Tuesday, 17 July 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 14 ) ክፍል አራት አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ( ምንጭ ቅዳሴ ማርያም ) 1ኛ ) ምንም እንኳ የቅዳሴ ማርያም መጽሐፍ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት ትርጉም ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ቢለንም ለተከታታይ ሳምንት ከተማርናቸው የእግዚአብሔር ቃል እውነቶችና ትምህርቶች የተነሳ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት የተሰጠው ተስፋ አንድና አንድ ኢየሱስ ስለሆነ መቼም ማርያም ናት እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ 2ኛ ) እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት የተሰጠው ተስፋ ( ኢየሱስ ) አሁንም የተጠበቀ ስለሆነ ከእናንተ ማንም ለዚያ ሳይበቃ እንዳይቀር እንጠንቀቅ ይለናል ( ዕብራውያን 4 ፥ 1 _ 4 ) 3ኛ ) ለዚህ መፍትሔው ወደ ዕረፍቱ እንድንገባ የተሰጠንንና የተጠበቀልንን ተስፋ ( ኢየሱስን ) እንደሚገባ መስማት ፣ ማመንና መታዘዝ ነው ( ዕብራውያን 2 ፥ 1 _ 4 ) 4ኛ ) እኛ ያመነው ግን ወደ ወደዚያ ዕረፍት እንገባለን ተብሎ ተጽፎልናል ( ዕብራውያን 4 ፥ 3 ) 5ኛ ) በዕብራውያን 12 ፥ 15 መሠረት ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድልበት ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ ይለናል በመሆኑም ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድልበት ማለቱ የእግዚአብሔርን ጸጋ ሳይዝ እንዳይቀር ማለቱ ነው 6ኛ ) ከዚህ እውነት የተነሳ የምንድነው በሥራችን ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ጸጋ መጣል የለብንም ( ኤፌሶን 2 ፥ 8 ፣ ቲቶ 2 ፥ 11 ፣ ገላትያ 2 ፥ 21 ) 7ኛ ) የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያስጥሉን ወይንም ሳንይዝ እንዳንቀር የሚያደርጉንና ወደ አለመታዘዝ ሊወስዱን መራራ ሥር ሆነው በውስጣችን የበቀሉ ቁጣ አድመኝነትና የመሣሠሉት ናቸው ( ዕብራውያን 12 ፥ 15 ) 8ኛ ) እግዚአብሔር የራሱን ዕረፍት እንድንካፈል ጋበዘን 9ኛ ) ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት መግባት የሚቻለው በልጁ በማመን ነው ( ዕብራውያን 4 ፥ 8 _ 10 ) ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment