Tuesday, 3 October 2017

የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር 2የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት እነማን ናቸው ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር 2 ባለፈው ትምህርታችን መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉበትን ምሥጢር በስፋት አንስተን የምንባባችን መነሻ ሃሳብ ባደረግነው በዘፍጥረት 6 ፥ 1 _ 4 መሠረት የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ ይላልና ምንም እንኳ መላዕክት በአንዳንድ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉ ቢሆኑም በዚህ ቦታ ላይ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት መላዕክት አለመሆናቸውን አየን ለምን ስንል በመላዕክት ዘንድ ማግባትና መጋባት የሌለ በመሆኑ መላዕክት የሰውን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን ለራሳቸው ያልወሰዱ መሆናቸውን የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት አድርገን በሰፊው ተመልክተናል ዛሬ ደግሞ ከዚሁ በተያያዘው ሃሳብ ተነስተን የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት መላዕክት ካልሆኑ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ በሰፊው በእግዚአብሔር ቃል ማብራርያነት እንመለከታለን የመጽሐፍቅዱስን ትርጉም ስንመለከት ታድያ ፦ 1ኛ ) እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የመሣፍንት ልጆች ናቸው የመሣፍንት ዘር ልዑል ፣ ልዕልት የሚለውን ትርጉም ይይዛል They were the noble and men of hig rank ኃያልና ጠንካራ ናቸው ዘጸአት 15 ፥ 11 ፤ ዘጸአት 12 ፥ 12 እንደገናም ፈራጆች መሆናቸውን ይነግረናል Where it is translated Judges ዘጸአት 22 ፥ 28 ፤ 1ኛ ሳሙኤል 2 ፥ 25 የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉ የተከበሩ የተደነቁ ልዑላን ወይም ባላባቶች ማለት ሲሆን በንግሥቷ ዙርያ ያሉ በዘላቂነት ጽኑ ኃያል የሆኑ ማለት ነው እንደገናም ኃያልና ጠንካራ የሆኑ የአምላክ ልጆች ማለት ነው ኢዮብ 1 ፥ 6 ፤ ኢዮብ 38 ፥ 7 ታድያ በዘፍጥረት 6 ፥ 1 እና 2 መሠረት ያገቧቸው የአምላክ ልጆች ከአዳም ልጆች ማለትም ከተመረጡት የሰው ሴቶች ልጆች ጋር በእርግጠኝነት ተመሣሣይነት አሏቸው እነዚህ የመሣፍንት ልጆች ዳኞች ፈራጆች ጠቃሚ የተባሉ የተከበሩ ሰዎች የሰውን ሴቶች ልጆች ሚስቶች ማድረጋቸው ይሄ ለእነርሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ወደ እነርሱ መመልከትና እነርሱን ለጋብቻ መውሰድ ወንጀል አይደለም ከእነርሱም ጋር ለዝሙት ውል መግባት ሃይማኖት አልባ ጋብቻ እንኩዋ ቢሆን እስካሁን ድረስ በከፊል ብቻ ነበር ዓለም አቀፍና በየትም ያለ ምግባረ ብልሹነት ወይም ውድቀት አልነበረም ነገር ግን በአቤል ምትክ የመጣው ሴት ይህንን የተረዳ በመሆኑ በሄኖስ ጊዜ አንድ ዓይነት ሰዎችን በእግዚአብሔር ስም ሊጠራ ጀመረ ዘፍጥረት 4 ፥ 25 ይህ ማለት የእግዚአብሔር ልጅና የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው This title manifestly relates to Genesis 4:26, where the same persons are said to be called by the name of the Lord, i.e. to be the sons and servants of God 2ኛ ) እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች በአቤል ፈንታ ከተወለደው ከሴት ጀምሮ የተወለዱ ናቸው እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ታድያ በደንብ የሚታዩ ታዋቂ የሆኑና ትልቅ ልህቀት ያላቸው አማልክት ተብለው ይጠራሉ ኃያል የሆኑ ልጆች ናቸው መዝሙር 82 ፥ 6 እግዚአብሔር ተጸጽቶባቸው አጠፋቸዋለሁ ካላቸውም በተቃራኒው ያሉ ሰዎች ናቸው ዘፍጥረት 6 ፥ 7 ሰዎቹም በአማካኝ በጣም የላቀ ነገር ያላቸው በባሕርያቸው የእግዚአብሔር መለያ ያላቸው እንደገናም ልዑል የተከበረና የተደነቀ ሰው በአጠቃላይ ሚስቶችን ወይም ሴቶችን ሊወስድ የሚችል አይሆንም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ስለሆኑ የሚፈርዱ የሚያለቅሱ ናቸው አለበለዚያም በኃጢአት የሚያለቅሱትን ሰዎች አይጠቅሱአቸውም እግዚአብሔር በሔዋን ልጅ በሴት መወለድ የተሟላ አስተያየት ለመስጠትና ለመሰየም ምክንያታዊ ነው ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በአቤል ፈንታ ለሔዋን ሴትን ሰጣት የእርስዋ ልጅ ሴት በዚህ ምክኛት ትኩረት የተሰጠው የእግዚአብሔር ልጅ ነው በሄኖስ የልደቱ ጊዜም በእግዚአብሔር ስም የመጠራት ልማድ ነበረው ዘፍጥረት 4 ፥ 26 ስለዚህ በአዳም ቤተሰብ ዙርያ ጥርጥር አልነበረም ሴት የተባለው ቀጥሎ እየኖረ ነውና በአዳም መስመር ላይ ሄኖክ ሰባተኛ ነው ደማቅና ምሳሌያዊ የሆነ እውነተኛ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር እየሄደና እየኖረ ነው በሴት ተወላጅ መሐል እግዚአብሔር ወርቃማ ቃሎችን ተናግሮአል እንደገናም ኖህ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአል ስለዚህም በተፈጥሮ የሽግጝር ወቅት ምክንያት የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል በአምላካዊ የሥነምግባር ሕግ ስሜትም ከመንፈስ ተወልደዋል ከመንፈስ መወለድ በኋላ በሥጋ ከእግዚአብሔር ጋር አልሄዱም መዝሙር 82 ፥ 6 ፤ ሆሴዕ 2 ፥ 1 ለዚህም ነው ከኖህ ጋራ ዳግመኛ ምድርን እንዳያጠፋ እንዳይረግማትም እግዚአብሔር ቃልኪዳን ያደረገው ኖህ በትውልዱ ጻድቅ ነበረ እንደገናም ኖህ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝቶ ነበረ ከጥፋትም ውሃ እርሱ ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ መርከቡ በእምነት ታዞ ስለገባ ድኅነት ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ሆነ 3ኛ ) የእግዚአብሔር ልጆች ከእግዚአብሔር ጎን የቆሙ ናቸው በየጊዜው ትርጉም በሚሰጥ ዘዴ በየጊዜው የሚያቀርቡ በእርሱ በተከበረው ስም የሚጠሩ በየቀኑ ባለ ንግጝር እና ጭውውት ከእጝዚአብሔር ጋር የሚሄዱ ናቸው በዘይቤያዊ ወይንም ምሳሌያዊ አነጋገር የልጅ ጥቅሙ በልዩ ልዩ ዓይነት አድራጎት መገናኘትን የሚያመለክት ነው ከእግዚአብሔር ጎን ቆሙ የተባሉትም ሰዎች ሀ ) ኖህ ለ ) አብርሐም ሐ) የሞተችዋ ራሔልና የእርሱ አባት ናቸው ዘፍጥረት 5 ፥ 32 ፣ ዘፍጥረት 15 ፥ 3 ፣ ዘፍጥረት 35 ፥ 18 The sons of God, therefore, are those who are on the Lord's side, who approach him with duly significant offerings, who call upon him by his proper name, and who walk with God in their daily conversation. The figurative use of the word "son" to denote a variety of relations incidental, and moral as well as natural, was not unfamiliar to the early speaker. Thus, Noah is called "the son of five hundred years" Genesis 5:32. Abraham calls Eliezer בן־בותי ben-bēytı̂y, "son of my house" Genesis 15:3. The dying Rachel names her son Ben-oni, "son of my sorrow," while his father called him Benjamin, "son of thy right hand" Genesis 35:18. ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment