Friday 15 February 2019

በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥ...በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተሰግስገው የገቡ ፣ እግዚአብሔርን የተኩ ፣ የአማልክት አምልኮዎች ( ክፍል ሰባት ) ( ቊጥር 13 ) እርሱም ሁሉንም እክዳለሁ ማርያምን ግን አልክድም አለ!!! የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን በተአምረ ማርያም 110 ቁጥር 7 ላይ ጥብርያዶስ ስለሚባል ስለ አንድ ነጋዴ ይናገራል :: ይህንንም የምታገኙት በተአምረ ማርያም 123ኛው እትም ላይ ነው :: ይህ ጥብርያዶስ ሃብታም የነበረ ነጋዴ ነበርና ወንድና ሴት ባሮች ነበሩት :: ይሁን እንጂ ሃብታም ቢሆንም በሃብቱ ደኸየ ታድያ ሰይጣን በድህነቱ መጥቶ ሥላሴን ክርስቶስን ማርያምን ካድ አለው:: እርሱም ሁሉንም እክዳለሁ ማርያምን ግን አልክድም አለ:: በዚህ ሁኔታ የሚሞትበት ጊዜ መጥቶ ማርያምም እንደ ልማድዋ መጣችለትና ልጅዋ ወዳጅዋን ይህን ሰው የማትምርልኝ ከሆነ ጡቶቼን እቆርጣለሁ ፊቴንም እቆራርጣለሁ አለችው :: እርሱም ስለዚህ ነገርዋ ማረላት ይለናል :: በመሆኑም ታድያ ይሄ መጽሐፍ አቅሉን የሳተ የሰይጣን መጽሐፍ መሆኑን የምናውቅባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው :: አንደኛ ማርያም ማርልኝ አለበለዚያ ጡቴን እቆርጣቸዋለሁ የምትለው በሰማይ የክርስቶስን ጽኑ ፍርድ በማስፈራራት ልጅዋን ልታስለውጥ ብላ ነው ይለናል መጽሐፉ :: ሌላው ደግሞ አሁንም መጽሐፉ ማርያምን ጡትዋን የምትቆርጥበትን ቢላዋ ፣ ሰይፍም ይሁን መቀስ ይዛለች እያለን ነው:: ታድያ በሰማይ ጡትም ሆነ ጡት የሚቆረጥበት ቢላዋ ሰይፍም ሆነ መቀስ አለን ? ይህ ደግሞ ከትንሣኤ በሁዋላ ስለሆነ ፍጥረታዊ ሰውነት የለምና ማርያምን ጡት ነበራት ስንል ልንናገር አንደፍርም :: ከዚህም ሌላ ይህም ሰው ክርስቶስንና ሥላሴን ክዶ ማርያምን አልክድም ስላለ በማርያም ኢየሱስን አስፈራሪነት ምህረት አገኘ ልንል አንችልም :: ኢየሱስ እንዲህ በቀላሉ ፍርዱንም ሆነ ሃሳቡን የሚለውጥ ጌታ አይደለም ትክክለኛዋ የኢየሱስ እናት ማርያምም ሰዎች ሁሉ ለኢየሱስ እንዲታዘዙና የዘላለም ሕይወት ባለቤቶች እንዲሆኑ የሚላችሁን አድርጉ ትላለች እንጂ በሰማይ መቀስ ይዛ ይህንን ሰው ካልማርክልኝ ጡቴን እቆርጣቸዋለሁ የሚል ቃል በማውጣት ኢየሱስን አላስፈራራችም ፣ አታስፈራራውምም ፣ አስፈራርታም ፍርዱን አላስለወጠችውም ፣ ወደፊትም አታስለውጠውም ይልቁንም እርስዋ ራስዋ በክርስቶስ ኢየሱስ አምና የዳነች አማኝ በመሆንዋ ይህንን የጨለማ ሃሳብ ጨርሶውንም አታስበውም :: የተወደዳችሁ ወገኖች በዛሬው ትምህርታችን እንግዲህ ይህንን የተአምረ ማርያም የትረካ ሃሳብ አንስተን ኦርቶዶክሳውያኑ ወገኖቻችን በመጽሐፍቅዱስ ላይ የተጻፈላትን ማርያምን ከማመን ይልቅ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፈላትን ማርያም በማመናቸው ምክንያት የሚቸገሩበትን ወደ ሁለት የሚደርሱ ነጥቦች በየተራ ተመልክተናል:: 1ኛ ) ማርያምን መካድ የሚፈልግ ሰው ማንም ባይኖርም ኦርቶዶክሳውያኑ ግን ማርያምን አንክድም የምንለው ትልቁ ምክንያታችን ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም ብለን ስለምናምን ነው ብለው ይረዳሉ ደግሞም ይናገራሉ 2ኛ ) ያለ እመቤታችን ማርያም ሥላሴ አይታወቅም ይላሉ ታድያ እኛም እነዚህን ሁለት ነጥቦች አንስተን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዳኝተነዋል የተለቀቀውን ቪድዮ በመስማት ትምህርቱን ተከታተሉ ታድያ አሁንም ትምህርቱ ያላለቀ በመሆኑ ተከታዩን በሚቀጥለው አቀርባለሁ እስከዚያው የጌታ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን የምላችሁ ወንድማችሁ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ተባረኩልኝ

No comments:

Post a Comment