Saturday, 14 July 2018
ገድላትና ድርሳናት መጽሐፍቅዱስን ተንታኞች እንጂ ተኪዎች አይደሉም ያሉት መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ የስሕተት አስ...ገድላትና ድርሳናት…………መጽሐፍቅዱስን ተንታኞች እንጂ ተኪዎች አይደሉም ሲሉ የተደመጡት የመጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ የስሕተት አስተምህሮ በእግዚአብሔር ቃል ተጋለጠ የቅኔውና የመጽሐፉ መምህር መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ገድላት፣ ድርሳናት የተአምራት መጻሕፍትና የመልካ መልክ ድርሰቶችም ጭምር የመጽሐፍቅዱስ ማብራርያዎች ናቸው ሊሉን የተጠቀሙበትን ዘዴ እንደሚከተለው አቀርባለሁ ስለ ድንግል ማርያም ብፅዕና እና ስለ ሌሎችም የመጽሐፍቅዱስ ሃሳቦች ሊናገሩ ፈልገው ማርያምን ዋና ተጠቃሽ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ስትል ማርያም ተናገረች ርዕሰ ዜናውን ሉቃስ አቀረበ እነ ኤፍሬም ሶርያዊ ፣ ነገረ ማርያም ፣ ተአምረ ማርያም ፣ ዮሐንስ አፈወርቅና የመሣሠሉት ደግሞ ማብራርያውን ወይም ትንታኔውን ሰጡ ሲሉ ሊያስረዱን ሞከሩ እኔ ግን በጣም የሚደንቀኝ 1ኛ ) እነዚህ አባት የለሽ የገድልና የድርሳን መጻሕፍት 2ኛ ) ተደራሽነታቸው ለማን እንደሆነ እንኳ የማይታወቁ መጻሕፍት እንዴት ሆነው ነው የትልቁ የእግዚአብሔር መጽሐፍና የእኛም መጽሐፍ የሆነው የመጽሐፍቅዱስ ማብራርያ ሊሆኑ የሚችሉት የመጽሐፍቅዱስን ስነ አፈታትና ትርጓሜን የተማረ ሰው መቼም አዋልድ መጻሕፍትም ሆኑ ገድላትና ድርሳናት የመጽሐፍቅዱስ ማብራርያ ናቸው ሲል እንዲህ ይላል ፣ ይህንንም ያስባል ብለን አንገምትም የመጽሐፍ ቅዱስን አተረጓጐም ማብራርያቸውን የምናገኘው አዋልድ መጻሕፍት ፣ ገድልና ድርሳናት ውስጥ ነው ሊል ቀርቶ መጽሐፍቅዱሱን ሲተረጉም እንኳ አውዱን በጠበቀ መልኩ አንቀጹንና ሙሉውን ምዕራፍ ተመልክቶ በቁርኝት ጥቅሶችና በማመሳከርያ ምንባቦች ሃሳቡን በመረዳት ነው አልፎም ሄዶ ከጠቅላላው የመጽሐፍቅዱስ ሃሳብ ጋር አስተያይቶ ሊገነዘብ ይወዳል ከዚህም ሌላ የተጻፈበትን ክፍለ ዘመን ፣ ለምንና ለማን እንደተጻፈ ፣ መቼ እንደተጻፈና የት እንደ ተጻፈ እነዚህን ሁሉ እና የመሣሠሉትን በማድረግ የተጻፈበትን ዋና ሃሳብ ያገኛል ይህንንም የሚያደርገው ማንም ሰው መጽሐፍቅዱስን ለገዛ ራሱ መተርጎም ባለመቻሉ ትክክለኛውንና መጻሕፍት የመሠከሩለትን የእግዚአብሔርን እውነት ለማግኘት ነው 2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 16 _ 21 ስለዚህ የቅኔውና የመጽሐፉ መምህር መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ይህቺን አጭር መልዕክትና የቪዲዮ ትምህርት ተመልክተው ትምህርቶትን በእነዚህ እውነቶች እንዲቃኙ ፣ እንዲያስተካክሉም በማሰብ ይህቺን አጭር ማሳሰብያ ከታላቅ ትሕትና ጋር ልተውሎት እወዳለሁ ወዳጅ ፣ ዘመድ ፣ ጓደኛ ፣ የቅርብ ሰዎችም ካላችሁ ይህ ትምህርት እንዳያመልጣቸው መልዕክታችንንም ሆነ ቪዲዮአችንን ለመጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ አድርሱአቸው የክፍል ሁለት ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከተሃድሶ ለኦርቶዶክስ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment