Tuesday 23 June 2015

010 የትምህርት ርዕስ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ ዓላማ አለው God’s Purpose in Marriage ክፍል ሁለት ቊጥር ፪ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ ዓላማ አለው ምክንያቱም ጋብቻን የሰራውና የጋብቻ ጥምረትንም ያመጣው ራሱ እግዚአብሔር ነው በማቴዎስ ወንጌል 19 ፥ 4 _ 6 ላይ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን፧ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው ይለናል ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ናቸው ታድያ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ ዓላማ አለው ካልን ሴት ማን ናት ? ዓላማዋስ ምንድነው ? 1ኛ ) ሴት ረዳት ናት እንደገናም አዋቂና ባለሞያም ናት ( ምሣሌ 31 ን በሙሉ እንመልከት ) 2ኛ ) ጋብቻ በእግዚአብሔር የተሰጠና የታዘዘ ግንኙነት ነው ክህነት እንደመስጠት ዓይነት ያለ ግንኙነት በመሆኑም እግዚአብሔር ሲያጣምር ክህነት ሰጥቶ ማለትም የጋብቻ ኦርዲኔሽን ሰጥቶ ነው ያጣመረው He then caused them to come together as man and wife to become << one flesh >> in this God ordained relationship 3ኛ ) ልባም ሴት እንዳለች ሁሉ አሳፋሪ ሴት በአጥንት ውስጥም እንደ ቅንቅን የሆነች ሴት አለች ( ምሳሌ 12 ፥ 4) 4ኛ ) ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት ማለት ባልዋን የምታንጸባርቅ ናት ማለትም በባልዋ ባለው በማንኛውም ነገር ላይ መጨመርን የምታደርግ ወይንም የምትደርብ ስትሆን አሳፋሪ ሴት ግን በተቃራኒው ያለውን ነገር የምታደርግ ፣ የምትላጭ ፣ እያሟጠጠችም የምታደርቅ ናት 5ኛ ) እውነተኛና ልባም ሴት በትዳር ውስጥ ባልዋን ለውጤታማነቱ ተጨማሪ ኃይል የምትሆንና ለዚሁ ለባልዋም የመጨረሻ ውጤት ናት 6ኛ )ውጤት የሚጠብቀው እግዚአብሔር ከባሎች ነው ሚስቶች ግን ለዚህ መንገዶች ናቸው 7ኛ ) ይህ እንዲሆን ታድያ የሴቶች ባሕርይ በእርግጠኝነት ያማረ ሊሆን ይገባል 8ኛ ) ለባልዋ ዘውድ የምትሆን ሴት ባሕርይዋ ያማረ ሊሆን ይገባል( ምሳሌ 12 ፥ 4 ) 9ኛ ) ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ብቻ ሳትሆን የባልዋም ክብር ናት( 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 7 ) 10ኛ ) ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ስትሆን ባልዋን ንጉሥ እያደረገችው ነው እንደገናም እራስዋንም በዚያው ልክ ንግሥት እያደረገች ነው ( ዘፍጥረት 18 ፥ 18 ) 11 ) ይሁን እንጂ ሚስት ለባልዋ የመጨረሻ ውጤት ሆና ብትመጣም ባል ሚስቱን ራስዋን እንድትሆን ማበረታታት አለበት የክፍል ሁለት ትምህርት ጠቅለል ያለ ሃሳቡ ይህን ይመስላል ይበልጥ በቪድዮ የተላለፈውን ስትሰሙት ደግሞ ትባረኩበታላችሁ እስከዚያው ሰላም ሁኑ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment