Thursday 2 June 2016

የመልዕክት ርእስ ፡- ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ ( መጽሐፈ መሣፍንት ምዕራፍ 16 በሙሉ )የመልእክት ርእስ ፡- ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ (መጽሐፈ መሣፍንት 16 ምእራፍ በሙሉ) ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ቃል ለሶምሶን የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባ ነበር ነገር ግን አልሆነም ደሊላ የተባለችው ሴትም ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ድምጽ እና የመምጣታቸውም ጉዳይ በሶምሶን ሕይወት ላይ በተለያየ ጊዜ እውን እስኪሆን ድረስ የምትጠብቅ ሴት ነበረች ነገር ግን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ የሚለው ድምጽ ለሶምሶን ከደሊላ ጋር ኩኩሉ አልነጋም ሲል የሚጫወተው የወዳጅነት ድምጽ ሆነበት በዚህም የማንቂያ ደወል ሊነቃ ስላልቻለ ይህንኑ ጨዋታ በተደጋጋሚ መጫወት ጀመረ መጽሐፍቅዱስ በጨዋታ ሜዳ የሚታገል ማንም ቢሆን እንደሚገባ ባይታገል የድሉን አክሊል አያገኝም ይለናል ስለዚህ በፋንታው ሶምሶን ውርደትና ሽንፈት ደረሰበት እንጂ የድሉን አክሊል በወቅቱ በዚያን ሰዓት አላገኘም ድሉ የደሊላና የፍልስጥኤማውያን ሆነ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እየተባለ በየጊዜው በደሊላ ሲነገረው የነበረው ነገር እውን ሆነ ታድያ አንዳንድ በጨዋታ መልክ ተለሳልሰው እና እንደ ቀልድ መስለው የሚነገሩን ነገሮች እውነት እላ ችሁአለሁ ወገኖቼ እውን ይሆናሉ እውን ሲሆኑም ደግሞ ይሆናሉ ስንል በማንጠብቅበት መንገድ ነው እንደገናም በሕይወታችን እውን ሲሆኑ አስከፊ ሁኔታን ይዘው ነው ይሄ ሊገባን ይገባል ታድያ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ልብ ልንል የሚገባው ሶምሶን በእርግጠኝነት ጠላት እንዳለበት ካወቀ ማድረግ የነበረበት ከደሊላ ጋር የነበረውን የኩኩሉ አልነጋም ጨዋታ ወዲያው በቅጽበት ማቆም ነበረበት ግን አላቆመም ወገኖቼ የኛም ችግር ከዚሁ የዘለለ አይደለም ማቆም የነበረብንን የኩኩሉ ጨዋታ ዛሬ ላይ ካላቆምነው በሁዋላ ላይ ከኩኩሉ ይልቅ መልኩን ቀይሮና እውን ሆኖ በሕይወታችን ሲመጣ ጊዜው የእኛ አይሆንምና በፍጹም ልናቆመው አንችልም ማቆም ካለብን ሁሉንም ነገር ማቆም ያለብን አሁን ነው ይህ ብቻ አይደለም ሶምሶን ጠላት እንዳለበት ካወቀ አሁንም ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እስኪባል መጠበቅ የለበትም እንደውም መጡብህ ሳይሆን ማጣባቸው መባል ነው ያለበት ለእርሱ ግን ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖ ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ ተባለ ይሁን እንጂ ከሶምሶን ይልቅ ለዚህ እና በዚህ ጉዳይ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ኢያሱ ነው ኢያሱ ያደረገው ነገር እንዲህ ነው ኢያሱም ከጌልጌላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው እያለ ከተናገረ በሁዋላ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ የለም ይለናል ኢያሱ ምእራፍ 10 በሙሉ አንብቡት እኛም ታድያ ለሶምሶን ሶምሶን ሆይ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ እንደተባለ ለእኛም በየስማችን እገሌ ሆይ ጠላቶችህ መጡብህ የምንባል መሆን የለብንም ይልቁንም በጠላቶቻችን ላይ ሌሊቱን ሙሉ ፈጥነን በመገስገስ የምንመጣባቸው የምናስደነግጣቸው የምንመታቸው እግዚአብሔርም የሚዋጋልን ሊሆን ነው የሚገባው ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ በጨዋታ ሜዳ እንደሚገባ ስንታገልና በትዳር ንግድ እራሳችንን ሳናጠላልፍ ስንቀር ማስተዋልም ሲኖረን ነው የተወደዳችሁ ወገኖች መልእክቱ እነዚህንና የመሳሰሉትን ሃሳቦች የጠቀለለ ነው በመልእክቱ እንግዲህ ተገልገሉ ተባረኩበት ተጠቀሙ ለሌሎችም ሼር አድርጉት ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

No comments:

Post a Comment