Thursday 2 April 2020

በየ ዓመቱ መስከረም 21 የተዋህዶ ወገኖችን ግሸን ደብረ ከርቤ እንዲሄዱ ማን አዘዛችው ለምንስ ይሄዳሉ?
አገራችን ላይ ያለችውን የተዋህዶ እምነት ጠፍጥፈው ዛሬ ያለችበትን ቅርጽ ያስያዟት በየጊዜው የተነሱ ዐፄዎች ናቸው ለቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመኑ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ሆነው መንፈሳዊ ህግን ያወጡ አና መጽሐፍትን ሳይቀር ያዘጋጁ ነበር ከነዚህ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የያዘው ደግሞ የ14 ተኛው መቶ ክፈለ ዘመን ገዥ ዘርዐ ያዕቆብ ነው
ይህ ግለሰብ ለቤተ ክርስቲያኗ ብዙ ህጎችን አውጥቷል ዛሬ ላይ መንፈሳዊ እየተባሉ ለቤተ ክርስቲያን ግልጋሉት እየሰጡ ያሉ መጽሐፍትንም አዘጋጅቷል ከነዚህ ውስጥ መስተብቁዕ ዘመስቀል ፣ መጽሐፈ ብርሐን ፣መጽሐፈ ሚላድ ፣መጽሐፈ ሥላሴ ፣መጽሐፈ ባሕርይ ፣ተዓቅቦ ምስጢር ፣ጦማረ ትስብእት ፣ስብሐተ ፍቁር ፣ክሂዶተ ሰይጣን ፣እግዚአብሔር ነግሠ፣ ድርሳነ መላእክት ፣ተአምረ ማርያም ፣ተአምረ ማርያም ወኢየሱስ፣ ተአምረ ትስብኢት ፣ልፉፈ ጽድቅ ፣ትርጓሜ መላእክት ሌሎች ተጨማሪ መጽሐትን የጻፈ ሰው ነው እነዚህ መጽሐፍት ዛሬ ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት ይሰጥባቸዋል
በተጨማሪም የደመራን በዓል ያዘዘው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ነው (መፅሐፈ ጤፉት ምዕራፍ 4 ገፅ 135) ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ የሱን ትዕዛዝ ልክ እምደ ሃይማኖታዊ ስርዓት ታስፈጽማለች ሌላም
« ለመስቀልና ለእመቤታችን ስግደት ይገባል» ብሎ ትዕዛዝ እንዳስተላለፈ እምቢ ያሉትን በድንጋ አስወግሮ እንዳስገደለ (ተአምረ ማርያም 24 ተኛው ተአምር) ይናገራል ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ለመስቀልና ለማርያም ስግደት ይገባል ብላ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብን ትዕዛዝ ታስተምራለች ምዕመኑም በተግባር ይፈጽመዋል
ዛሬ መስከረም 21 የሚከበረውን የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልም እንዲከበር ያዘዘው ይኸው ግለሰብ ነው
(መጽሐፈ ጤፉት ገጽ 113 )በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት መሰረት ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል የቀኙ ክፍል የተገረፈበት ጅራፍ ፣ሐሞት የጠጣበት ሰፈነግ ሳይቀር ከቅድሳን አፅም ጋር እዚሁ ኢትየጵያ ውስጥ አለ ተብሎ ይታመናል ከመጡት አፅሞች መካከል የኢየሱስ ወንድም የያዕቆብ ፣የማርያም እናት የሐና ፣ ሐዋርያው በርቶሉሜዎስ፣ የመጥምቁ ዮሐንስ የራስ ቅል ፣የቅዱስ ጊዎርጊስ ፣የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት ሳዊሮስና ዲዮስቆሮስን ጨምሮ ሄሮድስ ያስገደላቸው ህጻናት  እና ብዙ ለቁጥር ሚታክቱ አፅም ይገኝበታል (መጽሐፈ ጤፉት ምዕራፍ 5 ገጽ 137_138)
በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን ወደ ግሸን ደብር የተዋህዶ እምነት ያላቸው ሰዎች ሚሄዱት በዘርዐ ያዕቆብ ትዕዛዝ ከመስቀሉና ከቅዱሳን #አፅም በረከት ለማገኘት ነው መስከረም 21 በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ትዕዛዝ የሚከበረው የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል ምክኒያቱ ይህ ነው ብዙዎች ወገኖቻችን ለምን ትሄዳላችሁ ብትሏቸው አያውቁትም?
በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/orthox

No comments:

Post a Comment