Wednesday 18 September 2019

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መታደስዋን እንጂ መቃጠልዋን አንደግፍም እንቃወማለን ( ክፍል አንድ )ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መታደስዋን እንጂ መቃጠልዋን አንደግፍም እንቃወማለን ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን :: ሰሞኑን በኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ላይ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ቤተክርስቲያኒቱን በግብታዊነት ተነስተው ላቃጠሉ ሰዎች ከእርምጃቸው እንዲመለሱ በጽኑ ለማስገንዘብና ቤተክርስቲያኒቱም ማንና ምን እንደሆች እንዲያውቁ ለመርዳት ይሄ ትምህርት ለእነዚሁ ሰዎች ጭምር የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህም ሌላ ይህቺው ቤተክርስቲያን የነበራት የእግዚአብሔር ቃል አቋምና መሠረት ትክክለኛ ከመሆኑ የተነሳ ለብዙ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሳይቀር የመነሻ ምክንያት እና ምንጭ መሆንዋን ፣ እንደገናም ይህቺ ቤተክርስቲያን የሀገር ባለውለታም ከመሆንዋ ባሻገር ስለ ሀገር ስናስብ ስለዚህች ቤተክርስቲያን ጭምር ልናስብ ግድ እንደምንሰኝ እነዚህ ትምህርቶች የሚጠቁሙ ናቸው :: ስለዚህ ይህቺ ቤተክርስቲያን አሁን ላይ የሚያስፈልጋት መንፈሳዊ የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ እንጂ መቃጠል ባለመሆኑ ሕልውናዋን ከገጸ ምድር ለማጥፋት ሲሉ በእንዲህ ዓይነቱ ክፉ እርምጃ ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ ይህንን እርምጃቸውን እግዚአብሔር እንደማይደግፈውና እነርሱም እንደሚጎዱበት ትምህርቱ ያመላክታል :: ለማንኛውም ስለ ቤተክርስቲያኒቱ አነሳስና ሥረ መሠረት በውስጥዋም ያለውን መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ የሚጠቁሙ ማሳያዎችን ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት ለተከታታይነት አዘጋጅቻለሁ :: ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ማወቅ ለምትፈልጉ ሁሉ እነዚህ ትምህርቶች በብዙ ይጠቅሟችኋል ብዬ አስባለሁ :: ይሄ አሁን የለቀኩት የክፍል አንድን ትምህርት ነው :: የክፍል ሁለትና ቀጣዮቹም በሚቀጥሉት ጊዜያት በየተራ ይለቀቃሉ :: አሁን ግን በዚህ የክፍል አንድ ትምህርት ተባረኩ እላለሁ :: ከዚህም ባሻገር ጌታ ቢረዳንና ብንኖርና የአቶ ተፈራንና የባለቤታቸውን የወይዘሮ በላይነሽን የ60 ዓመት የክርስትና ጉዞና የትዳር ሕይወት ምን እንደሚመስል በምስክርነት መልክ በነገው ዕለት 10 AM ላይ ይዤ እቀርባለሁ :: በጸሎታችሁ አስቡን ፣ ጸልዩልን :: ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ :: አሁን ግን በዚህ ትምህርት ተባረኩ :: አባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ

No comments:

Post a Comment