Monday, 24 April 2017

ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) ክፍል ሰባትወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) ክፍል ሰባት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ዛሬ የክፍል ሰባት ትምህርታችን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል የሚል ነው ይሄ የሚሻል ተስፋ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ የሆነበት አዲሱ ኪዳናችን ነው ( ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 12 ፤ ኤርምያስ 31 ፥ 31 _ 34 ) ይመልከቱ ታድያ ይሄ አዲሱ ኪዳናችን ጌታ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ( በዘጸአት 24 ፥ 7 _ 8 ) ከተጻፈልን በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠው ኪዳን ይበልጣል የተመሠረተውም በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው ( ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 12 ፤ ዕብራውያን 12 ፥ 24 ፤ ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) በብሉይ ኪዳኑ ኪዳን የተጻፈልን አልደረሳችሁምና የሚል ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ በሆነበት በሐዲሱ ኪዳናችን ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ………… ደርሳችኋል የሚል ተጽፎልናል በመሆኑም ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ መጥቶአል ማለታችን ከዚህ እውነት ተነስተን ነው ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ይሄ ኪዳን መብለጡና የተሻለ መባሉ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ወደ አምስት የሚደርሱ ነጥቦች አሉ ለዛሬ የተመለከትናቸው ሁለቱን ነጥቦች ሲሆን በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜያችን ከእነዚህ የቀጠሉትን ሦስቱን ነጥቦች እንደሚከተለው በየተራ እንመለከታቸዋለን አምስቱ ነጥቦችም እንዲህ የሚሉ ናቸው 1ኛ ) የእግዚአብሔር ሕግ የልብና የሕሊና መርህ ሆኖ በመምጣቱ 2ኛ ) ሕዝቡ ፈቃዱን በመፈጸሙ ደስ የሚሰኝበት በመሆኑ 3ኛ ) እግዚአብሔርን ያለማወቅ ኃጢአት ለዘላለም ይወገዳል 4ኛ ) በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ጥብቅ ግንኙነት የተደረገ እና ወደፊትም በብዙዎች ሕይወት የሚደረግ በመሆኑ 5ኛ ) የኃጢአት ይቅርታ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር እውነት ሆኖአል የተወደዳችሁ ወገኖች ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ የሆነበት አዲሱ ኪዳናችን በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠው ኪዳን ይልቅ መሻሉና መብለጡ ከእነዚህ እውነቶች የተነሳ ነው የትምህርቱ ጠቅላላ ሃሳብ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ቪዲዮውን ስሙት ተባረኩበት ለሌሎችም ሰዎች ሼር አድርጉት በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የቀረውን እቀጥላለሁ እስከዚያው ሰላም ሁኑ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

Friday, 21 April 2017

ስለ ታቦት እየተሰጠ ላለ ተከታታይ ትምህርት ለአድማጮችና ለትምህርቱ ተከታታዮች የተነገረ ማሳሰብያስለ ታቦት እየተሰጠ ላለ ተከታታይ ትምህርት ለአድማጮችና ለትምህርቱ ተከታታዮች የተነገረ ማሳሰብያ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ስለ ታቦት እየተማማርን በእግዚአብሔር እርዳታና በእናንተም ጸሎት ክፍል ስድስት ላይ ደርሰናል ትምህርቱ አሁንም ይቀጥላል ትከታተሉ ዘንድ የዘወትር ጥሪዬና መልዕክቴም ነው ነገር ግን በዚሁ የታቦት ትምህርት ላይ ያልገባችሁና ልትጠይቁት የምትፈልጉት ነገር ቢኖር በውስጥ መስመር ልታነጋግሩኝ የምትችሉ መሆናችሁን ለማሳሰብ እወዳለሁ ትምህርቱንም ሌሎች ሰምተውት እንዲጠቀሙ ሼር በማድረግ እየተባበራችሁ ያላችሁ ወገኖች ጌታ ይባርካችሁ ልላችሁ እወዳለሁ የእግዚአብሔርን ሥራ አብረን እየሰራን ስለሆነ ሼር ማድረጉን ቀጥሉበት እላችኋለሁ ይህን መዝሙር እየሰማችሁ እንድትባረኩም የእህታችንን የዘርፌ ከበደን መዝሙር ጋብዣችኋለሁ ሰኞ ማለዳ ላይ በሚኖረን የዚሁ ተከታታይ ትምህርት አገልግሎት እስክንገናኝ ሁላችሁንም ተባረኩ በማለት የምሰናበታችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

Thursday, 20 April 2017

በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ...በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ክፍል አራት ) 1ኛ ) ቤተክርስቲያኒቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን የነገሠ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ማስረጃ ስትሰጥ ቀዳሚሁ ቃል እንዲል ስተረጉመው በመጀመርያ ቃል ነበረ ይለናልና ከአብ ጋር በቅድምና በቃልነት ይመሰገን የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ለብሶ ፣ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ ቢሆንም እነዚያ ስሞች ከስመ ሥጋዌው ማለትም ከሥጋዌ ስሙ የሚቀድሙ ስሞች በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ዋነኛ ማስረጃዎቻችንና ጠቋሚዎቻችን ናቸው ይለናል ትምህርቱ ስሞቹም ሆኑ የትዕዛዛቱ ምስጢራት በቪዲዮ ላይ የተብራሩ ስለሆኑ ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን መስማቱ ይበልጥ ይጠቅማል 2ኛ ) የውጣ ጥንታዊ የግሪክ ቋንቋና አስረኛ ቁጥር ስለሆነች እዝል ፣ ቅጽል የሌላት እንደ ጭራ የቀጠነች በአጻጻፍም ትንሽና ቀጭን በመሆንዋ የአብ ባሕርያዊ ቃል የሆነው ኢየሱስ በአጽባዕተ መንፈስቅዱስ ማለትም በመንፈስቅዱስ ጣቶች ፣ በመንፈስቅዱስ አሠራር በድንግል ማኅጸን እንዲቀረጽ አሰርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ በማኖር ነገረን በማለት ከዚያም መልስ ከመወለዱ ጀምሮ ባለ አስተዳደጉ ሁሉ በዮሴፍ ቤት ኢየሱስ ለአባትና ለእናቱ እየታዘዛቸው ያደገ በመሆኑ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በመንፈስቅዱስ ምክር ቀርጻ ያሳደገችው መሆኑን ትምህርቱ ይጠቁመናል 3ኛ ) ጽላቱ ከተሰበረ በኋላም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ፊተኞቹ አድርገህ እነዚህን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጥረብ በማለት በሰበርሃቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ ሲል መናገሩ ምሳሌነቱ ቃሉ የጌታ ምሳሌ በድንጋይ ጽላቶች ላይ የሚጻፉ ቃሎች ከእግዚአብሔር አፍ የወጡ እንደመሆናቸው ሁሉ ጌታችን ኢየሱስም በግብረ አምላካዊና በመንፈስቅዱስ የተገኘ የተጸነሰና የተወለደ መሆኑን እንደገናም ይሄ ጌታ በመንፈስቅዱስ አማካኝነት የተወለደ በመሆኑ በወንድና በሴት የግንኙነት ፈቃድ የተገኘ ወይም የተወለደ ባለመሆኑ እንበለ ዘር የተገኘ ነው ስትል ቤተክርስቲያኒቱ ርቱዕ በሆነው ትምህርቷ ታመሰጥራለች ትናገራለች 4ኛ ) ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን በማለትም የሰንበት ውዳሴ ማርያምን ለአብነት ጠቅሳ ደሙን በማፍሰስ እና በደሙም በማንጻት የእርሱ የሆኑትን አማኞች ለእግዚአብሔር መንግሥትና ለመንግስተ ሰማያት ያበቃ ወደፊትም የሚያበቃ እውነተኛው የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ኢየሱስ መሆኑንም በደስታ ታበስረናለች እነዚህን ማብራርያዎች የጻፍኩት በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት በመስማት የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራችሁና እንድትወዱትም ጭምር ለመርዳት ያዘጋጀሁት ነውና አንብቡት ቪዲዮውንም ስሙት ፣ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ( ክፍል ስድስት )የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ( ክፍል ስድስት ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ስንል በዛሬው ትምህርታችን እስራኤል በኪዳናቸው ያልጸኑበትን ሁለተኛውን የሕጉን ነገር በሰፊው እንመለከታለን ስለዚህ ሕጉ ምንም እንኳ ቅዱስና መልካም በጎና ጻድቅት ቢሆንም ሮሜ 7 ፥ 12 _ 13 ሰዎችን ግን ፍጹም ማድረግ አልቻለም ይህ ማለት ደግሞ ሕጉ በመተላለፍ ኃጢአት የሚሠሩትን ሁሉ ሊያጸድቃቸው ወይም ሕጉ የሚጠይቀውን ሁሉ ለመፈጸም የሚያስችል ኃይል ሊሰጠቸው አልቻለም ማለታችን ነው በዚህም ምክንያት ታድያ ሕጉን በተመለከተ ሐዋርያው አሁንም ስለ ሕጉ ሲናገር የምትደክም የማትጠቅም ስለሆነች የቀደመች ትዕዛዝ ተሽራለች አለን ( ዕብራውያን 7 ፥ 19 ) እንደገናም ሕጉን በተመለከተ ሐዋርያው በድጋሜ ከእግዚአብሔር የተሰጠና ትክክለኛ መሆኑን ሊጠቁመን አሁንም ስለዚሁ ስለ ሕግ ወደ ሰባት የሚደርሱ ነጥቦችን ነገረን እነርሱም ፦ 1ኛ ) ሕግ ኃጢአት አይደለም ( ሮሜ 7 ፥ 7 _ 9 ) 2ኛ ) ለሕይወት የተሰጠ ትዕዛዝ ነው ( ሮሜ 7 ፥ 10 ) 3ኛ ) ሕጉ ቅዱስ ትዕዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት ( ሮሜ 7 ፥ 12 ) 4ኛ ) ሕግ መንፈሳዊ እንደሆነ እናውቃለን ( ሮሜ 7 ፥ 14 ) 5ኛ ) ሕግ መልካም እንደሆነ እመሰክራለሁ ( ሮሜ 7 ፥ 16 ) 6ኛ ) በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛ ( ሮሜ 7 ፥ 22-24 ) 7ኛ ) በአዕምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ ( ሮሜ 7 ፥ 25 ) አለን ታድያ ከቁጥር 1 _ 7 የተጠቀሱትን እና ደረጃ በደረጃ የዘረዘርኳቸውን ሃሳቦች ለመረዳት ሮሜ 7 ፥ 7_ ፍጻሜ የተጻፈን ሃሳብ ለተጨማሪ መረጃ ብናነብ ይበልጥ እንረዳለን ከእነዚህ እና ከመሣሠሉት እውነቶች የተነሳም የብሉይ ኪዳኑ ሕግ ሰዎችን ማጽደቅ እና ፍጹምም ማድረግ ባይችልም ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል ለዚህም ነው ሐዋርያው አሁን ካለንበት ሁኔታ ጋር አያይዞ እምነት ግን መጥቶአል ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም ሲል የነገረን ገላትያ 3 ፥ 23 _ 25 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 5 ፥ 17 በምናነበውም ሆነ በዚህ በምንሰማው የቪዲዮ ትምህርት እግዚአብሔር ይባርከን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday, 18 April 2017

