Thursday, 30 August 2018

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ስድስት ) ( ቊጥር 1 ) የዛሬው አዲሱ ትምህርታችን በማስታወቅያው መሠረት አንድ ብሎ በክፍል ስድስት ተጀምሯል በውኑ ድንግል ወደ እኛ በአሁኑ ሰዓት መምጣት ትችላለችን ? 1ኛ ) በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፈ ሰዓታት ( የሰዓታት መጽሐፍ ) በተባለው የጸሎት መጽሐፍ ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ሲሉ ረጅሙን ዜማ እያዜሙ ይጸልያሉ በፍልሰታ ጸምና በዓቢይ ጾም እንዲሁም በሌሎች አጽዋማት ሳይቀር ካህናት በመንፈቀ ሌሊት ተነስተው ይህንኑ ጸሎት በዚህ የሰዓታት መጽሐፍ መሠረት ያደርሳሉ 2ኛ ) ህዝባዊ መዝሙርም ወጥቶለት ፣ ህዝባችንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም እያለ በመዘመር ድንግልን ይማጸናል ይህ ለምን ይሆን ? የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬው ትምህርታችን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ በሚለው የሰዓታት መጽሐፍ ቃል መሠረት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህናት ፣ የሰንበት ተማሪዎችና ሕዝበ ምዕመናን ጭምር ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም በማለት በመዝሙርና በአምልኮ ማርያምን ሲማጸኑና ሲጠሩ እንሰማቸዋለን :: በዚህ ትምህርት ውስጥ ግን ነይ ነይ እየተባለች የተጠራችው ማርያም በሞት የተወሰነችና ሞትም የከለከላት በመሆንዋ ልትመጣ እንደማትችል ትምህርቱ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት አብራርቷል :: ይሁን እንጂ ይህንን የቃሉን እውነት ካለመረዳት የተነሳ ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነይ ወይንም ነይ ነይ እናቴ ማርያም እያሉ አሁንም የኦርቶዶክስ ካህናትም ሆነ ሕዝበ ምዕመናን በዚህችው በማርያም ፍቅር ከመያዛቸው የተነሳ ቢቀጥሉ ሳያውቁት ወደ መናፍስት ጠሪና ወደ ሙታን ሳቢ መንፈስ ውስጥ ገብተው የጠረፍዋ ንግሥት መጫወቻ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት ንጉሥ ሳኦል ሳይቀር ሕይወቱ የተጎዳው በመናፍሥት ጠሪዎች መሆኑን ትምህርቱ አሁንም ማከያ ሃሳብ ሰጥቶ በአጽንኦት ይናገራል 1ኛ ሳሙኤል 28 በሙሉ ፣ 1ኛ ዜና መዋዕል 10 ፥ 13 እና 14 ን ይመልከቱ :: የተወደዳችሁ ቅዱሳን የዚህ ክፍል ዋና ትምህርት እንግዲህ ድንግል ማርያምን ንዒ ኃቤየ ኦ ድንግል ፣ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ነዪ ወይንም ነይ ነይ እምዬ ማርያም ሲሉ በመጣራት የሚመጣውን አደጋ የጠቆመን ብቻ ሳይሆን የመፍትሔውንም ዓይነት ደረጃ በደረጃ ነግሮናል 1ኛ ) በትንቢተ ኢሳይያስ 8 ፥ 19 መሠረት ከየትኛውም አቅጣጫ ጠይቁ የሚባል ነገር ሲመጣ ፣ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር መጠየቅ አለበት:: 2ኛ ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ መሄድ አለበት ( ትንቢተ ኢሳይያስ 8 : 20 - 22 ) ወደ ሕጉና ወደ ምሥክሩ ስንል ፣ ጊዜ ወስዶ መጽሐፍቅዱስን ከሚያስጠኑና ከሚያስተምሩ ሰዎች በአግባቡ መማር ፣ በመጽሐፍቅዱስ ጥናቶች ሳይቀር ታማኝ ተማሪ መሆንን ያጠቃልላል :: 3ኛ ) ስንጠራው እግዚአብሔር የሚመልስልን አምላክ ነውና ፣ ነይ ነይ እምዬ ማርያም ከማለት ይልቅ እግዚአብሔርን መጣራት ዳግም ለተወለደ ለማንኛውም ክርስቲያን ድልን የሚያጎናጽፈው ነው በማለት የዛሬው ትምህርት በዚሁ ይደመደማል :: እነዚህ ጥቅሶች ለመጨረሻውና ለ3ኛው ቊጥር ማጠቃለያንና መደምደምያን የሚሰጡ ቊልፍ ሃሳቦች ስለሆኑ መጽሐፍቅዱሳችሁን በመግለጥ ጥቅሶቹን አንብቡአቸው ተባረኩ መዝሙር ( 91 ) : 15 እና 16 ፤ 2ኛ ሳሙኤል 22 ፥ 4 - ፍጻሜ ፤ 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 20 _ 46 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 6 ፥ 9 ፤የማቴዎስ ወንጌል 7 ፥ 7 _ 12 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 6 ፣ 14 ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ አስፋው

No comments:

Post a Comment