የመልዕክት ርዕስ ሳኦልን ያሳሰበውና ግድ ያለው ነገር
ለቅዱሳን የታዘዘ ወቅታዊ መልዕክት
ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ
የመልዕክት ርዕስ
ሳኦልን ያሳሰበውና ግድ ያለው ነገር
እርሱም በድያለሁ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት እባክህ አክብረኝ
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው
1ኛ ሳሙኤል 15 ፥ 30
የተወደዳችሁ ወገኖች ይህንን መልዕክት በማስተዋል ሆናችሁ የምትከታተሉ ሁሉ ሳኦልን በተቀዳሚነትና በዋናነት ያሳሰበው ግድ ያለውም ነገር በእግዚአብሔር ፊት የሠራው በደል ያጠፋቸው ጥፋቶች ሳይሆኑ የሕዝቤ ሽማግሌዎች እያለ በሚጠራቸው መሪዎች አስተዳዳሪዎች ፊት እና በእስራኤል ፊት የነበረው ክብር እንዳይቀንስ ዝቅም እንዳይል ከመፍራት የተነሳ እየመጣበት ያለ አስከፊ ገጽታ ነው ነው በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ሳሙኤልን በድያለሁ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት እባክህ አክብረኝ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ እያለ ሲማጸነው ሲለማመጠውም እንመለከታለን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት እባክህ አክብረኝ ማለቱ ሳሙኤልም ሳኦልን የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል የእስራኤል ሃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትም ብሎት ነበርና ይህንኑ የተናገርክበትን ሃሳብህን ለውጠህ መንግሥትሕ የጸና ለሌላም የማይሰጥ ንጉሥ ነህ በለኝ በእስራኤልም ሆነ በሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ ስትል አክብረኝ ማለቱ ነበር ለዚሁ ጉዳዩ ሳኦል ሳሙኤልን አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜያለሁ በማለት ፣ የፈጸመም በመምሰል በብዙ የውዳሴ ቃልና የማሞካሸት ቃል ቀርቦታል ሳሙኤል ግን የሳኦልን የፊት ለፊት ኩሸትና የለበጣ ቃል ሳይሆን ከሳኦል ጀርባ ያለውን የበጎች ጩኸት ፣ የበሬዎችም ግሣት በጆሮው የሰማ በመሆኑ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድርነው የሚል ጥያቄ ካቀረበለት ውጪ ሌላ ምንም ሊለው አልፈለገም መቼም ሳኦልን የሚያሳቅሉ የሚያሳጡትም ነገሮች ከፊት ለፊቱ ባይኖሩም ከጀርባው ተደበቀው ገበናውን የሚያወጡበት የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ወይንም በሌላ ቃል የእርም አቤቱታዎች ለሳሙኤል ጆሮ በእርግጠኝነት መድረሳቸው አልቀረም ታድያ እነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ እያሉ ሳኦል ሳሙኤልን አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜያለሁ ስላለው ብቻ ሳሙኤልም እውነት ነው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የፈጸምክ ታማኝ ንጉሥ ነህ ስለዚህ ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ እንደማይለው ለሁላችንም ግልጽ ነው ስለሆነም ሳሙኤል በከንቱ ውዳሴና በሳኦል የለበጣ ቃል የሚገበዝ ፣ በዘመናችን እንዳሉ አስመስለውም እንደሚናገሩና እንደሚኖሩ እንደ አንዳንድ ነቢያት በበላበትም የሚጮህ ዓይነት ሰው አይደለም እርሱ ታማኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ በመሆኑ እግዚአብሔር ያለውን ብቻ የሚናገር ነው ሳኦል በዚህ አላበቃም ይህ የለበጣ ቃሉ በሳሙኤል ፊት ተቀባይነት እንዳጣ ሲረዳ መልኩን ቀይሮ እባክህ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ የሚል ልመና ውስጥ ገባ ይህ የሳኦል ልመና አሁንም የኃጢአትን ይቅርታ አስገኝቶ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ካለ ናፍቆትና ጉጉት የመጣ ሳይሆን ንግሥናን ዘውድንና በሰውም ፊት የሆነ ክብርን ላለማጣት ሲባል ተቀነባብሮ የቀረበ የይምሰል ይቅርታና ለእግዚአብሔር የመስገድ ፍላጎት ነው ታድያ ሳኦል ንግሥናውን ላለማጣት ሲል ኃጢአትን እንደታቀፈ ለእግዚአብሔር ቢሰግድም ሳሙኤል ግን እንዲህ ባለ ሁኔታ ከእርሱ ጋር ሊሰግድ አልተመለሰም ዛሬ ታድያ ሳኦል ብቻ ሳይሆን ብዙ ሰዎች ሳኦልን በሚመስል ብልሃትና የክፋት አሠራር ውስጥ ተቀምጠው ለእግዚአብሔር መስገድን ብቸኛና አማራጭ የሌለው ዓላማቸው ያደረጉ ፣ የእነርሱም መስገድ ሳያንሳቸው ለሚያያቸው ሁሉ ጤናማ ክርስቲያንና ታማኝ አገልጋይ ለመምሰል ሳኦል ሳሙኤልን እንዳለው ለራሱም ሄዶ እንዳደረገው ኑ ልትሰግዱ ከእኛ ጋር ተመለሱ በማለት ክብርንና ጥቅምን ጥልቅ የሆነ የግል ፍላጎታቸውንም ከማሳካት የመነጨ ተውኔት የሚፈጽሙ በዘመናችንም እንደ ሳኦል ያሉ መንፈሳውያን አርቲስቶች አልጠፉም እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሰግዱ መስለው ለእግዚአብሔር እንድንሰግድ ከእኛ ጋር ተመለሱ ይበሉ እንጂ እውነተኛው ስግደት ለእግዚአብሔር እንዲሰጥ ከመቅናት ተነስተው እያደረጉት ያለ ነገር አይደለም እንደውም እውነቱን ለመናገር እነዚህ ሰዎች ከእግዚአብሔር ይልቅ ስግደቱም ይሁን ማንኛውም ነገር በቅድሚያ ለእነርሱ ቢሆን ለእነርሱም ሆኖ ቢቀርብ ደስታውን አይችሉትም ለእግዚአብሔር እንድንሰግድ ከእኛ ጋር ተመለሱ የሚለው ያላሰለሰ ድምጻቸው ግን መንፈሳዊ ሊያሰኛቸው የተዘጋጀ የማጥመጃ መሣርያቸው ነው ይህም የሚያሳየን እነዚህ ሳኦልን የመሰሉ ሰዎች ወይም የሳኦል ወንድሞች ማለት ይቻላል ዓይን ያወጣውን የበሬዎቻቸውን እና የበጎቻቸውን ግሣት ከጀርባቸው እየሰማን እንዳልሰማንባቸው አድርገው በመቁጠር ብንሰማም እንኳን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ምንም ሳንናገርና ትንፍሽም ሳንል እነርሱ የሚፈልጉትን ስግደት ብቻ ለእግዚአብሔር እንድናመጣ አብረናቸውም እንድንሰግድ የሚሰብኩና የሚያስተምሩም ከሆነ ምንም ሳናቅማማ አሜንታችንን ከፍ ባለ ድምጽ እያሰማን አብረናቸው እንድንኖር ሳያሰልሱ የሚወተውቱን ናቸው ይህንን የየዋህነት መንገዳችንን ተጠቅመውም እነርሱ ያጠፉት ሳያንሳቸው እነርሱ ጥፋት ውስጥ ዓይናችን እያየ ወስደው ሊዘፍቁን ፣ ሊጎዘጉዙንና ሊነክሩን የጥፋታቸውም ተባባሪዎች ሊያደርጉን የሚሹ ናቸው ነገር ግን ይህ የጸጋ ዘመን ያልቃልና እግዚአብሔር የቀጠረላቸው ቀን እውነተኛ ንስሐ እንዲገቡ የተቀጠረ ቀን ነው እንጂ ይህን ክፉ ተግባራቸውን እየፈጸሙ በክፋታቸውም እየባሱ እየሳቱና እያሳቱ የሚጓዙበት የሕይወት መስመር አይደለም እነዚህን ሰዎች ተመለሱ አይበጃችሁም ማለት በመጽሐፉ ቃል መሠረት እውነት ቢሆንም በእነርሱ አስተሳሰብ ግን በራስ ላይ ገመድን እንደማሳጠር ተብሎ ስለሚታሰብ እንዲህ ዓይነቱ ሰው በእነርሱ ራዳር ውስጥ የገባና ቀይ የትራፊክ መብራት ሳይቀር የጣሰ መኪና ዓይነት ነው እንዲህ ላሉ ሰዎች ዛሬ ሳሙኤልና የሳሙኤል መልዕክቶች አስፈላጊ አይደሉም ቢኖሩም አፍራሽ ናቸው ከሚባሉ በስተቀር ተቀባይነት የላቸውም ስለዚህ ቅዱሳን እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ስናገኝ ስም ያላቸው አገልጋዮችም ይሁኑ በወንበር ላይ የተቀመጡ መሪዎች መንፈሳዊ የሚመስለውን የእናምልክ ግብዣቸውን ከምንቀበል ይልቅ በቅድሚያ ተቀበሉንም አልተቀበሉን ይህንን ነገር አይተን ቸል ማለት አንችልምና ስደትና መገፍተር ቢበዛብንም ያለምንም ይሉኝታ ይህን የማስመሰል ተግባር እንደ ሳሙኤል ጴጥሮስንም ፊት ለፊት እንደተቃወመው እንደ ጳውሎስ እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ጥላቻቸውንና ተቃውሞአቸውን ተንኮላቸውንም ጭምር ፈርተን ዝም ልንላቸው አይገባም ይልቁንም ያመጡትን ያምጡ እኛ ግን አምላካችንን ታምነን ሳንፈራቸው አላበጃችሁም ስንል ልንቃወማቸው ሳናቋርጥም በአጽንኦት ልንገስጻቸው ይገባል እግዚአብሔር በዚህ ኃይል ያስነሳን አሜን
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:
Post a Comment