Tuesday 12 February 2019

የመልዕክት ርዕስ ፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁንየመልዕክት ርዕስ ፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን መጽሐፈ ሩት 1 : 19 - 22 ፤ መጽሐፈ ሩት 2 : 20 የተወደዳችሁ ወገኖችና የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ተንከራታች የሆነችዋ ኑኃሚን ፣ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና ባዶዬን መለሰኝ ስለዚህ ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ ስትል ስሟን ሳይቀር መለወጥ የፈለገችው ኑኃሚን ፣ እንደገና ተመልሳ « በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረግን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው » በማለት የበጎነት አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን አንስታ ቦዔዝን የባረከችበትን ምስጢር ዛሬ ተመልክተናል ከዚህ የተነሳ ኑኃሚን በእግዚአብሔር ቸርነት ታግዛ ከእንዲህ ዓይነቱ የተስፋ መቁረጥ ሕይወት ነጻ የወጣችበትን የሚጠቁሙ ተዛማጅ ቃሎችን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁና ተከታተሉ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም እግዚአብሔርን አሰብሁት ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች ዓይኖቼ እንዲተጉ ያዝሃቸው፤ ደነገጥሁ አልተናገርሁም የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፤ የዘላለሙን ዓመታት አሰብሁ፤ አጠናጠንሁም በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት እግዚአብሔር ለዘላለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን? ለዘላለምስ ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ተቈረጠችን? የተናገረውስ ቃል አልቆአልን? እግዚአብሔርስ ሞገሱን ረሳን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን? ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ እንደ ተለወጠ የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤ የቀደመውን ተአምራትህን አስታወሳለሁና በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? ተኣምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ ለሕዝብህ ኃይልን አስታወቅሃቸው ( መዝሙረ ዳዊት  77 : 1 - 14 )   እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም ( መዝሙረ ዳዊት 103 : 10 ) ሁለታችሁን ከማጣ ተብሎ በእናቱ አማካኝነት ወደ አጎቱ ቤት የተላከ በአጎቱም በላባ ቤት ደሞዙ የተለዋወጠና የተነጠቀ ያዕቆብ ከመከራው ብዛት የተነሳ ሥፍራ ሳይለውጥ በዛው በአጎቱ ቤት እንዳለ እግዚአብሔር በሕይወቱ ጣልቃ ገብቶ ቸርነትን አደረገለት ስለዚህም የላባ ልጆች ይህን አሉት ያዕቆብም የሚከተለውን ሃሳብ ሰነዘረ ( ዘፍጥረት 31 : 5 - 14 ፤ 42 ) ከወንድሙም ጋር ተገናኝቶ እንዲህ ሲል ተናገረ ( ዘፍጥረት 33 : 11 ) ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት ( የዮሐንስ ወንጌል  4 : 10 ) የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ ( 2ኛ ቆሮንቶስ   8 : 9 ) እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው ቃሉ የታመነ ነው ( ቲቶ  3 : 3 - 8 ) እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው ስለዚህ፥ እነሆ፦ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚእግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን፦ የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን አገርና ካሰደድኋቸውም አገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል በምድራቸውም ይቀመጣሉ ( ትንቢተ ኤርምያስ  23 : 5 - 6 ) ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ  

No comments:

Post a Comment