Thursday 23 February 2017



የግጥም መነባንብ 




የግጥሙ ርዕስ   መብራቱ አይጠፋም










Image result for the lamp of god had not yet gone out and samuel was



የግጥም መነባንብ 




የግጥሙ ርዕስ   መብራቱ አይጠፋም



የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ነገ ማለዳ  በካናዳ ኦታዋ የሰዓት አቆጣጠር 10 ሰዓት 10:00 In the morning ላይ የሚጀምር እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ 15 የትምህርት ክፍለ ጊዜ ላይ ደርሰናልና ይህንን ትምህርት ይዤላችሁ በሰዓቴ እቀርባለሁ አምናለሁ ጌታ መንፈስቅዱስ ጥሩ ጊዜ ሰጥቶን በቃሉ ይገነባናል ትምህርቱ በፌስቡክ ላይቭ ነውና የሚተላለፈው ሳያመልጣችሁ በመስመሩ ላይ ገብታችሁ እንድትከታተሉ ላበረታታችሁ በጌታ ፍቅር እወዳለሁ ተባረኩልኝ ደግሞም በጌታ ወገኖቼ የሆናችሁትን የፕሮግራሜ ታዳሚዎችና ተከታታዮች ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ አከብራችኋለሁ ደግሞም እጸልይላችኋለሁ እናንተም ለዚህ አገልግሎት ጸልዩ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከዚህ በመቀጠል ግን ለነገው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንደ መሰናዶ ወይንም እንደ ማነቃቂያ የምትሆን እኔ ጋር ምሽት ስለሆነ ከሽ ከሽ የምታረጓትንና የምታጣጥሟትን እንደ እስናክ የእራት መክሰስ ዓይነት የሆነች አጠር ብላ እየጣፈጠች ወደ ውስጥ የምትገባ ግጥም  እነሆ ብያለሁ አንብቧት _________________

የግጥሙ ርዕስ መብራቱ አይጠፋም የሚል ነው 



 መብራቱ አይጠፋም 



ይለኮሳል እንጂ መብራቱ አይጠፋም 

የሚቀሰቀሰው ሳሙኤል አልተኛም 

የነኤሊ ዓይኖች ማየት ሲሳናቸው 

በኃጢአት በድካም የፈዘዙ ሆነው 

አጥርቶ የሚያይን ጌታ ያዘጋጃል 

መቅደስ የተኛውን ሳሙኤልን አይቷል 

ብርቅ የሆነውም ቃል የእግዚአብሔሩ 

ሊገለጥ ሊነገር በሀገር በምድሩ 

ጊዜው ደረሰና ሳሙኤል ተጠርቶ 

እነሆኝ እያለ ከተኛበት ነቅቶ 

ቃሉ በቤርሳቤህ በዳን ሲደርስለት 

ሳሙኤል ሆይ አንተ ነቢይ ነህ አሉት 

አውቀውት አምነውት ተስማምተውም ጠሩት 

ከስማችን በፊት መልዕክቱ ሲደርስ

የተላከ ሆኖ በመንፈስቅዱስ 

ተብለን ልንጠራ ለሰዎች ሳይቸግር 

ሐዋርያ ነቢይ መጋቢ አምባሳደር 

ሊጠሩን ሲነሱ በሙሉ አፋቸው 

ያለማስታወቅያ ፈቃደኛ ሆነው 

ጸጋችን ተገልጦ ለሰው የሚታየው 

ያን ጊዜ ጌታችን ከፍ ብሎ ይከብራል 

ምስጋናን ሊቀበል በምድር ይነግሣል 

ከዕንቅብ በታች ሆኖ የጋን ውስጥ መብራት 

መሆን ይቀርና ለሰው የሚያታክት

አይቀር ተደብቆ ሆኖ በልባችን 

የዓለም መድኃኒት የዓለም ብርሃን 

ይበራል ይደምቃል የጌታችን መብራት 

በእኛ ላይ ሲመጣ የመንፈሱ እሳት 

ይበራል ይደምቃል የጌታችን መብራት 

በእኛ ላይ ሲመጣ የመንፈሱ እሳት 








ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን 




Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry 



ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ 

No comments:

Post a Comment