Friday, 20 July 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 15 ) ክፍል አራት አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ( ምንጭ ቅዳሴ ማርያም ) ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን ( 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 15 ) የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ተስፋን በተመለከተ ይህ የመጨረሻና የማጠቃለያ ትምህርት ነው ከላይ በመግቢያ ጥቅሴ ላይ እንዳነሳሁት በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ ይለናልና በእኛ በእያንዳንዳችን ያለ ተስፋ ከተማርነው ትምህርት አንጻር ክርስቶስ እንጂ የቅዳሴ ማርያም ጸሐፊ እንደተናገረው ማርያም አይደለችምና ተስፋችን ስለሆነው ክርስቶስ ለሚጠይቁን ሁሉ መልስ ልንሰጥ ዘወትር የተዘጋጀን ልንሆን ይገባል በመሆኑም በዚህ ትምህርት ውስጥ የተካተቱ ሃሳቦች አሉ 1ኛ ) የመምጣቱን ተስፋ አስመልክቶ በእኛ ስላለው ተስፋ ምክንያት ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን በዝርዝር የምንመለከታቸው ይሆናል ሀ ) የመምጣቱ ተስፋ ወዴት ነው ? የሚሉና አባቶች ከሞቱበት ጊዜ ከፍጥረት መጀመርያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራል የሚሉ ፣ እንደራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበትም የሚመጡ ናቸው ( 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 4 ) ለ ) በጌታ የመምጣቱ ጉዳይም ጌታ ከመምጣት የሚዘገይ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ ( 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 9 ፣ ዕብራውያን 10 ፥ 37 _ 39 ) ሐ ) ጌታን በመጠበቅ ደግሞ የታከቱ ሰዎች አሉ ( 2ኛ ጴጥሮስ 3 _ 11 _ 15 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 25 በሙሉ ፣ የሉቃስ ወንጌል 12 ፥ 35 _ 48 ) ታድያ በእኛ ስላለ ተስፋ ምክንያትን የሚጠይቁ ሰዎች እነዚህንና እነዚህን የመሣሠሉ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ስላሉ እነርሱ ለሚያነሱት ጥያቄዎች ሁሉ በእኛ በኩል መልስ ልንሰጥ ዘወትር የተዘጋጀን መሆን አለብን 2ኛ ) ቃሉ እንደነገረን በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን ይላልና በእኛ ያለው ተስፋ ምንድነው ? ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ትምህርቱ በክለሣ መልክም ቢሆን በእኛ ያለውን ተስፋ በዝርዝርና በቅደም ተከተል ያቀርባል ሀ ) በእኛ ያለው ተስፋ ከዘላለም ዘመናት በፊት የተሰጠ ተስፋ ነው ( ቲቶ 1 ፥ 1 እና 2 ) ለ ) የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋ ነው ( 2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 4 ) ሐ ) ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ነው ( ዕብራውያን 7 ፥ 18 እና 19 ) መ ) ለአባቶች የተሰጠ ተስፋና በመጨረሻም እግዚአብሔር ኢየሱስን አስነስቶ ለእኛና ለልጆቻቸው የፈጸመው ተስፋ ነው ( የሐዋርያት ሥራ 13 ፥ 32 እና 33 ) ሠ ) የዘላለም ሕይወት ተስፋ ነው ( 1ኛ ዮሐንስ 2 ፥ 25 ) ረ ) እርግጠኝነት ያለበትና እንደ ነፍስ መልሕቅ የሆነ ተስፋ ነው ( ዕብራውያን 6 ፥ 19 ) ሰ ) የምንደፍርበት ፣ የምንመካበት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ የምንሆንበት ተስፋ ነው ( ዕብራውያን 3 ፥ 6 ) ሸ ) ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለየንበት ተስፋ ነው ( ሮሜ 1 ፥ 1 እና 2 ፣ 3 _ 5 ) ቀ ) የሕይወትን አክሊል የምናገኝበት ተስፋ ነው ( ያዕቆብ 1 ፥ 12 ) በ ) የተስፋችንን ምስክርነት የምንጠብቅበት ተስፋ ነው ( ዕብራውያን 10 ፥ 13 ) የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች እነዚህ ናቸው ለበለጠ መረጃ በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ይከታተሉ የተወደዳችሁ ወገኖች እንግዲህ የቅዳሴ ማርያም ጸሐፊ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት በማለት አዳም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ሲል በወቅቱ ለሆነው ነገር ማርያምን የተሰደደው የአዳም ተስፋ ናት ቢላትም መጽሐፍቅዱሳችን ግን ከዚህ በተቃራኒው የአዳም ተስፋው ክርስቶስ እንደሆነ በሰፊው ያትታል ታድያ እኛም ልናይ የሞከርነው ይህንኑ እውነት ነው ስለዚህ የአዳም ተስፋው ማርያም ሳትሆን ክርስቶስ መሆኑን መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት በሰፊው አብራርቼ ተናግሬያለሁ ቀጣዩ ትምህርታችን የሚሆነው ግን ተፈስሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ የአዳም ፋሲካው የሆንሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ የሚል በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ስላለ በቀጣዩ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን የአዳም ፋሲካው ማን እንደሆነ ከመጽሐፍቅዱሳችን አስረጂ በማቅረብ የምንመለከተው ይሆናል እስከዚያው ጌታ ሁላችንንም የዚያ ሰው ይበለን ቸር እንሰንብት አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment