Friday 27 September 2019

ፍጥረት ሁሉ ማንን ለማመስገን ተፈጠረ ? በተአምረ ማርያም መጽሐፍ መሠረት እመቤታችንን ወይስ እ/ርን ( Part 1 ) ==== ፍጥረት ሁሉ ማንን ለማመስገን ተፈጠረ ? የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ፍጥረት ሁሉ ማንን ለማመስገን ነው የተፈጠረው ? የተአምረ ማርያም የስድሳ አራቱ እትም የዘወትር መቅድም ቁጥር 7 ላይ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ይላልና ፣ የተፈጠርነው እመቤታችንን ለማመስገን ነው ? ወይንስ እግዚአብሔርን ለማመስገን ? መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 1 ፥ 12 ላይ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ እንደተፈጠርን ይናገራል እንጂ እመቤታችንን ለማመስገን እንደተፈጠርን አይነግረንም ስለዚህ የተፈጠርንበት ዓላማ ጌታን የማመስገን ዓላማ ስለሆነ ጌታንና ጌታን ብቻ እናመሰግናለን :: የአሮን እህት ነቢይቱ ማርያምም እየዘመረች እንደተናገረችው ለእግዚአብሔር ብቻ እንዘምራለን ኦሪት ዘጸአት 15 : 1 ፣ 20 እና 21:: ታድያ የተአምረ ማርያም መጽሐፍ ከዚህ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ሊያወጣን ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ በማለት ሌሎች አዋልድና ድርሳናት የተባሉ የኦርቶዶክስ መጻሕፍትን አጋዥ በማድረግ የማርያምን ፈጣሪነት ሊያሳየን ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን ለፈጠረች ለድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለእርስዋም እንገዛ ሲል ጥሪ አቀረበልን ( ምንጭ የየካቲት ኪዳነ ምሕረት ዚቅ ገጽ 144 ) :: የማርያም ሲገርመን መርቆርዮስ የተባለ ለክርስቶስ ሰማዕት መሆኑ እንኳ በውል የማይታወቀውን ሰማዕት ነው ብላ አምናና ተቀብላ ፈጣሪ አድርጋም በማቅረብ ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ ምድርን በዕጽዋት ወይም በአበቦች ያስጌጥክ መርቆርዮስ ሆይ ለስምህ እገዛለሁ በኃይልህም አመሰግናለሁ ወደ አንተ የመጣውን የሥጋ ለባሽን ሁሉ ጸሎት ስማ ይቅርታህንም አታዘግይብን ብርሃንህንና እውነትህን ላክ እነርሱም ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራ ወደ መቅደስህ ይውሰዱኝ የሚለውን ተረት ተረት እንድንቀበልና ፈጣሪንና ሥራውን ሁሉ ለመርቆሬዎስ ሰጥተንና መርቆሬዎስንም በፈጣሪ ቦታ ተክተን መርቆሬዎስን እንድናመሰግንና ወደ እርሱም እንድንጸልይ ነገሩን :: በመሆኑም ወገኖቼ ሆይ የተፈጠርንበት ዓላማ ማንን የሚያመሰግን ሊሆን ይገባዋል ? እኛስ ማንን ነው ማመን ያለብን ? አዋልድና ድርሳናት የተባሉ የኦርቶዶክስ የተረት መጻሕፍትን ወይስ መጽሐፍቅዱስን ? የተፈጠርነው ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ስለሆነ ማመስገን ያለብን እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና ያለውን እግዚአብሔርን ብቻ ነው ( ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ፥ 1 - 3 ) :: ነገር ግን ፍጡርን በፈጣሪ ቦታ ተክቶና የፈጣሪንም ምስጋና ለፍጡር ሰጥቶ ፍጡርን ማመስገን እግዚአብሔርን አንተ የለህም አምላክም አይደለህም ማለትን የሚያመለክት በመሆኑ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ከመሠለ ክህደት ይጠብቀን ነው የምለው :: ጌታ እግዚአብሔር አሁንም ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም እያለን ከዚህም ሌላ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም ሲልም እየተናገረን ( ዘጸአት 20 ፥ 1 - 6 ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 42 ፥ ) የእግዚአብሔርን አምላክነትና የአምላክነቱንም ሥራ ለፍጡር በመስጠት ወደ ፍጥሩ አምልኮ መመለስ ማለት ግን ለእኔ ትልቅ መታወር ነው እግዚአብሔርንም በእግዚአብሔርነቱ መጠን አለመረዳት ነው ( ሮሜ 1 : 20 - 25 ):: ለዚህም እግዚአብሔር ያስበን ከማለት በስተቀር ሌላ የምለው የለኝም :: ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንንም እግዚአብሔር በቃሉ ይፈውሳት እስራቶችዋንም ከላይዋ ላይ ይበጥስላት :: ለተጨማሪ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ ተባረኩ አባ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday 18 September 2019

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መታደስዋን እንጂ መቃጠልዋን አንደግፍም እንቃወማለን ( ክፍል አንድ )ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መታደስዋን እንጂ መቃጠልዋን አንደግፍም እንቃወማለን ( ክፍል አንድ ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን :: ሰሞኑን በኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ላይ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ቤተክርስቲያኒቱን በግብታዊነት ተነስተው ላቃጠሉ ሰዎች ከእርምጃቸው እንዲመለሱ በጽኑ ለማስገንዘብና ቤተክርስቲያኒቱም ማንና ምን እንደሆች እንዲያውቁ ለመርዳት ይሄ ትምህርት ለእነዚሁ ሰዎች ጭምር የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህም ሌላ ይህቺው ቤተክርስቲያን የነበራት የእግዚአብሔር ቃል አቋምና መሠረት ትክክለኛ ከመሆኑ የተነሳ ለብዙ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሳይቀር የመነሻ ምክንያት እና ምንጭ መሆንዋን ፣ እንደገናም ይህቺ ቤተክርስቲያን የሀገር ባለውለታም ከመሆንዋ ባሻገር ስለ ሀገር ስናስብ ስለዚህች ቤተክርስቲያን ጭምር ልናስብ ግድ እንደምንሰኝ እነዚህ ትምህርቶች የሚጠቁሙ ናቸው :: ስለዚህ ይህቺ ቤተክርስቲያን አሁን ላይ የሚያስፈልጋት መንፈሳዊ የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ እንጂ መቃጠል ባለመሆኑ ሕልውናዋን ከገጸ ምድር ለማጥፋት ሲሉ በእንዲህ ዓይነቱ ክፉ እርምጃ ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ ይህንን እርምጃቸውን እግዚአብሔር እንደማይደግፈውና እነርሱም እንደሚጎዱበት ትምህርቱ ያመላክታል :: ለማንኛውም ስለ ቤተክርስቲያኒቱ አነሳስና ሥረ መሠረት በውስጥዋም ያለውን መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ የሚጠቁሙ ማሳያዎችን ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት ለተከታታይነት አዘጋጅቻለሁ :: ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ማወቅ ለምትፈልጉ ሁሉ እነዚህ ትምህርቶች በብዙ ይጠቅሟችኋል ብዬ አስባለሁ :: ይሄ አሁን የለቀኩት የክፍል አንድን ትምህርት ነው :: የክፍል ሁለትና ቀጣዮቹም በሚቀጥሉት ጊዜያት በየተራ ይለቀቃሉ :: አሁን ግን በዚህ የክፍል አንድ ትምህርት ተባረኩ እላለሁ :: ከዚህም ባሻገር ጌታ ቢረዳንና ብንኖርና የአቶ ተፈራንና የባለቤታቸውን የወይዘሮ በላይነሽን የ60 ዓመት የክርስትና ጉዞና የትዳር ሕይወት ምን እንደሚመስል በምስክርነት መልክ በነገው ዕለት 10 AM ላይ ይዤ እቀርባለሁ :: በጸሎታችሁ አስቡን ፣ ጸልዩልን :: ሰዎችንም መጋበዝ አትርሱ :: አሁን ግን በዚህ ትምህርት ተባረኩ :: አባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ

Wednesday 11 September 2019

እንኩዋን አደረሳችሁ 2012 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንቁጣጣሽ የክፍል አንድ ዝግጅትወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም ወይረውዩ አድባረ በድው በቸርነትሕ ዓመትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ መዝሙር 64 ( 65 ) ፥ 9 - 13 የተወደዳችሁ ወገኖች ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን እንኩዋን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ አዲሱ ዓመት የበረከት የተድላና የደስታ ዓመት ይሁንላችሁ በማለት ምኞቴን እየገለጽኩ ዘመን የሚለወጥበት የመስከረም ወር ዘር ዘርተው ተክል ተክለው የሚኖሩ ሐረስተ ምድር በክረምት የዘሩትን ዘር አሽቶ አፍርቶ ምድርም በልምላሜ ተጊጣ እንስሳትም ለምለሙን ሣር ግጠው ጽሩውን ውኃ ተጎንጭተው ጠግበው አምረው የሚታዩበት የልምላሜ የፍሬ ወር ነው። “ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ እንዲሁ ታሰናዳለህና ትልምዋን ታረካለህ፥ ቦይዋንም ታስተካክላለህ፤ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥ ቡቃያዋንም ትባርካለህ ይለናልና ስለዚህ ዓመታቱን በቸርነቱ የለወጠ የበረከት እጁንም ሳያጥፍ ፍጥረትን ሁሉ የመገበ የሠራዊቱ ጌታ እግዚአብሔር ስሙ የተባረከ ይሁን ከዚህ በመቀጠል ይህንን የተለቀቀ የእንቁጣጣሽን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ የክፍል አንድ መልዕክት ተከታተሉ ተባረኩ