ላጩት ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ በመቀጠልም ትክክለኛውና ዋነኛው በፍልስጥኤማውያን በቀዳሚነት የሚጠበቀውም የደሊላ የሥራ ጊዜ ተጀመረ ሶምሶን የነቃው እንግዲህ የደሊላ የሥራ  ጊዜ ተጀምሮ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩ ነው ማለትም ሶምሶን የነቃው ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እያለች ደሊላ ልታዋርደው በጀመረች ጊዜ ነው ይህ ጊዜ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ተደጋጋሚ የሆኑ የደሊላ የሙከራ ቃላቶች እውን የሆኑበት ጊዜ ነው ወገኖቼ አንዳንድ የሙከራ ቃላቶች ለቀልድ ያህል የተነገሩ የመሠሉ የጫወታ ዘይቤዎች ሲሆኑ ጊዜውን ጠብቀውና ጫወታ መሆናቸውም ቀርቶ ለእኛ ለሞታችን የተዘጋጁ ወጥመዶች ሆነው ሲገለጡ ከወዲሁ ካልነቃንባቸው በሕይወታችን የሚያመጡት እጅግ አሳዛኝ የሆነ የታሪክ ጠባሳ ነው ስለዚህ ይህ ከመሆኑ በፊት በተደጋጋሚ ወደ ሕይወታችን ለሚመጡ ጫወታ መሰል የሙከራ ቀልዶች ቆይተው የጠላት ቁምነገሮችና ታርጌቶች ይሆናልና እዚያ ጋር ሳይደርሱ በሕይወታችንም ላይ ሳያደሩ ከወዲሁ ልናስብበት ልንቀጫቸውና ፍጻሜም ላይ ሳይደርሱ በአጭሩ ልናስቀራቸው ይገባል ታድያ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው የወዳጅነት ጭውውት መሰል የሙከራ ቀልዶች የሙከራ ቀልድ መሆናቸው አብቅቶ በሶምሶን ላይ እውንና የተግባር መገለጫዎች የሆኑበት ጊዜ በመሆኑ በእርግጥም ፍልስጥኤማውያን በሶምሶን ላይ መምጣት ችለው ነበር መጽሐፉ አሁንም እንደሚነግረን እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው ከእንቅልፉም ነቅቶ፦ እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር ይለናል መሣፍንት 17 20 _ 22 ስለዚህ በማናኛውም አቅጣጫ እና የሥራ ዘርፍ ተጀመሩ ያልናቸው የሥራ ጅማሬዎች  ተከታትለን ካላየናቸው ባልጠበቅነው ሁኔታ ተፈጽመው እንደ ሶምሶን ታሪካችንን አሳዛኝ ሊያደርጉት ይችላሉና ከወዲሁ ሥራዎቻችንን ሁሉ ጥንቃቄ የተሞላበት ልናደርገው ይገባል የተጀመሩ የሚመስሉ ደግሞ የተጀመሩ ናቸው ብለን ብዙ ርቀት ከተጓዝን በኋላ እኛ በጠበቅነው መንገድ ሳይሆን ሌላ ጅማሬን በሕይወታችን አምጥተው  መውጫን ያሳጡናል ፣ ለውርደትና ለሞትም ይዳርጉናል ስለዚህ   በትክክለኛ ሁኔታ የተጀመሩ ከሆኑ በትክክለኛ ሁኔታ የተጀመሩ መሆናቸውን ከወዺሁ ቆም ብለንና ከጒዞአችንም ተገተን በትክክል የተጀመሩ መሆናቸውን ልናይ  ልናጤናቸውም ይገባል መልእክቱ ቀጣይ ክፍል ሁለት አለው ተባረኩ


       

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ



No comments:

Post a Comment