Thursday 2 April 2020


በኦርቶዶክስ ውስጥ ያለው ውስጣዊ ክፍልፍል..!


በኦርቶዶክስ ውስጥ ያለው ውስጣዊ ክፍልፍል..!
N.B - ከሰሞኑ በተለያዩ የኦርቶዶክስ መምህራን ተንኳሽነት በእስልምና ስላለው መከፋፈል በመፃፋቸው ምክንያት ብቻ "ዝንጀሮ የራሷ መላጣ አይታያትም" በሚለው ብሒል ተነሳስተን ፃፍነው እንጅ ይህ ጉዳይ የኛ አጀንዳ አይደለም። እንደሁኔታው በሰፊው ተዳሶ ሊቀጥልም ላይቀጥልም ይችላል።
......
በዚህች ጹሁፋችን የምንዳስሰው ከኦርቶዶክስና የካቶሊኩ የእርስ በርስ እልቂት በኃላ አገራችን ላይ በኦርቶዶክስ ውስጥ ስለተፈጠረው ግጭት በአንድ የታሪክ መጽሐፍ ላይ ብቻ የተገኘውን መርጠን ነው። በተክለ ጻድቅ መኹሪያ « የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልበነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ » ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደው የዚህ ክፍፍል ታሪክ እንደሚከተለው ይገለፃል፦
«የኢትዮጵያ ካህናትና ሕዝብ የሚጠሉትና የተጋደሉበት የካቶሊክ ሃይማኖት በዐፄ ሱስንዮስ መሞትና በዐፄ ፋሲል መንገሥ በሚሲዮኖቹ መጥፋት ከተወገደላቸው በኋላ በኢትዮጵያ ኦርዶክሳዊት ሃይማኖት ውስጥ ካራና ጸጋ ቅባት የሚባሉት ወገን ለይተው ክርክር ስለ አነሡ ለሕዝብና ለመንግሥት አስፈላጊ የነበረው #ሰላም #በሙሉ #አልተገኘም ነበር ።»
የቅባት ፣ካራና ጸጋ ግልፅ ልዩነቶች
፩- ክርስቶስ በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ ነው ተዋሕዶ ማለትም የእግዚአብሔር ልጅ የኛን ሥጋ ኣካሉ ከፍሎ ቢዋሐደው በሰውነቱ እንደ ኣብ እንደ መንፈስ ቅዱስ ያለ ፍጹም አምላክ ሆነ የሚሉ ተዋሕዶዎች(ካራዎች) ናቸው ።
፪- የሥጋና የቃል መዋሐድ ሁለትነትን አጠፋ እንጂ ቃል የለበሰውን ሥጋ የባሕርይ ኣምላክነት ክብር ያከበረ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚሉ ቅባቶች ናቸው ።
፫- ቃል በለበሰው ሥጋ በመንፈስ ቅዱስ እንደኛ የጸጋ ክብር አግኝቶ ክርስቶስ ተባለ የሚሉ የጸጋ ልጆች ናቸው ።
❐ የቅባቶችም ወገን ከጐጃም በተለይ ደብረ ወርቆች ናቸው ተዋሕዶ ግን በደብረ ሊባኖስ በሽዋ በጐንደር ፣ በትግሬ ነው ጸጋ ዎች ግን ይበልጥ የሚገኙት በሽዋ ነው ይባላል ።
(የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልበነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ በተክለ ጻድቅ መኹሪያ ገጽ 268—269)
በየግዚው የሚነሱ ነገሥታት ለሚከተሉት ሀራጥቃ የነበራቸው ወገንተኝነት፦
«ዐፄ ዘድንግልና ሱስንዮስ ለካቶሊኮች ዐፄ ፋሲልና አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ለተዋሕዶዎች ካሮች ፤ እነዐፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ እነዐፄ በካፋ ለጸጋ ልጆች ያደሉ እንደ ነበረ እንደዚሁ ጻድቁ ዮሐንስ እምነታቸው ቅብዐት በመሆኑ ለነርሱ ያደሉ ስለ ነበረ በሳቸው ዘመነ መንግሥት የጐጃም ቅባዐቶች እንደ ልባቸው ኖሩ ይባላል » ( ያለፈው ምንጭ ገጽ 279)
❐ በዐፄ ዳዊት የንግሥና ዘመን የነበረው የቅባትና ካራ ኦርቶዶክሶች የርስ በእርስ ግጭት እና ግፍ የተሞላበት ጭፍጨፋ
«ዐፄ ዳዊትም እንደ እንደራሴያቸው የቅባቶችን ሃይማኖት ይወዱ ነበር ይባላል ይሁን እንጂ ባንድ ወገን ከጭቅጭቅ ለመዳን በሌላውም ወገን ጕዳዩ የሚመለከተው የቤተ ክህነቱን የበላይ አለቃ ጳጳሱን
በመሆኑ እንዲያውስ በአቡነ ማርቆስ እግር አሁን የመጡትን ጳጳስ አቡነ ክርስቶዶሉን ጠይቋቸው ብለው ለሁለቱም ወገን ነገሯቸው እነሱም እሺ ብለው ቢትወደድ ዘጊዮርጊስን እንደ ዳኛ ይዘው ወደ ፡ ጳጳሱ ሄዱና የዚህኑ የሃይማኖት ነገር ጠይቋቸው ጳጳሱም የንጉሥ የዐፄ ዳዊትና የእንደራሴያቸው የቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ሃይማኖት ቅባት
መሆኑን ስላወቁ ክርስቶስ በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ ሆነ ብለው እንዳይመሰክሩ ፈሩና እንዲያው ፡በደፈናው « የኔ እምነት እንደ ሹመት አባቶቼ እንደነአቡነ ሲኖዳና እንደነኣቡነ ማርቆስ ነው ብለው መስሱላቸው » በዚህም ብልጠት ባለበት መልስ ሁለቱም ወገኖች ትርጕሙን ለየ ራሳቸው አድርገው ደስ እያላቸ ወደየሥፍራቸው ተመለሱ ።
ቤተ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉት የአዘዞና የሞና (መጕና) ሊቃውንትም አቡነ ክርስቶዶሉ ሃይማኖቴ እንደ ቀድሞዎቹ ጳጳሶች እንደ አባ ማርቆስና እንደ አባ ሲኖዳ ነው ማለታቸው ለኛ መመስከራቸው ነው ብለው ደስ እያላቸው ወደ አዘዞ ሄዱ ።
ቅባቶችም ከቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ጋራ ወደ ንጉሥ ተመልሰው ጳጳሱ የተናገሩትን ነገሯቸው ንጉሡም የአቡነ ማርቆስና የአቡነ ሲኖዳ ሃይማኖት እንደ ምን ኖሯል ብለው ባጠገባቸው ያሉትኝ መኳንንትና ሊቃውንት ጠየቋቸው እነሱም ንጉሡንና እንደራሴውን ደስ ለማሰኘት የነዚህ የሁለቱም ጳጳሳት ሃይማኖት «ክርስቶስ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ ሆነ ማለት ነው » ብለው ነገሯቸው ።
ንጉሡም « መልካም ነው ይኸንኑ ሄዳችሁ ባደባባይ ፡ በዐዋጅ ንገሩ » ብለው አዘዟቸው እነሱም ደስ እያላቸው ሄደው «ክርስቶስ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ ሆነ የሚሉት ቅባቶች ረቱ በተዋሕዶ የባሕርይ ልጅ ሆነ የሚሉት ተዋሕዶዎች ግን ተረቱ» ብለው ዐዋጅ ነግረው ተመለሱ ይኸንንም ዐዋጅና በዚህ ምክንያት በጐንደር የተደረገውን ደስታ በሰሙ ጊዜ ተዋሕዶዎች ዕጨጌያቸሁን ይዘው እንደ ገና ለመጠየቅ ወደ አቡነ ክርስቶዶሉ ዘንድ ሄዱና ይኸንኑ የቀድሞ ጥያቄያቸውን አድሰው ጠየቋቸው አቡኑም በዚህ ጊዜ ቢትወደዱና አንድም የቅባት ወገን ባጠገባቸው አለመኖሩን ተመለከቱና "ክርስቶስ በመዋሐዱ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ሆነ በመቀባቱ ግን መሲሕ ሆነ ብለው መለሱላቸው» ይኸንንም ከጳጳሱ በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸውና ተመለሱ አዘዞም እንደ ደረሱ በዕጨጌው ቤት ንሴብሖ እያሉ ዘመሩ ወረብም እየወረቡ ታላቅ ደስታ አደረጉ ።
ዕጨጌውም ጥላ ተይዞላቸው ታጅበው ወደ ደብረ ሊባኖስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ የዚህም ወሬ በጐንደር በተሰማ ጊዜ ንጉሠ ዐፄ ዳዊትና ቢትወደድ ዘጊዮርጊስ ተናደዱ የጃዊ ነገዶችን (የእስላምና የአረማውያንን የፈረሰኛ ወታደሮች) ሄዳችሁ የአዘዞን ሊቃውንት ፍጅዋቸው ብለው ሰደዷቸው እነሱም በግልቢያ ደርሰው ሊቃውንቱ በዕጨጌው ቤት እንዳሉ አገኝዋቸውና « መነኰሳቱን ግማሾቹን እየሰለቡ የቀሩትንም እየገደሉ በጭካኔ ፈጁዋቸው እጨጌ ተክለሃይማኖትም ዕራቁታቸውን እየጐተቱ
ደበደቧቸው ወደ ማታ ግን ንጉሥ እንግዲህ በቃችሁ ብለው ላኩባቸውና ተመለሱ » ይባላል
ከዚህ በኋላ ዐፄ ዳዊት ጳጳሱን ኣቡነ ክርስቶዶሉን አስጠርተው የቅባቶችን መርታትና የተዋሕዶዎችን መረታት ሕዝቡ ሁሉ እንዲያውቀው ሄደው ባደባባይ ዐዋጅ ይንገሩ ብለው አዘዟቸው ጳጳሱም መንፈሳቸው ደካማና ሰውን ደስ ማሰኘት ብቻ ስለ ሚወዱ ምንም የፊት ለፊት ክርክር ሳያደርጉ እሺ ብለው ወደ አደባባይ ሄደው « ክርስቶስ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክ ሆነ» ብለው ዐዋጅ ነገሩ ይባላል ።
(ያለፈው ምንጭ ገጽ 331–333)
አንግዲህ ታሪኩ ላይ እንዳየነው በየዘመኑ አዲስ ንጉሥ በተሾመ ቁጥር በሚቀሰቀሰው የኦርቶዶክስ የርስ በርሰ ግጭት ምክኒያት ብዙ ሰዎች ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ በግፍ ሲገደሉ ነበር። አንዱ የበላይነትን ሲያገኝ ሌላውን በግፍ እየጨፈጨፈ የሱን ሃሳብ በግድ እንዲቀበል ማድረጉ በነሱ የተለመደ አካሄድ ነው። በዚህ የግፍ ሰለባ ውስጥ የሀይማኖቱ ሊቃውንትም አልቀረላቸውም ነበር። ከግብጽ ተሹመው የሚመጡት ጳጳሳትም ቢሆን በየጊዜው የሚነሱት ነገሥታት ፍላጎት በእምነት ሽፍን ሕዝቡ ላይ መጫን እንጅ ለእምነት ግድ የሌላቸው ጥቅም አሳዳጆች ነበሩ። ትናንት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ልዩነትን ፈጥሮ ሲያጋድል የነበረው ከባዱን አጀንዳ ዛሬ ላይ በሙስሊሙ ውስጥ አስገብቶ እርስ በርስ ለማጋጨት መሰሪ የሆነ
አንዳንድ ደብተራዎች « አዲሱና ነባሩ እስልምና » የሚል ኦርቶዶክሳዊ ስያሜ ሰጥተው እየተንቀሳቀሱ ስናይ "ወይ አለማፈር..?!" አልን። ዳንኤል ክብረትም እነ ዘመንድኩንን ለመሳሰሉት ትንንሽ ደቀ መዛሙርቶቹ በድብቅ አቅጣጫ ይሰጣል ዘመድኩን ደግሞ በአደባባይ መርዙን ይረጫል።
ማስታወሻ፦ ከዚህ ጋር በተያያዙ ያሉ ታሪኮች ሰፊና በተለያዩ ድርሳናት የዘገቡ ናቸው። በመግቢያው ላይ እንደገለፅነው እንደሁኔታው ልንቀጥልበት እንችላለን..!

No comments:

Post a Comment