Saturday 13 July 2019

ክፍል ሁለት: ከ #Global_Faith_Mission_Ministries መስራችና ባለራዕይ ፓስተር ሜሮን ወ/ሐዋሪያት...በመጋቢ ሜሮን ወልደ ሐዋርያት የሚገርም የእምነት ማብራርያና በጸጋ የመኖር ጥቅም ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ምን እንደሆነ ፣ ቅድስናንም በተመለከተ በእግዚአብሔር ጸጋ ነው የምንቀደሰው ፣ ቅዱሳን ስለሆንን ባሕርያችን ስለሆነ በቅድስና እንኖራለን ለዚህም ቅድስና ሁልጊዜ ራሳችንን እንሰጣለን የቅድስናን ሕይወት የሚያስከትል የእግዚአብሔር ጸጋ ነው የክፍል ሁለት ድንቅ ትምህርት ነበር ስሙትና ተባረኩበት ባርያውን እግዚአብሔር ይባርከው ለዘመኑ ፣ ለትውልዱ መታነጽ እግዚአብሔር የቀሰቀሰው የእግዚአብሔር ሰው ስለሆነ እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች በመባረክና ጸጋቸውንም በመካፈል መባረክ አለ ተባረኩ

የመልዕክት ርዕስ ፦ የተቋረጠው ነገር በነበረው በዚያው ክብር ይቀጥላል ( ዘፍጥረት 18 : 9 - 15 ) የመልዕክት ርዕስ ፦ የተቋረጠው ነገር በነበረው በዚያው ክብር ይቀጥላል ( ዘፍጥረት 18 : 9 - 15 ) ለሀገር እንዲሁም ለቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት ነው በዚህ ውስጥ ሀገራችን አሁን ካለችበት ችግር እንድትወጣ ፣ የሀገር መሪዎቻችንም መንፈሳዊ ጉልበትንና አቅምን ከእግዚአብሔር እንዲያገኙ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር የሆነ መነቃቃትና ፈውስ እንዲሆን ጸሎት ተደርጓል ስለዚህ ይህን መልዕክት ሰምታችሁ ከዚህ የምልጃና የልመና ጸሎት ጋር አብራችሁ በመሆንና በመጸለይም ሀገራችሁን ቤተክርስቲያናችሁንም ሆነ ትውልድን ጥቀሙ ተባረኩበት የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ ቆሞስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Monday 8 July 2019

ርዕስ፦ በሰዎች ካልተወሰንክና ራስህንም ካልወሰንክ እግዚአብሔር ስላንተ የተናገረውን አንተንም የተመለከተበትን እይታ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ መልዕክት እንደሰማችሁት ዳዊትን አባቱ ታናሽ ነው በጎችን ይጠብቃል አለው ፣ የወንድሞቹንም ደህንነት እንዲጠይቅና ወሬንም እንዲያመጣለት ላከው :: የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤልያብ ደግሞ በጎችን ለማን ተውካቸው ? የልብህን ኩራት አይቻለው ሲል ተቆጣው ፣ አሳነሰው :: ሳኦል ደግሞ አንተ ብላቴና ነህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመዋጋት ትሔድ ዘንድ አትችልም አለው :: ጎልያድም ዳዊትን ትኩር ብሎ አየውና ብላቴና መልኩም ያማረ ነበርና ናቀው :: ከዳዊት የድሉ መልስ በኋላ ደግሞ ሳኦል ዮናታንን የሞት ልጅ ነውና ልከህ አስመጣው አለው ፣ ይህም አልበቃ ብሎት ዳዊትን አዋረደው ፣ በዚህ ሁሉ አልሸነፍ ሲል ደግሞ ሳኦል ዳዊትን አጥብቆ ፈራው ፣ ዕድሜውንም ሁሉ ለዳዊት ጠላት ሆነው :: እግዚአብሔር ግን ዳዊትን እንደ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከተው :: የተወደዳችሁ ወገኖቼ እግዚአብሔር እንደ ባለ ማዕረግ ሰው ነውና የሚመለከተን ሰዎች በሚያዩን ዓይን ሳይሆን እግዚአብሔር በሚያየን ዓይን ራሳችንን እንመልከት :: በሐዲሱ ኪዳንም እንደ ባለማዕረግ ሆነን የታየንበት እውነት ወደ ክብር የመጣንበት እውነት ነው :: መጽሐፍቅዱስ እንዲህ ይለናል ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና ይለናል ዕብራውያን 2 ፥ 10 - 18 ተባረኩ የቃሉ አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