Monday 22 June 2015

007 የጋብቻ ትምህርት ክፍል አንድ የትምህርት ርዕስ እግዚአብሔርን መካከል ያደረገ ጋብቻ መገንባት Build A God – Centered Marriage ቊጥር ፪ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል መዝሙር 127 ፥ 1 እግዚአብሔርን መካከለኛ ያደረገ ጋብቻ ለመገንባት እግዚአብሔርን ብቻ መካከለኛ ያደረገ ጋብቻ ይኑረን ዛሬ ቤታችን የሚበጠበጠውና የሚፈርሰው ብዙ ነገሮችን መካከለኛ እያደረግን ከማስገባታችን የተነሳ ነው እግዚአብሔርን ከመካከል አስወጥተን ገንዘብን ውበትን ሃብትንና ንብረትን ዘመዶችን ጓደኞችንና የመሣሠሉትን ሁሉ መካከለኞች አድርገን በትዳራችን መካከል ስናስገባ ቤታችን እግዚአብሔር የሠራው ቤት ቢሆንም እንኳ መፍረስና መበተን ይጀምራል እግዚአብሔር መካከለኛ ሆኖ የገባበት ጋብቻ ግን የሚፈርስና የሚበተን ሳይሆን የሚሠራና የሚገነባ ነው እግዚአብሔር ቤተሰሪ ስለሆነ ሊፈርስ የደረሰ ጋብቻን ሳይቀር መልሶ ይገነባል በቪድዮ የተለቀቀው የክፍል አንድ ትምህርት ይህንን በሰፊው ይዘረዝራል ፣ ያስተምራል ስለዚህ ቅዱሳን ወገኖች ይህ ትምህርት በውስጡ ብዙ ነገር ያዘለ ስለሆነ ይህንን ትምህርት በማስተዋል ሆናችሁ ተከታተሉት ከዚህም ሌላ እግዚአብሔርን የጋብቻችን መካከለኛ በምናደርገው ጊዜ እርሱ ከሚያደርግልን ነገር የተነሣ የሚሆንልን ነገር አለ ትምህርቱ ይህንንም በሰፊው ይዘረዝራል እግዚአብሔር የሚያደርግልን ነገር ፦ 1ኛ ) እግዚአብሔር ታላቅ የሆነ ሕግ ሰጪ ነው He is a great Low giver መዝሙር 18(19)፥ 7 _ 9 ፤ ያዕቆብ 1 ፥ 25 ፤ መዝሙር 22 ( 23 )፥ 3 ፣ 1 _ 6 2ኛ) እግዚአብሔር ታላቅ የሆነ ዕቅድንና ፕላንን አውጪ ነው He is a great Designer መዝሙር 32 ( 33 )፥ 11 ፤ ኤርምያስ 29 ፥ 11 ፤ ሮሜ 8 ፥ 28 3ኛ) የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት መፍቀድ አለብን እግዚአብሔር ዓለምን የሚቆጣጠር በመሆኑ በፍጥረቱ ላይ በመካከል ይገባል He is an Intervenes in his Creation ዕብራውያን 4 ፥ 13 4ኛ )እግዚአብሔር በዓላማ በምድር ላይ የሚሰራ ነው የእግዚአብሔርን ዓላማ በምድር ላይ እንተገብራለን Working out on Purpose here on earth 5ኛ)እግዚአብሔር ወንድና ሴትን የፈጠረ ነው One who creator us male and female ዘፍጥረት 2 ፥ 7 ፤ ዘፍጥረት 2 ፥ 18 6ኛ) ሰው ብቻውን በመሆኑ ያልተፈጸመና ያላለቀ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 23 7ኛ) ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር አንድና ከእርሱ ጋር በትክክል ማውራት ፣ ሃሳቡን መካፈል ፣ ዕቅዱን መካፈል ፣ ተስፋውንና ራዕዩን መካፈል የምትችል ናት ዘፍጥረት 2 ፥ 20 God made a « helper » Comparable to Adam One to whom he could truly relate and share his thoughts , his plans , his hopes and dreams እንግዲህ ቅዱሳን ወገኖቼ ከትምህርቱ ጋር ሁኑ ይህንንም ትምህርት እየሰማችሁ ተባረኩበት ተጽናኑበት ለሌሎችም ላልሰሙ ወገኖች አስተላልፉ እያልኩ የምሰናበታችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ተባረኩልኝ ለዘላለም

No comments:

Post a Comment