የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ?
ክፍል አምስት
በዚህ በክፍል አምስት ትምህርታችን ላይ የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? በሚል ሃሳብ ዙርያ ነው የምንማማረው ለዚህ ጥያቄ የምንሰጣቸውን መልሶች በአራት ዓይነት ክፍል ከፍለንና ለይተን በማየት ይሆናል የምንመለከተው
ከዚህ በመቀጠል እንግዲህ ወደ መጀመርያው ክፍል እናልፋለን
1ኛ ) The Transubstantiation view ( የአንድ ነገር ወደሌላ ነገር የመለወጥ ዕይታ )
በቲዎሎጂው አተረጓጐም የአንድ ነገር ወደሌላ ነገር የመለወጥ ዕይታ The Transubstantiation የሚባለው የዳቦውና የወይኑ ንጥረ ነገር ወደ ክርስቶስ አካል ማለት ወደ ቅዱስ ሥጋውና ወደ ክቡር ደሙ መለወጡ ነው ይህ እንግዲህ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዶክትሪንና አስተምህሮት ነው ከ1962 _ 1965 ባለው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተደነገገና የሆነ ነው ይህ ዕይታ የሚያስይዘን ወይኑና ዳቦው በትክክል ወይም በአሁኑ ሰዓት ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ሥጋና ደም በዚህ የትምህርት አደረጃጀት ቃሉ በቄሱ በሚነገርበት ጊዜ የሚሆን ነው ዶክትሪኑ Transubstantiation በመባል ይታወቃል የአንድ ነገር ወደ ሌላ ነገር የመለወጥ ዕይታ ነው ይህ ማለት የሚታየው የዳቦው ማለትም የኅብስቱ እና የወይኑ ሀብት አይለወጥም የውስጥ እውነታው ግን ወደ መንፈሳዊው ነገር እየተቀየረ የሚሄድ ነው ኢየሱስ ግን ይህን ዳቦ ማለት ኅብስቱን ሥጋዬ ወይኑን ደግሞ ደሜ ነው ቢልም ይዘትና ቅርጽ ባለው ቋንቋ ተጠቅሞበታል ሁልጊዜም ይጠቀመዋል ይህ ማለት ልክ አንድ ሰው ዛሬ ቢኖርና ፎቶ ግራፉን ይህ አባቴ ነው በማለት ቢያሳይ እንደማለት ነው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ፥ 11 ፣ 21 የተጻፈው ቃል ይህንን እውነታ የሚያስገነዝበን ሲሆን ቃሉም እንዲህ ይላል ምሳሌው ይህ ነው ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው ይለናል እንደገናም እርሱም መልሶ፦ እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው አላቸው ይለናል ስለዚህ ምሳሌው ይህ ነው ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው ማለት የእግዚአብሔር ቃል በዘሪው ተመስሏልና ከእግዚአብሔር የሚተላለፈው የመልእክት ቃል ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ነው ለማለት ነው እንደገናም
እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው ማለቱ የሥጋ ዘመዶቹ የሥጋ ዘመዶቹ እንዳልሆኑ ላለማመንና ላለመቀበል ብሎ ሳይሆን ይህ በእግዚአብሔር ቃል የመጣ ቤተሰብነት በሥጋ ከሚመጣ ወንድምነትና እህትነት ቤተሰብነትም ጭምር የሚበልጥና የላቀም መሆኑን ለማስገንዘብ ነው በመሆኑም ይህ ሥጋውን የመብላትና ደሙንም የመጠጣት ጥያቄ የአይሁድ ጥያቄ እንደገናም የደቀመዛሙርቱም ጭንቀት ማንጐራጐርና ወደኋላ ለመመለሳቸውም ምክንያት በመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ለዚህ አሳሳቢና ግራ አጋቢ ጉዳይ አሁንም ቅርጽና ይዘት በመስጠት ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል በዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 61 _ 65 መሠረት ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን ? እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል ? ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ ይለናል በመሆኑም ታድያ እኛም በምሳሌነት የቀረበውን ኅብስቱንና ወይኑን እንውሰድ እንጂ በጌታ እራት ማለት Holy
Communion ( በሆሊኮሙኒየን ) ስም የምንበላው ብርንዶ ሥጋ የለም ኢየሱስም በዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 54 _ 58 ላይ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል ቢለንም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው ስላለን ሥጋ ምንም አይጠቅምምና እንድንበላው የሰጠን ቃሉን ነው ቃሉን የምንበላው ደግሞ ስናምነው ነው ባለማመን ምክንያትም አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቃልና ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ አለ እንደገናም በዮሐንስ ወንጌል 6 ፥ 35 ላይ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም ነገር ግን አይታችሁኝ እንዳላመናችሁ አልኋችሁ አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድግ ከሰማይ ወርጃለሁና ሲል ነገረን የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ማለቱም በቃሉና በራሱ በዚሁ ጌታ ከማመናችን የተነሳ ወደዚህ ጌታ መጥተን ከቶውንም
የማንራብና የማንጠማም መሆኑን ነገረን እንጂ አሁንም እንድንበላው ያቀረበልን ሥጋም ሆነ ደም የለም እንደገናም የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም ስላለን ወደ እርሱ ብቻ እንድንመጣ ጋበዘን እንጂ ከእርሱ ሌላ የተዘጋጀ እንጀራ እንዳለና ወደዚህ እንጀራ ሄደን ይህን እንጀራና የተዘጋጀውን ውሃ በመብላትም ሆነ በመጠጣት ለዘላለም የማንራብ ፣ የማንጠማም መሆናችንን አልነገረንም ስለዚህ ላለመራብና ላለመጠማት ከኢየሱስ ውጪ የተዘጋጀ ሌላ እንጀራም ሆነ የሕይወት ውሃ አናውቅም እኛም ለዚሁ ስንል የምናዘጋጀው የሕይወት እንጀራም ሆነ የሕይወት ውሃ የለም ወደዚህ ጌታ መጥቶ በዚሁ ጌታ ያመነ ሁሉ ለዘላለም አይራብም ደግሞም አይጠማምና ይሄ ጌታ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ የተሰጠ የሕይወት እንጀራና የሕይወት ውሃ ነው ሳምራዊቷ ሴት እንኳ በፍጻሜው ሰዓት የናዝሬቱ ኢየሱስ በሰጣት መልስ መሠረት ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ ባላት ጊዜ ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ
ያለችው ከዚህ እውነት የተነሳ ነው ዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 13 _ 15 ጌታ እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል ባርኮልን በዚሁ ቃል ይጥቀመን አሜን
የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment