Saturday, 15 April 2017
ክፍል አንድ፦ የታቦቱ ምስጢር ፣ ታቦት ምንድነው ? በአብና በወልድ በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በማለት ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ በመቀጠልም በዛሬው ዕለት ታቦት በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትምህርት ዛሬ ጀምሬአለሁ ታድያ የዛሬው ንዑስ አርዕስት ፦ ክፍል አንድ፦ የታቦቱ ምስጢር ፣ ታቦት ምንድነው ? የሚል ነው ታቦት ምንድነው ? በሚል ሃሳብ በቀረበው ትምህርት መሠረት ታቦት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን የገባበትና ውልንም የፈጸመ በመሆኑ የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ኪዳን የገባበትና ይህንኑ ውል የፈጸመበትን ኪዳን ኪዳኑ በማድረግ ራሱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባው ፣ የራሱም የእግዚአብሔር ኪዳን በመሆኑ የእግዚአብሔርን ኪዳን አምናና የእግዚአብሔርንም ቃል መሠረት አድርጋ 10ቱ ቃላት እለ ተጽሕፋ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር በማለት ተናገረች ትርጉም 10ቱ ቃላት በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ናቸው ማለትን የሚያመለክት ነው ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት ) ፤ ዘጸአት 31 ፥ 34 ፤ ዘጸአት 34 ፥ 27 እና 28 ታድያ ይህንኑ እውነት ተከትሎም ፦ 1ኛ) በመጽሐፍቅዱሳችን ውስጥ ሰባት ኪዳናት መኖራቸውን 2ኛ ) የታቦቱ ኪዳን ከሰባቱ አንዱ የሆነና የሙሴ ኪዳን መሆኑ 3ኛ ) ጌታ እግዚአብሔር ሙሴን ከግራር እንጨት ታቦት እንዲሰራና ከሕዝቡም ጋር በመሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ያድር ዘንድ መቅደስ እንዲሰሩ መጠየቁ 4ኛ ) በዚህ ውስጥ የሙሴም ሆነ የእስራኤል የኪዳናቸው መሠረት የበግ ደም መሆኑን ተመልክተናል 5ኛ ) አያይዘንም ዛሬ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ሕጉ በታቦቱ ላይ ሳይሆን በልባችን ላይ የተጻፈ በመሆኑ የኪዳናችን መሠረት የክርስቶስ ደም ነው ይህ ደም ደግሞ ቅዱስ ሕዝብና ለርስቱም የተለየን ወገን የንጉሥ ካህናትም አድርጎናል ታድያ ይህ ደም አሁንም እንደ ብሉይ ኪዳኑ ዘመን የበግ ፣ የፍየል ወይም የኮርማዎች ደም ዓይነት ሆኖ የፈሰሰልንሳይሆንብቸኛው የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ሆኖ የፈሰሰልን ስለሆነ ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስና ለርስቱም የተለየ ወገን ቅዱስ ሕዝብም መሆናችንን አብስሮናል ትምህርቱም ይህንን እውነት በሰፊው ያብራራል ፣ ይተነትናል ቪዲዮውን ተከታተሉት ትባረኩበታላች ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment