ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የትምህርት ርዕስ
መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ
ሰኞ ማለዳ 10 ሰዓት ላይ የሚጀምር ለኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችና ለወንጌላውያን አማኞች እንዲሁም አገልጋዮቻቸውም ጭምር የሚሰጥ ትምህርት ነው ከዚህም ሌላ ይህንን ትምህርት በናፍቆት ሊከታተሉ ለሚወዱ ሁሉ ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑ ማንም ሰው ሊከታተለውና ሊሰማው የሚያስፈልገው ለተከታታይ ሳምንታት የሚሰጥ ተከታታይ ትምህርት ነው
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን እስካሁን ድረስ ከዚህ አገልግሎት ጋር ቆማችሁ የዚህ አገልግሎት ተካፋዮች እና ተጠቃሚዎች ስለሆናችሁ እንደገናም ለዚህ አገልግሎት መሳካት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ስላደረጋችሁ ጌታ አምላክ ዘመናችሁን ይባርክ እያልኩ ሰኞ በሚኖረን የፌስቡክ ላይቭ አገልግሎት እንደተነጋገርነው አዲስ ትምህርት የምንጀምርበት ጊዜ ነው መንፈሳዊ የሕይወት ተሃዶሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ምን እንደሚመስል ከመጽሐፍቅዱሳችን አስረጂ በማቅረብ በተለይም መንፈሳዊ ተሃድሶን በሰዎች ሕይወት ላይም ሆነ በቤተክርስቲያን ያመጡ ሰዎችን ከመጽሐፍቅዱሳችን እንመለከታቸዋለን እንደገናም በዚህ ውስጥ ቤተክርስቲያን ምን ትምሰል ? የሚል መጠይቅን ይዘን እንቀርባለን ከዚህም ሌላ ተሃድሶ በኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን መቼ ተጀመረ ?ቤተክርስቲያኒቱም ክርስትናን አንድ ብላ ከተቀበለችበትና ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የነበራት መንፈሳዊ አቋምና መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ምን እንደነበረ እንመለከታለን እንደገናም ከዚህ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል መረዳቷ የቱ ጋር እንደወጣችና እንደለቀቀች ከታሪክም ሆነ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት አጣቅሰን መረጃም ሰብስበን እንመለከታለን የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ ሰፋ ያሉ እውነቶችንና የእግዚአብሔር ቃል መረዳቶችን ይዞ የቀረበ ስለሆነ እናንተም ሰፋ ብላችሁና ማስታወሻ ደብተሮቻችሁንም አዘጋጅታችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑ ሰዎችንም ወደዚሁ የትምህርት ፕሮግራም በሰዓቱ ተገኝተው እንዲካፈሉ ጋብዟቸው ትምህርቱ እንደሚታወቀውበፌስቡክ ላይቭ የሚጀምረው በእኔ የሰዓት አቆጣጠር 10 AM ማለዳ ላይ ነው ሁልጊዜ ሰኞና ሐሙስ በዚህ ሰዓት ተዘጋጅቶ ይቀርብላችኋል በተረፈ በክርስቶስ ፍቅር በጣም እወዳችኋለሁ አከብራችኋላሁ ዘመናችሁ የተባረከ ይሁን በሰዓታችንና በቀጠሯችንም እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ በማለት የምሰናበታችሁ
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
God bless u all
yonasasfaw8@gmail.com
ፈጣን ተሐድሶ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ለዚህ ሥዕላዊ መጠይቅ መጽሐፍቅዱሳዊ መልሳችን
ተሐድሶ ያስፈልገኛል ስትል ወንጌልን አምና የተቀበለች ቤተክርስቲያን በአዲስ ፍጥረት ማንነት ትታደሳለች እንጂ አትጠፋም
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥ 17 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 23 ፤ የያዕቆብ መልዕክት 1 ፥ 18 እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል ይመልከቱ
No comments:
Post a Comment