Related image

የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው ( ክፍል አምስት )የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት 1ኛ ) በክህነቱ ምክንያት ነው ( ክፍል አምስት ) ጌታ እግዚአብሔር ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ……………… እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና ቸል አልኳቸው ይላል ጌታ ይላልና ኤርምያስ 31 ፥ 31 _ 34 ፤ ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 13 1ኛ ) ጌታ ለምን አዲስኪዳን መግባት አስፈለገው ? 2ኛ ) ስለምንስ የእስራኤል ቤት በኪዳኑ ሳይጸኑ ቀሩ ? በሚለው ሃሳብ ዙርያ በቊጥር አንድ በቀረበው መጠይቅ መሠረት ጌታ አዲስ ኪዳን መግባት ያስፈለገው አሁንም ስለሁለት ምክንያቶች እንደሆነ የክፍሉ ሃሳብ ያስተምረናል እርሱም 1ኛ ) በዕብራውያን 8 ፥ 6 መሠረት አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቷል ይለናል 2ኛ ) ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው ለሁለተኛው ሥፍራ ባልተፈለገ ነበር ስለሚል በእነዚህ በሁለት ሃሳቦች ምክንያት ጌታ እግዚአብሔር ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል በማለት ሐዲሱን ኪዳን ገባ ይሁን እንጂ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና ቸል አልኳቸው የሚል የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈልን በመሆኑ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በኪዳኑ ያልጸኑበት ምክንያት አሁንም ስለ ሁለት ነገር ነው እርሱም 1ኛ ) በክህነቱ 2ኛ ) በሕጉ ምክንያት ነው ይለናልና ለዛሬ በኪዳኑ ያልጸኑበትን የክህነቱን ምክንያት በሰፊውና በዝርዝር ተማምረናል በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን የሕጉን ምክንያት በሰፊው እንማማራለን ቪዲዮውን ተመልከቱት ትባረኩበታላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

