Wednesday 16 March 2016

ትምህርት አምስት ፦ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በተስፋ ቃል የሆነ የጸጋ መነሣሣትን ያደርጋል ( ዘጸአት 12 ፥ 25 ፤ ...የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች የትምህርት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በተስፋ ቃል የሆነ የጸጋ መነሣሣትን ያደርጋል ( ዘጸአት 12 ፥ 25 ፤ ገላትያ 4 ፥ 1 _ 7 ) 1ኛ ) ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል አዲሲቱን ምድር ሊሰጣቸው የጸጋ መነሳሳትን አድርጎላቸው ነበር ሲናገራቸውም ይህንን አለ እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር እንደተናገረ ወደሚሰጣችሁ ሀገር በገባችሁ ጊዜ ይህን አምልኮ ጠብቁ አላቸው ዘጸአት 12 ፥ 25 እንደገናም የተስፋው ቃል እንዲፈጸም እርሱን ማክበር እና ከልብ መለመንም ይገባል በጥላቻ ላሉና ለማይታዘዙ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ዋና ነጥብ አስቀመጠ ገላትያ 3 ፥ 15 _ 29 2ኛ ) እግዚአብሔር በተስፋ ቃል ስለገባው የዘላለም ሕይወት ክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ ሊታመን ያስፈልገዋል ዕብራውያን 9 ፥ 15 3ኛ ) ጌታ እግዚአብሔር አዲሲቱን ምድር ሊሰጣቸው የጸጋ መነሣሣትን ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ያደረገው ዘጸአት 12 ፥ 25 በሐዲስ ኪዳንም ለገላትያ ክርስቲያኖችን ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባርያ አይደለህም ሲል ለእነዚሁ የገላትያ ክርስቲያኖች ልጆች ስለሆኑ እግዚአብሔር አባ አባት የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባቸው ውስጥ ላከ ስለዚህ ልጅ ከሆኑ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች መሆናቸውን አረጋገጠላቸው እንደገናም ይህ ጉዳይ በሕይወታቸው የማያጠራጥርና እውነተኛ ስለሆነ ይበልጥ አምነው በእነዚህ እውነቶች ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆሙ በተስፋው ቃል የሆነ የጸጋ መነሳሳትን ይሰጣቸዋል ለምን ስንል አንደኛው ሃሳብ ሕግንና የጸጋ መዳንን ለይቶ ካለማውቅ የተነሣ ሕግን ወደመጠበቅ ሕይወት የተመለሱ በመሆናቸው ነው ሁለተኛው ሃሳብ ደግሞ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባርያዎች ሆነው ሊገዙ በዚህም ጉዳይ አሁንም ወደኋላ የተመለሱ ስለሆኑ ነው ይህ ደግሞ ደካማ የሚናቅና የመጀመርያ ትምህርት እንደሆነ የክፍሉ ሃሳብ ይናገራል ከዚህም ሌላ ቀንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ የሚጠብቁ በመሆናቸው ስለዚህ ጳውሎስ ምንአልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችችኋለሁ ይላቸዋል 4ኛ ) ለዚህ ሁሉ የመመለስ ምክንያቶቻቸው አርነታቸውን ሰልለው ባርያዎች ሊያደርጓቸው የሚፈልጉ ስለነበሩ ነው እነዚህ ሰዎች ወደራሳቸው ሊወስዱአቸው የሚተጉ ፣ መውሰዳቸው ግን ለመልካም ያልሆነ ሰዎች ናቸው ፍላጎታቸውም እናንተን ከእኛ ነጥለው የራሳቸው ሊያደርጓችሁ ስለወደዱ ነው እያለ ሐዋርያው ይነግራቸዋል ገላትያ 2 ፥ 4 ፣ ገላትያ 4 ፥ 17 4 ) ታድያ እነዚህ የገላትያ ክርስቲያኖች ከእነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች የስህተት ትምህርት ሊያመልጡ የሚችሉበት ትልቁ መንገድ ቃሉን በማወቅ የሆነ አርነት መሆኑን ከጠቆማቸው በኋላ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ ይላቸዋል ይሁን እንጂ አርነት የሚወጡት በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው እና የቃሉንም እውነት አውቀው በቃሉ ሊኖሩ ውሳኔ ሲያደርጉ ብቻ መሆኑን ከጠቆማቸው በኋላ የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ አርነት የመውጣትን መነሣሣት እንዲያደርጉ ያበረታታቸዋል ገላትያ 5 ፥ 13 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 31 _ 32 5ኛ ) ሐዋርያው በገላትያ ክርስቲያኖች ሳይቀር ወደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያንም ተሻግሮ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያንን ስለ መንፈሳዊ ነገር እንዲያውቁ ውዴታው መሆኑን እየጠቆማቸው በቃሉ የሆነ የጸጋ መነሣሣትን ይሰጣቸዋል 2ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 1 _ 3 ለምን ስንል እነዚህ ቅዱሳን አሕዛብ ሳሉ በማናቸውም ጊዜ እንደሚመሩ ድምጽ ወደሌላቸው ጣኦታት እንደተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ በማለት ያስታውሳቸዋል ሐዋርያው ታድያ ወደ እነዚህ ጣኦታት እንደተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ ሲላቸው በድሮና በመጀመርያ ትዝታ ሊያኖራቸው ወይም ሊያስቀምጣቸው ፈልጎ ሳይሆን በአንድ ወቅት የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በተለያዩ ነገሮች ተገፋፍተው የማይናገሩ ጣኦታትን ያመልኩ ስለነበር አሁን ግን ባገኙት የልጅነት መንፈስ ከነዚህ ጣኦታት የተለያዩ በመሆናቸው በመንፈስቅዱስ እንዲመሩና በጨመረ እውቀት እንዲመላለሱ ለማስገንዘብ ነው ይህንን እውነታ የነገራቸው 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 19 እና 20 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 1 _ 11 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 17 እና 18 ፤ ሆሴዕ 4 ፥ 6 6ኛ ) በዮሐንስ መጥምቁና በጌታችን በኢየሱስ መካከል ያለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ Transition Period ወይም የሽግግር ጊዜን የሚጠይቅ በመሆኑ ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌል እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ ይለናል የማርቆስ ወንጌል 1 ፥ 14 እና 15 ስለሆነም እኛም በዚህ እውነት ላይ ተመርኩዘንና በተስፋ ቃል የሆነ የጸጋ መነሣሣት አድርገን በዮሐንስ ትምህርትም ሆነ በሕግ አስተማሪዎች ፣ በሌሎችም በዘመናችን ባሉ የሃይማኖትና የሥርዓት አስተማሪዎች ወግና ልማድ እንዲሁም ትምህርት ውስጥ ካለን ሽግግር አድርገን ወደ ክርስቶስ ትምህርት በፍጥነት ልንመጣ ይገባል 2ኛ ዮሐንስ 9 _ 11 7ኛ) ክርስቶስ ፦ ገና ደካሞች ሳለን ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና …………… እንደገናም ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለእኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ሮሜ 5 ፥ 6 _ 11 ስለዚህ ይህንን እውነታ ካወቅንና ቃሉንም ከተረዳን ማንንም በማያሻማ መልኩ ጊዜው አሁን የክርስቶስ እና የእኛ ስለሆነ ጌታን የሕይወታችን ጌታና አዳኝ አድርገን በመቀበል አሁኑኑ ዛሬ ነገ ሳንል መዳን አለብን ራዕይ 12 ፥ 10 _ 12 ፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 ፣ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ወገኖቼ ታድያ እነዚህ ጠቃሚ ነጥቦች በቪዲዮ የተለቀቀውን መሠረታዊ ትምህርት ይበልጥ ጉልህ አድርገው የሚያሳዩ ስለሆኑ ከዚህ በመቀጠል እነዚህኑ የሚለቀቁትን ቪዲዮዎች በየተራ እየተከታተላችሁ በመስማት ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment