Friday, 23 August 2019

Drinking tela with Ethiopian Orthodox Priests in Tigrayሆድን ወይንም ከርስን ለመሙላት ብቻ ሲባል በብልጣብልጥ ካህናት ተጽፎ የተዘጋጀ የመጽሐፈ ግንዘት ተረትና የሽንገላ ሃሳብ ወገኔ ልንገርህ እንግዲህ ንቃ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ፣ ዶሮን ሲያታልሉአት በመጫኛ ጣሉአት ፣ ለማያውቁሽ ታጠኚ እና የመሣሠሉትን ብዬዋለሁ :: ሃሳቡ እንዲህ የሚል ነው :: ጸሐፊዎቹ ጮሌዎች እንደመሆናቸው መጠን ጥቅም እንዳይቀርባቸው ሲሉ አንድም የቤተክርስቲያን አባል ጸሎተ ፍትሐት ሳይደረግለት ወይንም ፍትሐት ሳይፈታ ከዚህ ዓለም ወደ መቃብር መሸኘት እንደሌለበት ይህንን ጽፈዋል :: በመጀመርያ በግዕዙ ቃል አስቀምጠውና ወደ አማርኛ እተረጉመዋለሁ :: ወኢመንኖሙ ለአዝማዲነ ለአበዊነ ወለአሃዊነ እመኒ ኮኑ ኃጥአነ እስመ ክርስቶስ መጽአ በእንተ ኃጥአን ወአኮ በእንተ ጻድቃን :: ወደ አማርኛው ሲተረጎም እንዲህ የሚል ነው :: " ዘመዶቻችን አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ኃጥአንም ቢሆኑ አንናቃቸው ክርስቶስ የመጣው ስለ ኃጥአን እንጂ ስለ ጻድቃን አይደለምና " በማለት ጸሎት ፍትሐት እንዲደረስላቸውና እንዲፈቱ እነ መምሬ ሽርሽርና እነ መምሬ ሆድ አምላኩ በዚሁ በመጽሐፈ ግንዘት መጽሐፋቸው ላይ አዘዋል :: ( ምንጭ መጽሐፈ ግንዘት መቅድም ጮራ መጽሔት ቊጥር 15 ) ታድያ ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ እነዚህ እነ መምሬ ሆድ አምላኩ " ዘመዶቻችን አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ኃጥአንም ቢሆኑ አንናቃቸው ክርስቶስ የመጣው ስለ ኃጥአን እንጂ ስለ ጻድቃን አይደለምና " ሲሉ ይህችን በማር የተሸፈነች ቃል መናገራቸው ክርስቶስ ለሞተላቸው ለኃጥአን ወንድሞቻቸው ከዚህም ሌላ ለክርስቶስና ለክርስቶስ ወንጌል ጭምር ተቆርቊረው ይመስሏችኋል ? በፍጹም አይደለም የአርባና የሰማንያ እንዲሁም የሙት ዓመት ድግስና ተዝካር እንዳይቀርባቸው ከማሰብ ልግል ጥቅማቸው ሲሉ ነው :: ለኃጥአን ወንድሞቻቸውና ለክርስቶስ ወንጌል ተቆርቊረው ቢሆንማ ሰዎች የሚድኑት በሥጋ ከማንቀላፋታቸውና ከመሞታቸው በፊት ገና በሕይወት እያሉ ኢየሱስን በማመን ብቻ በመሆኑ ( 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 ) ለሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኋላ ፍርድ ተመድቧልና ( ዕብራውያን 9 ፥ 27 ) ሰዎቹ በሥጋ ከመሞታቸውና ከማንቀላፋታቸው በፊት ሰዎችን ከዘላለም ፍርድ ለማስመለጥ ገና በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ነበር መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው ሲሉ ይህንኑ አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን ሊሰብኩላቸውና ሊያስተዋወቋቸው የሚገባው (የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ):: አሁን ግን ወንድሞቻችን ኃጥአንም ቢሆኑ አንናቃቸው ክርስቶስ የመጣው ስለ ኃጥአን እንጂ ስለ ጻድቃን አይደለምና ሲሉ ይህቺን ጣፋጭ መሰል የመደለያ ጥቅስ መጥቀሳቸው ሰዎች ሊያዘጋጁላቸው ወደሚወዱት ወደ ድግሷና ተዝካርዋ ጠጋ ጠጋ ለማለትና ሆዳቸውንም ለመሙላት እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው :: በመሆኑ በእነዚህ አታላይ ቄሶች ለዓመታት ከዘመድ ከጓደኛ ከወንድም ከእህት ከአባት እስከቅድም አያት ድረስ በደረሰ ነገር ሁሉ ተዝካር በማውጣት ገንዘባችንን የተዘረፍንና የተነጠቅን ቢሆንም አሁን ግን ነቄ ብለናል :: ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት እንዲሉ አብዛኞቹ የመንደር ካህናት ስለሆኑ የተዝካርና የዝክር ነገር ሲባል አይሆንላቸውምና ለመብላት ሲሉ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም :: እንደዚህም የሚያደርጉት ሕዝቡን ስለናቁት ነው :: በገዛ አፋቸውና በመጽሐፋቸውም ጭምር እንደተናገሩት ሕዝቡን የናቁት ሌላው ሳይሆን እነርሱ ራሳቸው ናቸው :: እንዲህም እያሉ ነው እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል በትክክክል የማያውቀውን ሕዝብ እያታለሉ የሚበዘብዙት :: ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም ሲል የክርስቶስ መምጣት የማያስፈልጋቸው ጻድቃን አሉ ለማለት አይደለም :: ይህንን ጥቅስ በማስተዋል አንብቡ ( ሮሜ 3 ፥ 11 — 23 )ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም ማለቱ መምህራችሁ ከቀራጮች ጋር ስለምን ይበላል ብለው ራሳቸውን ጻድቃን አድርገው ኃጢአተኞችን ለሚንቁ ፈሪሳውያን የተናገረው ነው ( የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 13 ፤ የማርቆስ ወንጌል 2 ፥ 17 ) በማንበብና በማስተዋል ወደ ቃሉ እውነት መምጣት ይሁንልን ተባረኩልኝ ወንድማችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ከኦርቶዶክስ ተሃድሶ ሐዋርያዊ አገልግሎት

No comments:

Post a Comment