Saturday, 15 April 2017

በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ...በሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ለመሆኑ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸው ማስረጃዎች ( ክፍል አራት ) 1ኛ ) ቤተክርስቲያኒቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን የነገሠ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ማስረጃ ስትሰጥ ቀዳሚሁ ቃል እንዲል ስተረጉመው በመጀመርያ ቃል ነበረ ይለናልና ከአብ ጋር በቅድምና በቃልነት ይመሰገን የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ለብሶ ፣ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ ቢሆንም እነዚያ ስሞች ከስመ ሥጋዌው ማለትም ከሥጋዌ ስሙ የሚቀድሙ ስሞች በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ለመሆኑ ዋነኛ ማስረጃዎቻችንና ጠቋሚዎቻችን ናቸው ይለናል ትምህርቱ ስሞቹም ሆኑ የትዕዛዛቱ ምስጢራት በቪዲዮ ላይ የተብራሩ ስለሆኑ ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን መስማቱ ይበልጥ ይጠቅማል 2ኛ ) የውጣ ጥንታዊ የግሪክ ቋንቋና አስረኛ ቁጥር ስለሆነች እዝል ፣ ቅጽል የሌላት እንደ ጭራ የቀጠነች በአጻጻፍም ትንሽና ቀጭን በመሆንዋ የአብ ባሕርያዊ ቃል የሆነው ኢየሱስ በአጽባዕተ መንፈስቅዱስ ማለትም በመንፈስቅዱስ ጣቶች ፣ በመንፈስቅዱስ አሠራር በድንግል ማኅጸን እንዲቀረጽ አሰርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ በማኖር ነገረን በማለት ከዚያም መልስ ከመወለዱ ጀምሮ ባለ አስተዳደጉ ሁሉ በዮሴፍ ቤት ኢየሱስ ለአባትና ለእናቱ እየታዘዛቸው ያደገ በመሆኑ ድንግል ማርያም ኢየሱስን በመንፈስቅዱስ ምክር ቀርጻ ያሳደገችው መሆኑን ትምህርቱ ይጠቁመናል 3ኛ ) ጽላቱ ከተሰበረ በኋላም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ፊተኞቹ አድርገህ እነዚህን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጥረብ በማለት በሰበርሃቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ ሲል መናገሩ ምሳሌነቱ ቃሉ የጌታ ምሳሌ በድንጋይ ጽላቶች ላይ የሚጻፉ ቃሎች ከእግዚአብሔር አፍ የወጡ እንደመሆናቸው ሁሉ ጌታችን ኢየሱስም በግብረ አምላካዊና በመንፈስቅዱስ የተገኘ የተጸነሰና የተወለደ መሆኑን እንደገናም ይሄ ጌታ በመንፈስቅዱስ አማካኝነት የተወለደ በመሆኑ በወንድና በሴት የግንኙነት ፈቃድ የተገኘ ወይም የተወለደ ባለመሆኑ እንበለ ዘር የተገኘ ነው ስትል ቤተክርስቲያኒቱ ርቱዕ በሆነው ትምህርቷ ታመሰጥራለች ትናገራለች 4ኛ ) ወኮነ አራቄ ለሐዲስ ኪዳን በማለትም የሰንበት ውዳሴ ማርያምን ለአብነት ጠቅሳ ደሙን በማፍሰስ እና በደሙም በማንጻት የእርሱ የሆኑትን አማኞች ለእግዚአብሔር መንግሥትና ለመንግስተ ሰማያት ያበቃ ወደፊትም የሚያበቃ እውነተኛው የሐዲስ ኪዳን አስታራቂያችን ኢየሱስ መሆኑንም በደስታ ታበስረናለች እነዚህን ማብራርያዎች የጻፍኩት በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት በመስማት የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራችሁና እንድትወዱትም ጭምር ለመርዳት ያዘጋጀሁት ነውና አንብቡት ቪዲዮውንም ስሙት ፣ ተባረኩበት ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

የታቦቱ አገልግሎት ( ክፍል ሦስት ) የታቦቱ አገልግሎት ክፍል ሦስት በክፍል ሦስት ትምህርት የታቦቱ አገልግሎት በሚል ንዑስ አርዕስት የተነሳሁ ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥ ፦ 1ኛ ) ታቦቱን በተመለከተ አሰርቱ ቃላት የተጻፈባቸው የሁለቱ ጽላቶች ማኖርያ መሆኑ 2ኛ ) ከእስራኤል መሪዎች ጋር የእግዚአብሔር መገናኛ ነበር 3ኛ ) በዚህም ምክንያት ታቦቱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር 4ኛ ) ሙሴም ታቦቱን አሰርቶ ሲያበቃ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አኖረው የእስራኤልም ሕዝብ ይዘውት ይጓዙ ነበር ይለናል 5ኛ ) ታቦቱ ወኪል የሆነና ሲንቦሊዝም የሆነ በመሆኑ የእስራኤል ጦረኞች በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ የያህዌ መገኘትና ምልክት ነበር 6ኛ ) አሁንም ታቦቱ ምስክርነቱን የሚያሳይና የተሰየመም በመሆኑ በመሠረታዊው ዓላማ ምክንያት ሀ ) የያህዌ ታቦት መሆኑን ለ ) የቃል ኪዳን ታቦት መሆኑን ሐ ) የጥንካሬው ታቦት መሆኑን የሚያሳይ ነው እነዚህን ሃሳቦች ይዘን ወደ ሐዲሱ ኪዳን የኪዳን አገልግሎት ስንመጣ ከቊጥር 1 እስከ 6 በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደሙ የኪዳናችን መሠረት በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኛችን ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመኖሩ ምልክታችን ፣ ይዘነው የምንጓዘው ታቦታችን ፣ የእግዚአብሔር ጉብኝቱ እና መገኘቱ የታየበት ምልክታችን ፣ እግዚአብሔር የተናገረበት ድምጻችንና የቃልኪዳን ታቦታችን እንዲሁም የጥንካሬ ኃይል የተገለጠበት በመሆኑም የጥንካሬው ኃይላችንና ታቦታችን ነው ትምህርቱ በአጭሩ እነዚህን ሃሳቦች በሙሉ ይጠቀልላል በትምህርቱ እንዲባረኩ ቪዲዮውን አዳምጡ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

ክፍል አንድ፦ የታቦቱ ምስጢር ፣ ታቦት ምንድነው ? በአብና በወልድ በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በማለት ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ በመቀጠልም በዛሬው ዕለት ታቦት በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትምህርት ዛሬ ጀምሬአለሁ ታድያ የዛሬው ንዑስ አርዕስት ፦ ክፍል አንድ፦ የታቦቱ ምስጢር ፣ ታቦት ምንድነው ? የሚል ነው ታቦት ምንድነው ? በሚል ሃሳብ በቀረበው ትምህርት መሠረት ታቦት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን የገባበትና ውልንም የፈጸመ በመሆኑ የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ኪዳን የገባበትና ይህንኑ ውል የፈጸመበትን ኪዳን ኪዳኑ በማድረግ ራሱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባው ፣ የራሱም የእግዚአብሔር ኪዳን በመሆኑ የእግዚአብሔርን ኪዳን አምናና የእግዚአብሔርንም ቃል መሠረት አድርጋ 10ቱ ቃላት እለ ተጽሕፋ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር በማለት ተናገረች ትርጉም 10ቱ ቃላት በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ናቸው ማለትን የሚያመለክት ነው ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት ) ፤ ዘጸአት 31 ፥ 34 ፤ ዘጸአት 34 ፥ 27 እና 28 ታድያ ይህንኑ እውነት ተከትሎም ፦ 1ኛ) በመጽሐፍቅዱሳችን ውስጥ ሰባት ኪዳናት መኖራቸውን 2ኛ ) የታቦቱ ኪዳን ከሰባቱ አንዱ የሆነና የሙሴ ኪዳን መሆኑ 3ኛ ) ጌታ እግዚአብሔር ሙሴን ከግራር እንጨት ታቦት እንዲሰራና ከሕዝቡም ጋር በመሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ያድር ዘንድ መቅደስ እንዲሰሩ መጠየቁ 4ኛ ) በዚህ ውስጥ የሙሴም ሆነ የእስራኤል የኪዳናቸው መሠረት የበግ ደም መሆኑን ተመልክተናል 5ኛ ) አያይዘንም ዛሬ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ሕጉ በታቦቱ ላይ ሳይሆን በልባችን ላይ የተጻፈ በመሆኑ የኪዳናችን መሠረት የክርስቶስ ደም ነው ይህ ደም ደግሞ ቅዱስ ሕዝብና ለርስቱም የተለየን ወገን የንጉሥ ካህናትም አድርጎናል ታድያ ይህ ደም አሁንም እንደ ብሉይ ኪዳኑ ዘመን የበግ ፣ የፍየል ወይም የኮርማዎች ደም ዓይነት ሆኖ የፈሰሰልንሳይሆንብቸኛው የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ሆኖ የፈሰሰልን ስለሆነ ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስና ለርስቱም የተለየ ወገን ቅዱስ ሕዝብም መሆናችንን አብስሮናል ትምህርቱም ይህንን እውነት በሰፊው ያብራራል ፣ ይተነትናል ቪዲዮውን ተከታተሉት ትባረኩበታላች ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

የክፍል ሁለት ትምህርት ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ የክፍል ሁለት ትምህርት ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ የክፍል ሁለት ትምህርት ፦ ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ በመጽሐፍቅዱሱ ቃልና በእውነተኛይቱ ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት ሲመዘን ምን እንደሚመስል የምናይበት እውነት ነው ትምህርቱን ተከታተሉት ትባረኩበታላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

የታቦቱ አገልግሎት ( ክፍል ሦስት ) የታቦቱ አገልግሎት ክፍል ሦስት በክፍል ሦስት ትምህርት የታቦቱ አገልግሎት በሚል ንዑስ አርዕስት የተነሳሁ ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥ ፦ 1ኛ ) ታቦቱን በተመለከተ አሰርቱ ቃላት የተጻፈባቸው የሁለቱ ጽላቶች ማኖርያ መሆኑ 2ኛ ) ከእስራኤል መሪዎች ጋር የእግዚአብሔር መገናኛ ነበር 3ኛ ) በዚህም ምክንያት ታቦቱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር 4ኛ ) ሙሴም ታቦቱን አሰርቶ ሲያበቃ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አኖረው የእስራኤልም ሕዝብ ይዘውት ይጓዙ ነበር ይለናል 5ኛ ) ታቦቱ ወኪል የሆነና ሲንቦሊዝም የሆነ በመሆኑ የእስራኤል ጦረኞች በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ የያህዌ መገኘትና ምልክት ነበር 6ኛ ) አሁንም ታቦቱ ምስክርነቱን የሚያሳይና የተሰየመም በመሆኑ በመሠረታዊው ዓላማ ምክንያት ሀ ) የያህዌ ታቦት መሆኑን ለ ) የቃል ኪዳን ታቦት መሆኑን ሐ ) የጥንካሬው ታቦት መሆኑን የሚያሳይ ነው እነዚህን ሃሳቦች ይዘን ወደ ሐዲሱ ኪዳን የኪዳን አገልግሎት ስንመጣ ከቊጥር 1 እስከ 6 በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደሙ የኪዳናችን መሠረት በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኛችን ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመኖሩ ምልክታችን ፣ ይዘነው የምንጓዘው ታቦታችን ፣ የእግዚአብሔር ጉብኝቱ እና መገኘቱ የታየበት ምልክታችን ፣ እግዚአብሔር የተናገረበት ድምጻችንና የቃልኪዳን ታቦታችን እንዲሁም የጥንካሬ ኃይል የተገለጠበት በመሆኑም የጥንካሬው ኃይላችንና ታቦታችን ነው ትምህርቱ በአጭሩ እነዚህን ሃሳቦች በሙሉ ይጠቀልላል በትምህርቱ እንዲባረኩ ቪዲዮውን አዳምጡ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

Thursday, 13 April 2017

የታቦቱ አገልግሎት ክፍል ሦስት በክፍል ሦስት ትምህርት የታቦቱ አገልግሎት በሚል ንዑስ አርዕስት የተነሳሁ ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥ ፦ 1ኛ ) ታቦቱን በተመለከተ አሰርቱ ቃላት የተጻፈባቸው የሁለቱ ጽላቶች ማኖርያ መሆኑ 2ኛ ) ከእስራኤል መሪዎች ጋር የእግዚአብሔር መገናኛ ነበር 3ኛ ) በዚህም ምክንያት ታቦቱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር 4ኛ ) ሙሴም ታቦቱን አሰርቶ ሲያበቃ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አኖረው የእስራኤልም ሕዝብ ይዘውት ይጓዙ ነበር ይለናል 5ኛ ) ታቦቱ ወኪል የሆነና ሲንቦሊዝም የሆነ በመሆኑ የእስራኤል ጦረኞች በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ የያህዌ መገኘትና ምልክት ነበር 6ኛ ) አሁንም ታቦቱ ምስክርነቱን የሚያሳይና የተሰየመም በመሆኑ በመሠረታዊው ዓላማ ምክንያት ሀ ) የያህዌ ታቦት መሆኑን ለ ) የቃል ኪዳን ታቦት መሆኑን ሐ ) የጥንካሬው ታቦት መሆኑን የሚያሳይ ነው እነዚህን ሃሳቦች ይዘን ወደ ሐዲሱ ኪዳን የኪዳን አገልግሎት ስንመጣ ከቊጥር 1 እስከ 6 በጠቀስኩት ሃሳብ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደሙ የኪዳናችን መሠረት በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኛችን ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የመኖሩ ምልክታችን ፣ ይዘነው የምንጓዘው ታቦታችን ፣ የእግዚአብሔር ጉብኝቱ እና መገኘቱ የታየበት ምልክታችን ፣ እግዚአብሔር የተናገረበት ድምጻችንና የቃልኪዳን ታቦታችን እንዲሁም የጥንካሬ ኃይል የተገለጠበት በመሆኑም የጥንካሬው ኃይላችንና ታቦታችን ነው ትምህርቱ በአጭሩ እነዚህን ሃሳቦች በሙሉ ይጠቀልላል በትምህርቱ እንዲባረኩ ቪዲዮውን አዳምጡ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

Saturday, 8 April 2017

ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ :--- የክፍል ሁለት ትምህርት የክፍል ሁለት ትምህርት ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ የክፍል ሁለት ትምህርት ፦ ታቦት ከምን እንደተሰራ ፣ አጀማመሩና ምሳሌነቱ በመጽሐፍቅዱሱ ቃልና በእውነተኛይቱ ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት ሲመዘን ምን እንደሚመስል የምናይበት እውነት ነው ትምህርቱን ተከታተሉት ትባረኩበታላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: ስለታቦት ምስጢር ያውቃሉ ካላወቁ የተቀዱ ቪዲዮችን ይመልከቱ ጥያቄ ካልዎት በውስ...

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry: ስለታቦት ምስጢር ያውቃሉ ካላወቁ የተቀዱ ቪዲዮችን ይመልከቱ ጥያቄ ካልዎት በውስ...: ስለታቦት ምስጢር ያውቃሉ ካላወቁ የተቀዱ ቪዲዮችን ይመልከቱ ጥያቄ ካልዎት በውስጥ መስመር ይጻፉልን ...
ስለታቦት ምስጢር ያውቃሉ ካላወቁ የተቀዱ ቪዲዮችን ይመልከቱ ጥያቄ ካልዎት በውስጥ መስመር ይጻፉልን

Image may contain: 1 person, sky and outdoor

Thursday, 6 April 2017