Tuesday 16 June 2015

003 የትምህርት ርዕስ እግዚአብሔርን የመቀደስ ሕይወት ክፍል ሦስት እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ላይ ጠብ ያደረጉበት፥ እርሱም ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው ኦሪት ዘኍልቍ 20 ፥ 12 እና 13 ጌታ እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን ላይ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም ሲል ይህንን ውሳኔ ያሳለፈባቸው እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ጋር በተጣሉበት ጊዜ ሙሴና አሮን በማኅበሩ መካከል እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን መግለጥ ስላልቻሉ ነው እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ነው የተጣላው ? ስንል መጽሐፉ እንዴት እንደተጣላ ይነግረናል የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም በሙሴና በአሮንም ላይ ተሰበሰቡ ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፦እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁን ? ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን ? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው የሚጠጣም ውኃ የለበትም ኦሪት ዘኍልቍ 20 ፥ 1 _ 5 ወገኖቼ ቦታውም ምድረበዳ ይሁን ፣ ክፉ ስፍራም ይባል ፣ ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ይሁን ፣ የሚጠጣም ውሃ አይኑር እስካሁን ድረስ ከምንም ሳያጎድላቸው እዚህ ያደረሳቸው እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ጋር አለ እስራኤል ይሄና ያ ጠፋ የለም ቦታውም ምድረበዳ እና ክፉ ሥፍራ ነው ከሚሉት ነገር ጀርባ ትልቁን እግዚአብሔርን ነበር ማየት ያቃጣቸው ይህ ሁኔታ ታድያ ለማህበሩ ብቻ ሳይሆን ለነ ሙሴም ሳይቀር ግር የሚያሰኝ ነገር ሆኖባቸው ነበር ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ለነሙሴ ክብሩን ገለጠ እነሙሴም ሊያደርጉት የሚገባውን መመርያ ነገራቸው እነ ሙሴ ግን ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔርን መመርያ ተከትለው ማድረግ አልቻሉም ይሄና ያ የለም ቦታውም ምድረ በዳ ነው ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁን ? እያለ በእጃዙር ከእግዚአብሔር ጋር ክፉኛ እየተጣላ ላለ ለእስራኤል እግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑን አልገለጡም ይልቁንም ያልታዘዙትን በማድረግና ድንጋዩንም በመምታት እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን ? አላቸው አዲሱ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም ይህን ሁኔታ ይበልጥ አብራርቶ ይጽፈዋል እናንት አመጸኞች አድምጡ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን ? አላቸው ይለናል በመቀጠል ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ ይለናል ዛሬም ሆነ በዘመናት መካከል ግን ከዐለቱ ውሃ ማውጣት የሚችል መጽሐፉም እንደሚነግረን እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል አሁንም በጥም እሞታለሁ፥ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ሶምሶን ወደ እግዚአብሔር ጮኸ እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም ይለናልና መጽሐፈ መሣፍንት 15 ፥ 18 _ 20 በሌሒ ያለውን ዐዘቅት በመሰንጠቅ የታመነ እግዚአብሔር ዛሬም የታመነ ነው በመሆኑ እርሱ እግዚአብሔር ነው እንደውም አሁንም መጽሐፉ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ጠጥተዋልና ያም ዐለት ክርስቶስ ነው ይለናል 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 4 ይህ መንፈሳዊ ዐለት የሰው ልጆችን ከሥጋዊም ሆነ ከመንፈሳዊ ጥም ሊያረካ ላመኑበትና ለተጠጉት ሁሉ ዛሬም የሚከተል ዐለት ነው ጠብ ጠብ የሸተተው እስራኤል ግን የትላንቱን የእግዚአብሔርን መልካም ነገር ረስቶ ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ ዛሬም ይህን ሊያደርግ እግዚአብሔር ታማኝ ነው ሲሉ እነ ሙሴ እግዚአብሔርን በጠበኛው በእስራኤል ፊት መቀደስ አቃታቸው እርሱን እግዚአብሔርን ከሚቀድሱት ይልቅ እናንት አመጸኞች አድምጡ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን ? ሲሉ እርሱ ክብሩን ገልጦላቸው ሳለ ያን ክብር ለራሳቸው በመውሰድ ራሳቸውን መቀደስ መረጡ ለዚህ ነው ጌታ እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን ላይ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም ሲል የተናገራቸው 1ኛ) እግዚአብሔርን መቀደስ ያለብን መቼ ነው ? ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ጠብ ባደረጉበት ጊዜ ነው ጥቅሶቹ በቪድዮ በተለቀቁት ትምህርቶች ውስጥ በስፋት ቀርበው ስላሉ እነርሱን ተከታትላችሁ መስማት የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ በጌታ ፍቅር ላሳስብ እወዳለሁ 2ኛ ) እግዚአብሔርን የምንቀድሰው በምንድነው ? በተናገረው ቃል ነው አሁንም ለዚህ በማስረጃነት የቀረቡ ጥቅሶች በዚሁ በቪዲዮ የትምህርት ቀረጻ ውስጥ ተዘጋጅተው አሉና እነዚሁኑ ጥቅሶች ፣ ትምህርቶቻቸውንም ጭምር ገብታችሁ የምትከታተሉ መሆናችሁን ላሳስብ እወዳለሁ ወገኖች በጌታ በሆነው ፍቅር አብዝቼ እወዳችኋለሁ በጸሎቴም አስባችኋለሁ እስከዚያው ጌታ በነገር ሁሉ አብዝቶ ይባርካችሁ በማለት የምሰናበታችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ሁላችሁም ተባረኩልኝ አሜን

No comments:

Post a Comment