የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ?
ክፍል ሰባት
3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት
Symbolic
View and The Dynamic View
በዚህ በክፍል ሰባት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው ምልክታዊ ትዕይንቶችን እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንትን ነው በእንግሊዘኛው Symbolic View and The Dynamic View ይባላል ምልክታዊ ትዕይንቶች ( Symbolic
View ) ኅብስቱና ወይኑ ክርስቶስ በሰውነቱ ለከፈለው እና ደሙን ላፈሰሰው ምልክት የሆነ ብቻ ነው እርሱ እንደተናገረው የጌታ እራት በመጀመርያ ክርስቶስ ለፈጸመው ሥራ ማስታወሻ ነው ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝቦች አንድነታቸውን በሚጠብቁበት ጊዜ ማለት እርስ በእርሳቸው ያላቸውን አንድነት ሲጠብቁ ከአንዱ ከክርስቶስ ጋር ናቸው ይህ ደግሞ በተጠመቀችና ነጻነት በወጣች ቤተክርስቲያን ያለና የተያዘ ትዕይንታዊ ነጥብ ነው ለዚህ ሃሳብና ድምጽ ደግሞ የበለጠ ቦታና ዋጋ በመስጠት በጌታ እራት ጊዜ ጌታ ያደረገውን ክርስቲያን የሚያደርገውና ቃል የሚገባበት ነው እንቅስቃሴን የሚፈጥርና ኃይል ያለው ትዕይንት
በእንግሊዘኛው The Dynamic View የተባለው ደግሞ የመጨረሻው ጆን ካልቪን ለፕሪስፒቴርያን ቤተክርስቲያን ማሻሻያ የሰጠ የእርሱን ትምህርት The Dynamic View ን የሚከተሉ ናቸው ይህ ዕይታ የመጨረሻ የሆነ የእርሱ ዕይታ ነው እርሱ በሉተርና በዝዊንግሊ መካከል አካባቢ የተነሳ ነው ካልቪን ከዝዊንግሊ ጋር የተስማማ ነው እርሱ እንደተረዳው ኅብስቱና ወይኑ ክርስቶስ በአካል ለመገኘቱ በጥንተ ነገሩ ሆኖ ምሳሌ የሆነ ነው ምክንያቱም አካሉ በሰማይ ተነስቶ ከብሮአል ( ዕብራውያን ፲ ፥ ፲፪ እና ፲፫ ) እስካሁን ድረስም እርሱ እንቅስቃሴን ኃይልን የሚፈጥር በእንግሊዘኛው The Dynamic View ሲሆን በጌታ እራት ጊዜም በመንፈስቅዱስ አማካኝነት መንፈሳዊ መገኘት የሚያደርግ ነው ይለናል በአምልኮ አገልግሎትና የእግዚአብሔር ቃል በሚታወጅበት ጊዜ የጌታን እራት እንወስዳለን የከበረው ጌታ መንፈሳዊ መግቦቱን ከከበረው ሰውነቱ እርሱን ለተቀበሉ ይሰጣል በኅብስቱ መግቦቱ በሚታይ ሰውነቱ ክርስቶስ በሰውነቱ የከበረ ነውና ለነፍሳችን ሙሉ የሆነ ብሩህ ደስታንና ንቃትን ጉብዝናን ይሰጠናል ከክርስቶስ ጋር በሰውነት ወይም በአካል መካከል ካለ የሕይወትና የአንድነት ግንኙነት ምክንያት ራስ ሆኖ ለተነሳው ክርስቶስ በቤተክርስቲያን የእርሱ አካልና አባላት ነን ( ኤፌሶን 1 ፥ 18 _ 23 ፤ ኤፌሶን 4 ፥ 15 እና 16 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 23 )ይህንን መግቦት ወደ ክርስቲያኖች የሚያዘዋውረው በእኛ በሚኖረው በመንፈስቅዱስ ነው ( ሮሜ 8 ፥ 9 _ 11 )ይህ ካልቪን ያመነው የመንፈስቅዱስ መንገድ ደግሞ ምሥጢራዊ የሆነና መሳሳት የሌለበት መንገድ ነው የካልቪን ዕይታ በእነዚህ መጻሕፍት በትክክል የተጻፈ የእግዚአብሔር መግቦትና ሥልጣን በሕዝቡ ላይ የሚሠራ ነው (ኤፌሶን 3 ፥ 14 _ 21 ፤ ቆላስያስ 2 ፥ 6 _ 10 ፣ 19 ) ምንጭ New Alustrated Bible Dictionary እና ከመሳሰሉት ተጠናክሮ የተወሰደ
እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል ይባርክልን
የJoshua Breakthrough Renewal
Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment