Sunday, 8 October 2017

የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፫የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፫ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ? የሚለው የክፍል አስራ ስምንት እና የቊጥር 3 ትምህርትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ መጽሐፍቅዱሳችን አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም ነው የሚለን ዘፍጥረት 5 ፥ 5 በመሆኑም ከአዳም ሞት በኋላ የሴት ቤተሰብ ከቃየን ቤተሰብ ጋር ፈጥኖ የተለየ መሆኑን የአረብኛ የመጽሐፍቅዱስ መተርጉማን ተናግረዋል እነዚሁ መተርጉማን አያይዘው ሲናገሩ ሴት ልጆቹንና የልጆቹን ሚስቶች ይዞ ከፍ ወዳለው ተራራ ሔርሞን ወደ ተባለው አዳም ወደተቀበረበት ተራራ ሲሄድ ቃየን ደግሞ ልጆቹን ይዞ በሸለቆ ስር መኖር ጀመረ አቤልም ሲመለከት ንጹሕና ቅዱስ ተራራ አገኘ መላዕክት ድምጹን ሊሰሙት ቅርብ የሆኑበት ከመንፈሳዊ መዝሙሩም ጋር ሊገናኙ የሚያስችላቸው ቦታ ነበር ታድያ ልጆቹና የልጆቹ ሚስቶች በእግዚአብሔር ስም ወደሚጠሩበት ቦታ እንዲመጡ ፓትርያርክ ሴት ለምኗቸው ነበር እንደገናም ማንም ሰው ቃየንን ለማግኘት ከዚያ ተራራ የሚወርድ አልነበረም ነገር ግን ያም ቢሆን ጥቂቶች ከተራራው ወረዱ የቃየንን ቆነጃጅት ልጆች የልጅ ልጆቹን ወሰዷቸው እነርሱንም ተከተሏቸው የመረጧቸውንም ለሚስትነት ወሰዷቸው በጉልበት ግን አልነበረም ሕገወጥ በሆነ መንገድም ተጋቡ ማራኪና መልከ መልካም የሆኑትን ለሥጋቸው የሚያስደስታቸውን ያለ ምንም ምግባርና ጠባይ ያለ ምክርና የቤተሰብ ፈቃድ ያለ እግዚአብሔር ምክር ያስደሰቷቸውን ሴቶች ወሰዱ ቃየን ሱሰኛ በሆነበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ዓይነት ሳይጋቡ ፈጸሙ በመዝፈንና በመደነስ ጊዜአቸውን አጠፉ የሴት ዝርያዎች ወይም የእግዚአብሔር ልጆች ቆሻሻ የሆነው ስሜታቸው ምንድነው ? ስንል ወርደው የቃየንን ልጆች ተገናኟቸው ዝሙትንም ከእነርሱ ፈጸሙ ይለናል እንግዲህ የኤሎሂም ልጆች ዝነኛ የሆኑ የመንግሥተ ሰማያት ሰዎችና የሴት ቤተሰቦች ናቸው ታድያ የሴት ልጆች ጊዜ ወስደው የውሃው ጎርፍ ሊመጣ ባለበት ሰዓት ከቃየን ልጆች ጋር ተጋቡ የመጽሐፍቅዱሱም ጥቅስ ከዚህ የተነሳ የተጠቀሰ ነው የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 38 ፤ የሉቃስ ወንጌል 17 ፥ 27 እንደገናም ጋብቻን የሚከለክል የሚያግድ ትዕዛዝ እያለ በጋብቻ ተቀላቀሉ ዘጸአት 34 ፥ 16 ፤ ዘፍጥረት 26 ፥ 34 እና 35 ፤ ዘፍጥረት 27 ፥ 46 ፤ ዘፍጥረት 28 ፥ 1 ን እንመልከት በዘጸአት 6 ፥ 2 ላይ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ ይለናል በዘጸአት 6 ፥ 4 ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በድሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ ይለናል ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሰውን ሴቶች ልጆች ለራሳቸው ወስደው ያገቡት እግዚአብሔር ፈቅዶላቸውና ሴቶቹንም አጥንቶቻችሁና ሥጋዎቻችሁ ናቸው ብሎ ሰጥቷቸው ሳይሆን በዓይኖቻቸው ፊት መልካሞች እንደሆኑ አይተዋቸው መርጠዋቸውም ነው ይህ ዕይታና ምርጫ ደግሞ ቃየላዊ የሆነ ሚስትን የማየትና የመምረጥ ዕይታና ምርጫ ነው በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ቃየል ብቻ ሳይሆን የቃየል ዘሮችም ናቸው በዚሁ መንገድ ሚስቶቻቸውን መርጠው ያገቡት ይህ መንገድ ታድያ በዓይን አምሮት የተፈጸመ የጋብቻ ሥርዓት ስለሆነ እግዚአብሔር በዚህ ነገር የለበትም ይህንንም መንገድ ለጋብቻ አልተጠቀመም ደግሞም ሰዎች ይህንኑ የዓይን አምሮት መንገድ ተከትለው እንዲጋቡ አላመለከተም ወገኖቼ ሆይ ሰዎች በዚህ በዓይን አምሮት መንገድ ተጋብተው ልጅ እስከ መውለድ ድረስ ደርሰው ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ ማለት ልጆችን የወለዱ በመሆናቸው ደርሰው የታወቁ ኃያላን ሆነዋልና ጋብቻው በዓይን አምሮት የተፈጸመ ቢሆንም እንኳ በቃ መጋባታቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንደገናም እግዚአብሔር አዋቂ ስለሆነ ጋብቻውም ትክክል ነው ስንል ድምዳሜ ላይ መድረስ የለብንም አንድ ሰው ያልተፈቀደለትን ሴት አግብቶ ልጆች ስለተወለዱለት የታወቀና ኃያል ሆነ ማለት ትዳሩም ሆነ ልጆቹ ከእግዚአብሔር የተገኙ ናቸው እርሱም የተባረከና በትክክለኛ መንገድ ላይ የለ ሰው ነው ማለት አንችልም የዚህን ሰው ትክክለኛነትና ኃያል መሆን የሚገልጹ የተወለዱለት ልጆች አይደሉም ማንም ሰው እኮ በተሳሳተም መንገድ አግብቶ ይሄ ሊሆንለት ይችላል ስለዚህ መለኪያዎቹ እነዚህ ሊሆኑ ይገባል ማለት የለብንም ይገባልም ስንል ማሰብ የለብንም ይገባል ሲሉ ማሰብም ሆነ ያሰቡትንም ነገር ትክክል ነው ሲሉ ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ደግሞ በዚህ የጋብቻ ሂደት ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሄዱበት መንገድ ምንም ዓይነት ይሁን ንስሐ የማያስፈልገው በመሆኑ ትክክል ናቸውና በዚያው ይቀጥሉበት ማለታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይህ ብቻ አይደለም ሌሎችም ወደፊት በዚህ መንገድ መጥተው የሚጋቡ ቢኖሩ እንኳ የሚመጣባቸው ችግር የለም እያልን በመሆኑ ትውልድን ወደተሳሳተ መንገድ እየመራን ነውና አሁንም ከተጠያቂነት አንድንም እንዲህ ማድረጋችን ደግሞ ራሳችንንም ሆነ ሌላውን ማታለል የሆንብናልና ሌሎችም ንስሐ እንዲገቡ ተናግረን ራሳችንም ደግሞ በጊዜ ንስሐ ገብተን ትዳራችንን በዚሁ የንስሐ ሕይወት ካላስተካከልን በስተቀር ጋብቻን የሚከለክለውንና የሚያግደውን ትዕዛዝ ተላልፈን ልንጣመር ከማይገቡን ሰዎች ጋር ተጣምረን የተጋባን የተቀላቀልንም በመሆናችን ከዚህም ሌላ ሌሎችም መጥተውና በእኛው መንገድ ተጋብተው እንዲቀላቀሉ በማድረጋችን በፍጻሜው የምንከፍለው ዋጋ የከፋ ይሆናል ሚስትን መውሰድ በጠቅላላው የብሉይኪዳን ሕግ በእግዚአብሔርም የጋብቻ ግንኙነት ምሥረታ ሰዎች ስሜታቸውን በሚቀሰቅስ መንገድ ተነሳስተው በቀላሉ የውጫዊ ግንኙነት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረታቸውን የሚያደርጉበት ነው ይሁን እንጂ አሁንም እግዚአብሔር ይህንን መንገድ ለጋብቻ አልተጠቀመም ለዚህ ጉዳይ እነዚህን ጥቅሶች አሁንም ደግመን እንመልከታቸው ዘፍጥረት 26 ፥ 34 እና 35 ፤ ዘፍጥረት 27 ፥ 46 ፤ ዘፍጥረት 28 ፥ 1 ውድ ወገኖቼ ሆይ ለዚህ ትምህርት ማጠናከርያ እንዲሆን ከእንግሊዘኛው የመጽሐፍቅዱስ ኮመንታሪ የተወሰዱና በዚህም ትምህርት ውስጥ የተካተቱ ሃሳቦች ስላሉ ሃሳቡን በእንግሊዘኛውም አንብባችሁ መረዳት ለምትፈልጉ እንደሚከተለው ጽሑፉን አቅርቤላችኋለሁ አንብባችሁ ተባረኩበት Matthew Henry's Concise Commentary According to the Arabic writers (l), immediately after the death of Adam the family of Seth was separated from the family of Cain; Seth took his sons and their wives to a high mountain (Hermon), on the top of which Adam was buried, and Cain and all his sons lived in the valley beneath, where Abel was slain; and they on the mountain obtained a name for holiness and purity, and were so near the angels that they could hear their voices and join their hymns with them; and they, their wives and their children, went by the common name of the sons of God: and now these were adjured, by Seth and by succeeding patriarchs, by no means to go down from the mountain and join the Cainites; but notwithstanding in the times of Jared some did go down, it seems; See Gill on Genesis 5:20 and after that others, and at this time it became general; and being taken with the beauty of the daughters of Cain and his posterity, they did as follows: and they took them wives of all that they chose; not by force, as Aben Ezra and Ben Gersom interpret, for the Cainites being more numerous and powerful than they, it can hardly be thought that the one would attempt it, or the other suffer it; but they intermarried with them, which the Cainites might not be averse unto; they took to them wives as they fancied, which were pleasing to the flesh, without regard to their moral and civil character, and without the advice and consent of their parents, and without consulting God and his will in the matter; or they took women as they pleased, and were to their liking, and committed fornication, to which the Cainites were addicted; for they spent their time in singing and dancing, and in uncleanness, whereby the posterity of Seth or sons of God were allured to come down and join them, and commit fornication with them, as the Arabic writers (m) relate. Keil and Delitzsch Biblical Commentary on the Old Testament The question whether the "sons of Elohim" were celestial or terrestrial sons of God (angels or pious men of the family of Seth) can only be determined from the context, and from the substance of the passage itself, that is to say, from what is related respecting the conduct of the sons of God and its results. That the connection does not favour the idea of their being angels, is acknowledged even by those who adopt this view. "It cannot be denied," says Delitzsch, "that the connection of Genesis 6:1-8 with Genesis 4 necessitates the assumption, that such intermarriages (of the Sethite and Cainite families) did take place about the time of the flood (cf. Matthew 24:38; Luke 17:27); and the prohibition of mixed marriages under the law (Exodus 34:16; cf. Genesis 27:46; Genesis 28:1.) also favours the same idea." But this "assumption" is placed beyond all doubt, by what is here related of the sons of God. In Genesis 6:2 it is stated that "the sons of God saw the daughters of men, that they were fair; and they took them wives of all which they chose," i.e., of any with whose beauty they were charmed; and these wives bare children to them (Genesis 6:4). Now אשּׁה לקח (to take a wife) is a standing expression throughout the whole of the Old Testament for the marriage relation established by God at the creation, and is never applied to πορνεία, or the simple act of physical connection. ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment