Friday 1 February 2019

የመልዕክት ርዕስ ፦ አታልቅሺ ( የሉቃስ ወንጌል  7 : 13 ፤ 11 - 17 ) የምንባቡ ኃይለ ቃል ፦ ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና አታልቅሽ አላት የሉቃስ ወንጌል  7 : 13 ፤ 11 - 17 የመልዕክት ርዕስ ፦ አታልቅሺ የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዛሬው መልዕክት በእርግጠኝነት እንደምትባረኩበት አምናለሁ :: ጌታ አታልቅሺ ፣ አታልቅስ ፣ አታልቅሱ ያለን ፤ ወደፊትም ይሄ ሁኔታ በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ የሚለን ቀጥሎ ለእኛ ለልጆቹ ያለውንና ያሰበውን መልካም ነገር ስለሚያደርግ ነው ስለዚህ ጌታችን እንዲሁ እንደ ሰው በአፉ ይህንን ለማለት ብቻ ወይንም እንዲሁ ማለት ስላለበት አታልቅሺ ፣ አታልቅስ ፣ አታልቅሱ ያለን አይደለም ፣ ወደፊትም አይለንም :: ታድያ ይህቺንም መበለት በልጅዋ ሞት አዝኖላት አታልቅሺ ሲላት ለማለት ብቻ ያለ ሳይሆን ቀጣዩን የልጅዋን ነገር ከቃሬዛ ላይ የማስነሳትና መልሶም ለእርስዋ የማስረከብን ተግባር ሊያከናውንላት ወዶ ነው ደግሞም አከናወነላት :: ስለዚህ ወገኖቼ እንዲሁ እንደዚህች መበለት እኛም በአስከፊው ጉዳዮቻችን ዙርያ አልቅሰን ከሆነ አታልቅሱ ይበለን :: አታልቅሱ ያለን ጌታ ቀጣዩን ነገር በሕይወታችን ያለመከልከል ያደርጋል :: ውድ ወገኖቼ ሆይ በዚህ ውስጥ ታድያ እኛም እንደዚህች መበለት በዚህ ደግ ጌታ ተጽናንተን ከሆነ ማጽናናቱን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም ተግሣጹንም ጭምር መቀበል አስፈላጊያችን እንደሆነ ማመን አለብን:: ለዚህም ነው ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል ያለን :: ለበለጠ መረጃ ቪዲዮውን ደግማችሁ ስሙት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት

No comments:

Post a Comment