Tuesday, 18 April 2017

የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው ( ክፍል አምስት )የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው ( ክፍል አምስት ) ጌታ እግዚአብሔር ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ……………… እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና ቸል አልኳቸው ይላል ጌታ ይላልና ኤርምያስ 31 ፥ 31 _ 34 ፤ ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 13 1ኛ ) ጌታ ለምን አዲስኪዳን መግባት አስፈለገው ? 2ኛ ) ስለምንስ የእስራኤል ቤት በኪዳኑ ሳይጸኑ ቀሩ ? በሚለው ሃሳብ ዙርያ በቊጥር አንድ በቀረበው መጠይቅ መሠረት ጌታ አዲስ ኪዳን መግባት ያስፈለገው አሁንም ስለሁለት ምክንያቶች እንደሆነ የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል እርሱም 1ኛ ) በዕብራውያን 8 ፥ 6 መሠረት አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቷል ይለናል 2ኛ ) ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው ለሁለተኛው ሥፍራ ባልተፈለገ ነበር ስለሚል በእነዚህ በሁለት ሃሳቦች ምክንያት ጌታ እግዚአብሔር ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል በማለት ሐዲሱን ኪዳን ገባ ይሁን እንጂ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና ቸል አልኳቸው የሚል የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈልን በመሆኑ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት አሁንም ስለ ሁለት ነገር ነው እርሱም 1ኛ ) በክህነቱ 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ይለናልና ለዛሬ በኪዳኑ ያልጸኑበትን የክህነቱን ምክንያት በሰፊውና በዝርዝር ተማምረናል በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን የሕጉን ምክንያት በሰፊው እንማማራለን ቪዲዮውን ተመልከቱት ትባረኩበታላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment