Wednesday 22 June 2016

የመልዕክት ርዕስ ፦ ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ ( 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 31 )የመልዕክት ርዕስ ፦ ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ ( 1ኛ ሳሙኤል 17 ፥ 31 ) መሰማት ዛሬ የብዙ ሰዎች ፍላጎትና ጥያቄ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ነው ብዙ ሰዎች ባሉበት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከሌላው ይልቅ በብዙ እንዲሰሙ ሌላው ቀርቶ አጠገባቸው ካለው ከወንድማቸው ወይም ከእህቶቻቸው ይልቅ አብልጠው እና በልጠው ተሽለውም እንዲሰሙ የሚፈልጉበት ጊዜ ላይ ያለን በመሆኑ የውዽድሩ መጠን ከመቼውም በላይ እየናረና ከፍም እያለ የመጣበት ሰዓት ላይ ደርሰናል በመሆኑም ይህ ሁኔታ በጊዜው እልባት ሊያገኝ ሲገባው መፍትሔ ሰጪ ጠፍቶ አንዱ ሌላውን ከሚሰማው ይልቅ በዚያው ልክ አንዱ አንዱን እንዳይሰማው የሆነበት እንሰማማ ሲሉ በአንድ ጠረጴዛ የተቀመጡ ቢሆኑም እንኩዋ የሚቀመጡት ተደማምጠው መፍትሔ ላይ ለመድረስ ሳይሆን ለክርክርና ለፍጭት ለድብድብ አልፎም ለመለያየት ነው የዳዊት መሰማት ግን ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በብዙ የተለየ ነው ዳዊት የተናገረው ቃል የተሰማው ልሰማ ወይንም የእኔ ቃል ብቻ ይሰማ በሚል መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሳይሆን ጌታ እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲሰማ ስለፈቀደለት ነው ታድያ ዛሬም በዘመናችን እንዲሰሙ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተፈቀደላቸው ሁሉ የቱንም ያህል ተቃውሞ ቢደርስባቸው ፣ ድምጻቸውም እንዳይወጣና እንዳይሰሙ ቢደረጉም እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ይሰማሉ ቃላቸው እስከ ምድር ዳርቻ የወጣ ሰዎች መሰማት ስላለባቸውና ሰዎችም ስለፈቀዱላቸው የተሰሙ ሳይሆኑ እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው የተሰሙ ነበሩ ( መዝሙር 19 ፥ 4 )እግዚአብሔር ሲፈቅድ የማይሰማ ማንም የለም ታድያ ይሄ ትምህርት የሚያስታውሰን የዳዊትን የተናገረውን ቃል መሰማት ብቻ ሳይሆን ቃሉ በንጉሥ ሳኦል ሳይቀር የተሰማው ዳዊት ወደዚህ መሰማት የመጣበትን መንገድና ዝርዝር ሁኔታ ትምህርቱ ይጠቁማል ስለዚህ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ ረዘም ብሎ ሰፋ ያለ ቢሆንም ታግሳችሁና ጊዜ ወስዳችሁ እንደሚገባ ብትሰሙት በብዙ ትጠቀማላችሁ ብዬ አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry Servant of Lord Yonas Asfaw

No comments:

Post a Comment