Sunday, 12 July 2015

003የትምህርት ርዕስ Part 2 ጉዳያችን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሁን የተወደዳችሁ ወገኖች ሰው ሁሉ ፊቱን ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር መልሶ ለነገሮቹ ሁሉ ፍጻሜ እግዚአብሔርን እንዲፈልግና ጉዳዩንም የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዲያደርግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ትምህርት ነው ዛሬ ግን ብዙ ሰዎች ወደ ጌታ ቤት መጥተውና ጌታንም ጭምር እናገለግላለን እያሉ ጉዳያቸው ግን ሰዎችና ሁኔታዎች ስምና ዝና ክብር ጥቅምና የመሣሠሉት ሊሆኑ ይችላሉ ታድያ እነዚህ ሁሉ ጉዳዮቻችን በሚሆኑ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በብዙ እንተላለፋለን ለትምህርታችን እንደመነሻ ጥቅስ አድርገን የወሰድነው ዘኁልቁ 9 ፥ 18 ፣ 23 ነው እስራኤል የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጉዳያቸው ባደረጉ ጊዜ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይጓዙ ነበር በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሠፍሩ ነበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር የሚለውን ሃሳብ ነው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ የእስራኤል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ባሮች የነሙሴም ጉዳይ ስለነበረ የእግዘብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁና ያስጠብቁም ነበር ብለናል ዘኁልቁ 9 ፥ 23 ፤ ዘኁልቁ 33 ፥ 2 እንደገናም የራሱ የእግዚአብሔርም ጉዳይ ትእዛዙ ነበረ ብለን ያነሳናቸው ሰፊ የሆኑ ተከታታይ ሃሳቦች አሉን ትምህርቱ ሰፋ ያለ ስለሆነ ተከታታይነት ባለው እና ረዘም ባለ ሃሳብ የቀረበ ነው ባለፈው እግዚአብሔርን የመቀደስ ሕይወት ከሚለውም ትምህርት ጋር የተገናኘ ሃሳብ አለው እግዚአብሔርን የመቀደስ ሕይወት የያዙ ሰዎች ጉዳያቸው የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ እግዚአብሔርን ይቀድሱታል እንግዲህ ወገኖቼ በዚህ አጭር ጽሑፍ ወደ እናንተ የቀረብኩት ትምህርቱን እንደሚገባ ለመከታተል እንዲያመቻችሁ እንደ መግቢያና መንደርደርያ ሊሆኑ የሚችሉ ጥቂት ሃሳቦችን ለመስጠት ያክል ነው እንግዲህ ትምህርቱ ከዚህ በመቀጠል በፌስቡክም ሆነ በብሎጎቼ እንደገናም በጎግል አድራሻዬ ላይ ሰፍሮ ስለሚገኝ እየገባችሁ ማዳመጥ የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ በጌታ ፍቅር ሆኜ ማሳሰብ እወዳለሁ የጌታ ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን ተባረኩልኝ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment