Thursday, 20 April 2017
የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ( ክፍል ስድስት )የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ( ክፍል ስድስት ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ስንል በዛሬው ትምህርታችን እስራኤል በኪዳናቸው ያልጸኑበትን ሁለተኛውን የሕጉን ነገር በሰፊው እንመለከታለን ስለዚህ ሕጉ ምንም እንኳ ቅዱስና መልካም በጎና ጻድቅት ቢሆንም ሮሜ 7 ፥ 12 _ 13 ሰዎችን ግን ፍጹም ማድረግ አልቻለም ይህ ማለት ደግሞ ሕጉ በመተላለፍ ኃጢአት የሚሠሩትን ሁሉ ሊያጸድቃቸው ወይም ሕጉ የሚጠይቀውን ሁሉ ለመፈጸም የሚያስችል ኃይል ሊሰጠቸው አልቻለም ማለታችን ነው በዚህም ምክንያት ታድያ ሕጉን በተመለከተ ሐዋርያው አሁንም ስለ ሕጉ ሲናገር የምትደክም የማትጠቅም ስለሆነች የቀደመች ትዕዛዝ ተሽራለች አለን ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) እንደገናም ሕጉን በተመለከተ ሐዋርያው በድጋሜ ከእግዚአብሔር የተሰጠና ትክክለኛ መሆኑን ሊጠቁመን አሁንም ስለዚሁ ስለ ሕግ ወደ ሰባት የሚደርሱ ነጥቦችን ነገረን እነርሱም ፦ 1ኛ ) ሕግ ኃጢአት አይደለም ( ሮሜ 7 ፥ 7 _ 9 ) 2ኛ ) ለሕይወት የተሰጠ ትዕዛዝ ነው ( ሮሜ 7 ፥ 10 ) 3ኛ ) ሕጉ ቅዱስ ትዕዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት ( ሮሜ 7 ፥ 12 ) 4ኛ ) ሕግ መንፈሳዊ እንደሆነ እናውቃለን ( ሮሜ 7 ፥ 14 ) 5ኛ ) ሕግ መልካም እንደሆነ እመሰክራለሁ ( ሮሜ 7 ፥ 16 ) 6ኛ ) በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛ ( ሮሜ 7 ፥ 22-24 ) 7ኛ ) በአዕምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ ( ሮሜ 7 ፥ 25 ) አለን ታድያ ከቁጥር 1 _ 7 የተጠቀሱትን እና ደረጃ በደረጃ የዘረዘርኳቸውን ሃሳቦች ለመረዳት ሮሜ 7 ፥ 7_ ፍጻሜ የተጻፈን ሃሳብ ለተጨማሪ መረጃ ብናነብ ይበልጥ እንረዳለን ከእነዚህ እና ከመሣሠሉት እውነቶች የተነሳም የብሉይ ኪዳኑ ሕግ ሰዎችን ማጽደቅ እና ፍጹምም ማድረግ ባይችልም ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል ለዚህም ነው ሐዋርያው አሁን ካለንበት ሁኔታ ጋር አያይዞ እምነት ግን መጥቶአል ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም ሲል የነገረን ገላትያ 3 ፥ 23 _ 25 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 5 ፥ 17 በምናነበውም ሆነ በዚህ በምንሰማው የቪዲዮ ትምህርት እግዚአብሔር ይባርከን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment