Tuesday 21 February 2017


ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ 

አታውቁም



   


..........ለመሠል ባልንጀሮ  የተሰጠ የክፍል ሁለት መልስ 




Image result for do u want us to call  fire to come

Image result for do you want us to call fire down from heaven







……….. ለመሠል  ባልንጀሮች  የተሰጠ የክፍል ሁለት መልስ




የመልዕክቱ ዋና ኃይለ ቃል 




ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም







ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ አግበኣ ለመጥባሕትከ ውስተ ቤታ 
እስመ ኲሉ ዘይቀትል በመጥባሕት ይመውት በመጥባሕት
ወንጌል ዘማቴዎስ ምዕራፍ ፳፮ ቊጥር ፶፪




በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው ፦ ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና
ሰይፍህን ወደ ሥፍራው መልስ
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 26 ቊጥር 52





ወወድቀ ዲበ ምድር ወሰምዐ ቃለ ዘይቤሎ ፦——
ሳውል ሳውል ለምንት ትሰድደኒ ይብእስከ ረጊጽ ውስተ ቀኖት በሊሕ ( ግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ ፱  ቊጥር ፬ )
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9 ቊጥር 4




Image result for the son of man came to seek and save the lost





እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና ፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 55 እና 56 




የተወደዳችሁ ወገኖቼ በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ እያልኩኝ ለዛሬ ለእናንተ ለአንባቢዎች ወዳዘጋጀሁት መልዕክት አልፋለሁ በመምሕር ምሕረተ አብ ጉዳይ ላይ ወንድሜ ባለመረዳት ባዘጋጀውና ተነሣ ሕዝቤ ተነሣ የጥንቱ እንዳይረሳ ሲል በቪዲዮ በለቀቀው የክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት የአዋጅ መልዕክቱ ከእኔም ሆነ እኔን ከመሠሉ ወንድሞቼ ተገቢ የሆነ መልስ መሰጠቱ ይታወሳል ይሁን እንጂ  ምሕረተአብን  ቊርጥ  የሆኑ ናቸው ባንልም ምሕረተ አብን የመሠሉ ፣ ምሕረተ አብ መሠል  ፣ መሣዮች ፣ ተመሣሣዮች ወይንም  ልዩነት የሌላቸው ባልደረቦች  ልንላቸው እንችላለን  በየቤተ እምነቱ አይጠፉምና ብዕሬን በምሕረተ አብ ላይ ብቻ ለበጐ በሆነ እውነትና ለመመለስ በሆነ ቃል ሳላሳርፍ እርሱን ለመሠሉ ባልንጀሮቹና  ተመሳሳዮቹ ሁሉ መልዕክቴ አንድ ብላ እንድትደርስ ለእናንተ ለአንባቢዎች  እነሆ ብያለሁ እና ተከታተሉ  ተመሣሣዮችን ወይም ልዩነት የሌላቸው ቢጤዎችን የግድ በአንድ  ክልል ፣ መንደርና ሠፈር ውስጥ   ማየት እንደገናም እንፈልግ ብለን ስንነሳ ደግሞ   በዚሁ ሠፈርና መንደር  ውስጥ መፈለግም ሆነ ፈልገን ማግኘት አይጠበቅብንም  ተመሣሣዮችን ከሚመሣሠሉበት ነገር ተነስተን በአንድ ካታጐሪ ውስጥ ካታጐራይዝድ አድርገን ብንመድባቸውና ብናስቀምጣቸውም መገኛቸው ግን በልዩ ልዩ ቦታ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎችና ሀገሮች እንደገናም በተለያዩ የቤተ እምነት  ተቋሞች ፣ ድርጅቶች ፣ በየሰፈሩ  በየመንደሩ ውስጥ ሳይቀር ልናገኛቸው እንችላለን ለዚህ አባባሌ በዮሐንስ ወንጌል 9 ፥ 8 _ 12 ላይ  ጥሩ ምሳሌ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን የዚህን ዓይነ ሥውር ሰው ታሪክ ወደ እናንተ ማቅረብ ወደድኩኝ  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና ሂድና በሰሊሆም መጠመቅያ ታጠብ አለው ትርጓሜው የተላከ ነው ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ ይለናል ወገኖቼ የሚፈለገው ግን የዚህ ዓይነ ሥውር ማየቱ ነውና በማየቱ ማለትም እያየ ስለመጣ ደስ ይበለን  ይሁን እንጂ አንዳንዶች ጐረቤቶቹ የዚህን ሰው ማየት ያልሰሙና ያላወቁ በመሆናቸው መልኩ ሳይቀር ጠፍቶባቸው የከረመ ሆኖባቸዋል ነገር ግን አንዳንዶቹ ደግሞ ቀድሞ ሲለምን አይተውት የነበሩ  በመሆናቸው ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን ? አሉ ሌሎች ደግሞ አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ አሉ ያንጊዜ እርሱም እኔ ነኝ አለ እነርሱም ታድያ ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ ?ቢሉት የሆነለትን ነገር ተራ በተራ ዘርዝሮ መናገር ጀመረ ይህ ሰው ታድያ ከፊተኛው ማንነቱ  ይልቅ ዛሬ ላይ ባለ ሕይወቱ ጐረቤቶቹን ሳይቀር ማደናገር የቻለው ዓይን በማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ባገኘው ዓይን ለማየት  በመቻሉም ጭምር ነው  ወገኖቼ ቢደናገር ቢደናገር ሌላ ይደናገር እንጂ ጐረቤት ግን ይደናገራል ፣ ይጠፋዋል ብለን ልንገምት አንችልም ጐረቤት ማለት የውስጥ ገበናን እንኳ ሙሉ ለሙሉ ያውቃል ባንልም ቢያንስ የቅርብ ሰው  እና ጐረቤታችንም ስለሆነ  ስለ እኛ የሚያውቃቸው አንዳንድ የውስጥ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ መጽሐፍቅዱሳችን በ1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥  12  ላይ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን ይለናል ታድያ አብርሃም በኬጢ ሰዎች መካከል ሲኖር ኑሮው መልካም ስለነበረ ሚስቱ ሣራ በሞተችበት ጊዜ እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛ እና መጻተኛ ሰው ነኝ በእናንተ ዘንድ የመቃብር ርስት ስጡኝ ሬሳዬንም ከፊቴ ልቅበር ሲል በጠየቀ ጊዜ የኬጢ ልጆችም ለአርብሃምም መለሱ አሉትም ፦ ጌታ ሆይ ስማን አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ ከመቃብር ሥፍራችን በመልካሙ ቦታ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም አሉት ይለናል ዘፍጥረት ምዕራፍ 23 ፥ 3 _ 7 እና ዘፍጥረት ምዕራፍ 23 ን በሙሉ አንብቡት ታድያ አብርሃምን ለኬጢ ሰዎች ማን አለቃ አደረገው ? ስንል መልሳችን ባጭሩ የኑሮው መልካምነት አለቃ አደረገው ነው ስለዚህ አብርሃም ከኬጢ ሰዎች ጋር አብሮ ሲኖር ዝም ብሎ ዓይነት በሆነ የተመሣሣይ  ጉርብትና ቡና ጠጡ ሲል እየጠራ፣ እየተጠራና እየተጠራራ እየጠጣ ፣ እያጣጣና  እየተጣጣ አልነበረም የኖረው ስለዚህ አብርሃም ከኬጢ ሰዎች ጋር በአንድ ዓይነት የኑሮ ሁኔታ የተመላለሰ ስላልነበረ የሰዶም ሰዎች የአጐቱን ልጅ ሎጥን በርህን ክፈት ሲሉት እንደተጋፉት አብርሃምን ግን  የተጋፋ  አንድም  የኬጢ ሰው አልነበረም እነዚህ የኬጢ ሰዎች አብርሃምን ያሉት አንድና አንድ ነገር ቢኖር  አሁንም ጌታ ሆይ ስማን አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ ከመቃብር ሥፍራችን በመልካሙ ቦታ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም ነው ለእኛም እንደ ሎጥ ሳይሆን እንዲሁ እንደ አብርሃም ባለ የከፍታ ሕይወት ምልልሳችን ምክንያት ለሌሎች መልካም ሆነን መልካም በሆነው የበረከት ቃል ወደ እኛ መጥተው የሚባርኩንንና እኛም የምንባረክባቸውን ሰዎች ይስጠን  የኑሮ መልካምነት መልካም ጉርብትናንና ጥሩ ስምን ብቻ  የሚያተርፍልን አይደለም የሚያዩን ሰዎች ከዚያ ባሻገር ባለ ነገር ሁሉ ሰላማቸውን የሚያስጠብቅ በጎ ነገር በእኛ በእያንዳንዳችን ሕይወት ከማየታቸው የተነሣ  ለአብርሃም የሰጡትን ከእግዚአብሔር የሆነ አለቅነትና የመቃብር ሥፍራ ዓይነት ለእኛም በእኛ ዘመን ያሉ የኬጢ ዓይነት ሰዎች ልዩ ልዩ ስጦታዎቻቸውን በምንፈልገው መጠን ሊሰጡን ዝግጁዎች ናቸው በእርግጠኝነትም ሳይከለክሉን ይሰጡናል የመንፈሳዊ ሕይወት ለውጥ ትርጉሙና ከሌላውም ጋር   በልዩነት የሚያስቀምጠን ምስጢሩም ሆነ መንገዱ እንግዲህ ይሄ ነው  ያው አንድ ዓይነት ሆነን ልዩነት ያላሳየን ጎረቤቶች ከሆንን ግን የሎጥ በሰዶም ሰዎች ፊት ያጋጠመው ዕጣ ፈንታ ሳንጠራጠር በእርግጠኝነት የእኛም  ይሆናል ዘፍጥረት 19 ፥ 1 _ 11 ይህም ሁኔታ ያለጥርጥር በሕይወታችን ይደርስብናል  ከዚህ ውጪ ወይንም ከዚያ ያለፈ ሌላ ምንም መሆን አንችልም  ከዚህ በመቀጠል   መጀመርያ ላይ ወዳነሳሁት ዕውር ሆኖ ወደ ተወለደው ሰው ታሪክ ስመልሳችሁ የዚህ ሰው ዓይን ማግኘትና ማየት ታድያ ለቅርቦቹ ማለትም ለአንዳንዶች ጐረቤቶች ሳይቀር እርሱ ነው አይደለም እርሱን ይመስላል በሚሉ አወዛጋቢ ቃላት ግራ ያጋባ ነበር እኛም ወገኖቼ ታድያ እንደዚህ ዓይነ ሥውር ዓይናችን በርቶ ማየት ስንችልና ለውጥ በሕይወታችን ሲመጣ አይደለም በሩቅ ለሚያውቀን ሰው  የቅርብ ሰዋችን ለሆነው ፣ ቡና ለሚያጣጣንና የቤታችን ጓዳ ድረስ ገብቶ ገበናችንን ሳይቀር ለሚያውቀው ሰው ሁሉ ለውጣችን እርሱ ነው እርሱ አይደለም እርሱን ይመስላል እርሷ ነች እርስዋ አይደለችም እርስዋን ትመስላለች እርሳቸው ናቸው እርሳቸው አይደሉም እርሳቸውን ይመስላሉ እነርሱ ናቸው እነርሱ አይደሉም እነርሱን ይመስላሉ እያስባለ   በማያደናግርና ግራም በማያጋባ መልኩ ትክክለኛውን እኛነታችንን እና የተለወጠውን ማንነታችን  ሊያሳያቸው ይገባል እላለሁ   በተለይ የቅርቡ ሰው ማለትም ጐረቤቱ ለውጡን ያወቀለት ሰው እንዴት ጌታ የረዳውና የታደለ ሰው  መሠላችሁ የእኛ ትክክለኛ  የሆነው ለውጣችን የሚታወቀው ደግሞ አጠገባችን ባለ ሰውና ጐረቤታችንም በሆነው ሰው ምስክርነት ነው ስለዚህ ስለሕይወታችን የመለወጥ ጉዳይ ዛሬ ታድያ ጐረቤቱም ሆነ በቅርቡ የሚያውቀን ምን ይል ይሆን ? ለአብርሃም ከኬጢ ሰዎች የተሰጠው መልስ ዛሬ ላይ ለእኛ ሆኖና እኛም ለዚህ በቅተን ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ የምትከለከሉትም ሆነ የምታጡት ነገር የለም እንባላለን ? ወይስ በተቃራኒው እናንተስ ከእግዚአብሔር አይደላችሑም ስንባል ሎጥን ሊገፉት ከደጅና ከበር ውጪ ባሉ ሰዎች መግፋትና መጋፋት የእኔ ፣ የአንተ ፣ የአንቺ ፣ የእኛ ፣ የእናንተ የሁላችን የምንለውን በር ለመስበር በሆነ የመገፋፋት ሕይወት ውስጥ እንኖራለን ? መልሱን እንግዲህ ለእኔ ለጻፍኩትም ሆነ ለእናንተ ለአንባቢዎች የምተወው ይሆናል ይሁን እንጂ  ለብዙዎቻችን የሕይወት መለወጥ ጐረቤት የሚሰጠው ምላሽ ዛሬ ላይ ሆነን ስንሰማው  እርሱ ነው እርሱ አይደለም እርሱን ይመስላል የሚል ሳይሆን   ትላንትናና ከዚያ በፊት ከድሮም ጀምሮ የምናውቀው ያው እርሱ ነው ምንም የተለወጠ ነገር አላየንበትም ፣ አልተሻሻለም ፣ አልተቀየረም ለምን እንዲሁ ትዳክማላችሁ ? እርሱ እንደሆነ ክርስቶስ ቢመጣም እንኳ የሚቀየር ዓይነት ሰው አይደለምና ባወጣው ያውጣው ተዉት  የሚል መልስ  ነው ሲሰጥ  የምንሰማው እንደው እንበልና ሀገር ቀይረን፣ ዓመታት ቆይተን ተመልሰን እዚያው የድሮው ቦታችን ብንሄድ እንኳ ግልጽ የሆነና ይሉኝታም የማያውቅ አንዳንዱ ሲያገኘን ኡኡኡ መሻሻል የለም እንዴ ? ያው ነህ እኮ እንደውም ብሶብህ ነው የመጣኸው ነው  የሚለንና ስለዚህ ለውጥ የሌለው ሕይወትም ሆነ ክርስትና እንዲሁም በመድረክ የሆነ የአገልግሎት ግርታ  በአብዛኛው በእኛም ሆነ በሌሎች   ሕይወት እጅግ በጣም አጠያያቂ እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል ከዚህም ሌላ ጉድለት የሞላበት ሕይወታችንንና ያልተለወጠው እኛነታችንን ያዩ አንዳንንድ ሰዎች አምላካችን እግዚአብሔር በሁሉም ዘንድ የተከበረ ሆኖ  ሳለ እነዚህ ሰዎች ግን በእኛ ያለውን እግዚአብሔርን አያከብሩትም  ሮሜ 2 ፥ 17 _ 24  ለዚህም ነው እንግዲህ አብዛኞቹ ሊቀበሉን ይቸገሩና እናንተ ከእኛ በምን ትሻላላችሁ ? የሚሉን እነርሱ ጋር የሚታየው ነገር በሙሉ እኛም ጋ አለና አንድ ስሙን መጥቀስ የማያስፈልገኝ ወንጌላዊ ሥፍራ ቀየርክ እንጂ ሕይወትህ አልተቀየረም  በፊት በቀድሞ ሕይወትህ እዚያ ታጭበረብር ነበረ አሁን ደግሞ አመንኩ ሕይወቴ ተቀየረና   የመሣሠሉትን ሆንኩ ትላለህ ብሶብህ ግን ታጭበረብራለህ ሲል ተናገረ ስለዚህ ወገኖቼ ዛሬ ለእኛም የሚያስፈልገን የስፍራ ለውጥ ሳይሆን የሕይወት ለውጥ ነው ሕይወታችን ሊለወጥ ያስፈልጋል ሕይወታችን ሲለወጥ አገልግሎታችን ይለወጣል ከዛ ውጪ ግን ሁሉም ነገር  ድካም ነው  አንዳንዶቻችንማ ዓይን ያወጣ ጥፋት ላይ ስላለን ክፋታችንን የሚገልጥብንና እውነቱንም የሚነግረንን ሰው አንወድም ከዚህ የተነሣ መምህር የሚለውን ስም ለብሶ  የሀገሬ ሰው ምሕረተአብ በግላጭ እንዳደረገው እኛም ለይቶልን እንደ ምሕረተ አብ መምህሩ ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት ስንል በየቪዲዮዎችና የማሰራጫ አውታሮች አንናገር እንጂ ልዩ ልዩ ትላልቅና ጃይንት የሆኑ የአገልግሎት ስሞችን ለብሰን በስማችን እያስፈራራንና ሥልጣናችንንም ተገን አድርገን ውስጥ ውስጡን ጓዳ ለጓዳ ሾተላችንና ስለታችንን የምንስል እንደገናም እኔን አይመስልም ፣ የኔን ሃሳብ አይቀበልም ፣ ስለኔም መልካም አይናገርም ስንል የምናስባቸውን ሰዎች ስም በማጥፋት አብዝተን የምናሳዽድ ፣ የምንጠላ ፣ የምንነድፍ ፣ የምንወጋ  ጥቂቶች አይደለንም  ሰይፋችንም ወደ ሥፍራው አልተመለሰም መጽሐፍ ያልተቀበልከውስ ምን አለህ የተቀበልክ ከሆንክ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለ ምንድነው ይለናልና 1ኛ ቆሮንቶስ 4 ፥ 7 ከዘለዓለም ሕይወት ጀምሮ እስከ አገልግሎት የጸጋ ስጦታ ድረስ ያሉት ስጦታዎችና ሌሎች የበረከት  ስጦታዎች በሙሉ የእኛ ሳይሆኑ የጌታ ናቸው ታድያ የእኛ ባልሆኑ በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ጌታ ወደ እኛ መጥቶ እኛ ግን ምንም እንዳልተቀበልን በመሆን  በተራ ማንነትና በዓለማዊ ኑሮ ተጠላልፈን አይደለም የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለን ልንጠራ አሁን ላይ ባለማወቅ ሕይወትና በሃይማኖት ቅነት ተይዘው ከሚያሳድዹት  ከነምሕረተአብ ባልተለየና ባልተናነሰ ሁኔታ ውስጥ አለን  በጥቂቱ ምናልባትም የቦታና የአለባበስ ልዩነት ሊኖረን ይችል ይሆናል ምክያቱም እርሱ እዚያ ነው እኛ እዚህ ነን እርሱ ያማረች መልክ ያላት ቀሚስና ባለዘለበት መስቀል እያለዋወጠ አንገቱ ላይ ያንጠለጥላል  እኛ ደግሞ ያማሩ ሱቶችን ከነከረባቶች እየለዋወጥን ሽቶአችንንም ተነስንሰን በየሰንበቱ  ልንሰብክና ልናስተምር በሕዝብ ፊት ተሰይመን እንቀርባለን  ይሁን እንጂ በቦታና በሁኔታ የተወሰንን ነንና ከሰሚዎቻችን መረዳትና የእምነት ልዩነት የተነሣ  ምንም እንኳ ስብከቶቻችን ልዩ ልዩ ዓይነት ቢሆኑም ከስብከቱና ከአገልግሎቱ መልስ ያለው ሾተላችንና ጎመዳችን ግን ፍጹም አንድ ዓይነት ነው እንደውም በየዋሕነትና በሃይማኖተኝነት ቅናት ውስጥ ተኲኖ  ከተመዘዘው ከምሕረተአብ ሰይፍ ይልቅ የእኛ ሰይፍ የባሰ ነው  አንዳንዴ እኮ እነ ምሕረተአብ ምን ያድርጉ ? እኛ በተመዘዘውና ወደ ሥፍራውም ባልተመለሰው በጴጥሮስ ሰይፍ ስለሆነ አገልግሎታችንን የምናካሂደው እነ ምሕረተአብም ከነ ሰይፋቸው ነው ያሉት ስለዚህ ማንን አይተው ሰይፋቸውን ይጣሉ ይህንኑ ሰይፋቸውን የራሴና የእኔ ብለው የያዙት ስለሆነ የራሳቸው ፣ የየግል መለያቸውና መታወቅያቸው አድርገውት   ከእኛ በተቃራኒው ቆመዋል   ወገኖቼ አገልጋዮችና የሐዲስኪዳን አማኞች በሙሉ የጴጥሮስ ሰይፍ እኮ በራሱ በጴጥሮስ ፈቃደኝነት ወደ ሥፍራው ተመለሰ እንጂ የእኛ ሰይፍማ ገና ወደ ሥፍራው ያልተመለሰ ስለሆነ ስንቱን ሰው በልቷል ፣ ስንቱን አወራርዷል ፣ የስንቱንስ ሰው ጆሮ ቆርጧል መሰላችሁ ሕዝባችን ሁሉ እኮ በእኛ ሰይፍ ተወግቶ ተቀልቶና ተቆርጦ ደምቷል ገናም እንደሚገባ ታክሞ ያላገገመ ስለሆነ  ብርቱ ቁስለኛ ነው በዚሁ በእኛው በተመዘዘበት ሰይፍ ምክንያትም በምሬት ሆኖ በልቅሶ በዋይታና በአቤቱታ ውስጥ ነው ያለው ይህ መቅላትና መቁረጥ ደግሞ ለአንዳንዶች የብሉኪዳን ሰባኪዎችና የጴጥሮስ ዘመን ሰዎች ልክ እንደ ጴጥሮስ ድንገተኛ ከሆነ የእንቅልፍ መባነን ውስጥ ወጥተው ስለሆነ የሚያገለግሉት  ጆሮ ቆራጮች ናቸው ስለሆነም በኢያሱ ዘመን ሳይቀር የተፈቀደ የሥጋ ግርዛት መስሏቸው ማገልገል ያለብን ከነ ሰይፋችን ሕዝብን እየቀለጠምንና እየቆረጥን ነው ብለው ከነሰይፋቸው ሊቀጥሉ ቢሞክሩም ታድያ  እኛ ግን ከወዲሁ ሳንፈቅድላቸውና ፋታም ሳንሰጣቸው ልናስቆማቸው ይገባል  ዛሬ ላይ ባለ የሐዲስኪዳን ዘመን ላይ ነውና ያለነው ግርዛቱ የሥጋ ሳይሆን ጌታ የሰጠን የመንፈስን ግርዛት ነው  ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3 : 3  ፣ 1ኛ ጢሞቴዎስ 3 ፥ 14 _ 16   ፣ ቆላስያስ 2 ፥ 11 _ 15 ፤ ሮሜ 2 ፥ 29  መግረዣውም የኢያሱ ዘመን ባልጩት ወይም ስለት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በጽኑ ልንነግራቸውና ይህንኑ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረን ልናስታጥቃቸው ይገባል ዕብራውያን 4 ፥ 12 ፤ ኤፌሶን 6 ፥ 13 እነርሱም እንዲህ የሚሉት ይህንንም የሚያደርጉት የሥጋን ሰይፍና የመንፈስን ሰይፍ ጠቀሜታ ለሕይወታቸው በውል ለይተው  ስላላወቁ  ነው  ወገኖቼ ! የእግዚአብሔር ቃል በሌለበት ቦታ ሁሉ ያለው  የሥጋ ሰይፍ  ስለሆነ የእግዚአብሔር ቃል የሌላቸው ሰዎች  ሁልጊዜ የሚመዙት ጴጥሮስ የመዘዘውን የሥጋ ሰይፍ ነው በመሆኑም በዚህ ምክንያት ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን ብጥብጥ ይሆናል የተመዘዘው ሰይፍ ደግሞ የሥጋ ስለሆነ ገላጋይ እንኳ መሐል ሊገባ ችግር ነው በዚህም ሁኔታ ፖሊስ ሳይቀር ደርሶ የዘጋቸውን ያለጊዜያቸው የተከፈቱ ኪዮስክ ወይም ቡቲክ መሠል ቤተክርስቲያኖችን  በዘመኔ አውቃለሁ ሲከፈቱ በተጠሩ የክብር እንግዶች ሪቫኖቻቸው በመቀስ እየተቆረጡ በብዙ የሕዝብ ጭብጨባ ነው የተከፈቱት ሲዘጉ ግን  በሚያሳዝን ሁኔታ በሮቹ በፖሊስ ከማስጠንቀቅያ ጋር በሆነ መታሸግ ታሽገውና ሕዝብም ተበትኖ ተዘጉ በሆነውም ነገር በጊዜው ዓይኔ ያየና ጆሮዬም የሰማ በመሆኑ  ሃዘኔ እጅግ ጥልቅ ነበረ ውድ ወገኖቼ  ሆይ ለዚህ አሳፋሪና አስነዋሪ ጉዳይ የሚባለው ጌታ እግዚአብሔር ይቅር ይበለን  ይታደገን  ነው  ቤተክርስቲያንን እንደፈለግን እየሆንን ለግል ጥቅማችን የምንከፍታት የመገበያያ ጉሊታችን ወይም ሱቅ በደረቴ አይደለችም ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል ስለሆነች የምትቋቋመው ለሥጋዊ ጥቅምና ፍላጎታቸው ባደሩ አገልጋዮች ምኞት ሳይሆን በእግዚአብሔር ዓላማና ፈቃድ ነው መንጋው ደግሞ ታናሽም ቢሆን መንግሥትን ሊሰጠው የአባቱ ፈቃድ የሆነለት ስለሆነ ሁሉም ሰው እንደ መጠራቱ መጠን በነፍስ ወከፍ የመንግሥት ልጅ ተብሎ የተሰበሰበ የእግዚአብሔር መንጋ ነውና አገልጋዮች እንዲሁ ከሜዳ ተነስተው በዘልማድ እንደ ጠፍ ከብት የሚነዱት አይደለም ፣ ሊሆንም አይገባም የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 16 _ 20 ፤ የሉቃስ ወንጌል 12  ፥ 32 እና 33 ፤ ቆላስያስ 1 ፥ 13 እና 14  ቤተክርስቲያን ደግሞ የእውነት ዓምድና መሠረት ስለሆነች የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ናት ቅዱሳንም  በዚህ ቤት ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ ተጽፎላቸዋል 1ኛ ጢሞቴዎስ 3 ፥ 14 እና 15 ታድያ እኛ ቅዱሳን በተጻፈው በዚህ እውነት ልክ ስንኖር ነገሮች ሁሉ መልክ ይይዛሉ የተዛቡ ነገሮችም  ይስተካከላሉ ቤተክርስቲያንም እንደገና ወደ ትክክለኛ መንፈሳዊ ይዘትዋና መሠረትዋ ወደ ቀደመ ክብርዋና ማንነትዋም   ትመለሳለች እንደገናም ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቊጣም የዘገየ ይሁን የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና ተብሎ የተጻፈልን በመሆኑ ያዕቆብ 1 ፥ 20 እና 21  እውቀት በጐደለውና ባዶ በሆነው ቅንዓት ተሞልተው የሚነሱ ሰዎች በትክክለኛው የአገልግሎት ሕይወት ሊማሩ ፣ ሊለወጡ ሊስተካከሉና ሊቀረጹ ራሳቸውን ይሰጣሉ እንጂ ከዚህ በኋላ ባለና በሚመጣ ትውልድ መካከል እየደነፉ ፣ እየተቆጡ ፣ ጆሮም እየቆረጡ አገልግሎት ስለሌለ አያገለግሉም እያልኩ ነው አለበለዚያም ደግሞ ይሄ ሁሉ ቀርቶባቸው  ይሰናበታሉ ማለትም እንዳያገለግሉ ይሆናሉ  ለምን ስንል መንፈሳዊ ግልጋሎት የቃልና የኑሮ ምሳሌነት የታከለበት እንጂ ድንፋታና ቊጣ በተሞላበት የክተት ሠራዊት  በመጣልህና በወዮልህ መንፈስ ተሞልቶ ለጆሮ ቆረጣ የሆነ መነሣሣት አይደለም ያለፈው ዘመን ይብቃችሁ ተብለናልና ሮሜ 10 ፥ 1 _ 4 ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 4 ፥ 1 _ 4 ቤተክርስቲያንን ወደ ቀደመ መንፈሳዊ ይዘትዋና መሠረትዋ የሚመልሳት የሰዎች ቊጣና በእውቀትም ያልሆነ  የቅንዓት እርምጃ ሳይሆን መሠረታዊ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ነው ስለዚህ ልዩነት ሳይኖር ሁላችንም ድንፋታውንና ቀረርቶውን እኔ እበልጥ ባይነቱንና ምታ ነጋሪቱን ትተን  ሊገነባን ወደሚችለው ወደ እግዚአብሔር ቃል ትምህርትእንድንመለስ እግዚአብሔር ይርዳን መልዕክቴን ጨርሻለሁ ሰላም ሁኑ ተባረኩ

ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry 



ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ 

No comments:

Post a Comment