Saturday 26 March 2016

የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ በተስፋ ቃል መፈተን በተስፋ ቃል ከተፈተኑት መካከል ፦ 1ኛ) አብርሃም ነው አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው ይለናል ዕብራውያን 11 ፥ 17 እና 18 ታድያ የአብርሃም ፈተና እንዲሁ ይስሐቅን በእምነት የማቅረብ ፈተና አይደለም በውስጡ ብዙ የመስዋዕትነት ሕይወት አለው ይህንንም በዘፍጥረት 22 ፥ 10 ጀምሮ እስከ 19 ቊጥር ድረስ የተጻፈልን በመሆኑ ይህንን ሁኔታ በዚሁ ክፍል በዝርዝር እናገኘዋለን እንዲሁም በዘፍጥረት 12 ፥ 10 _ 20 ላይ በምድር ራብ በሆነ ጊዜ አብራም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ መውረዱን የክፍሉ ሃሳብ ይነግረናል ይህ ራብ ደግሞ የጸና ነበርና ወደ ግብጽም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እህቴ ነሽ በማለትና እህቱም ነኝ እንድትል ሦራን በማሳመን ከግብጽ ሰዎች አስደንጋጭ ሞት ሚስቱ በሆነችው ነገር ግን እህቱ ነኝ በዪ ባላት በሦራ ምክንያት የማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ሦራ ለግብጹ ንጉሥ ለፈርኦን ሚስት ልት ሆን የተወሰደች በመሆንዋ እውነተኛውን ጉዳይ የሚያውቀው እግዚአብሔር በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የአብራምን ሚስት ሦራን ለዚሁ ለአብራም አተረፈለት ስለዚህም ንጉሥ ፈርኦን አብራምን ጠርቶ ይህ ያደረግህብኝ ምንድር ነው ? እርስዋ ሚስት እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም ? ለምንስ፦ እኅቴ ናት አልህ ? እኔ ሚስት ላደርጋት ወስጄአት ነበር አሁንም ሚስትህ እነኋት ይዘሃት ሂድ ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው ይለናል 2ኛ) ዮሴፍ ነው በመዝሙር 104 (105)፥ 16 _ 19 በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ በፊታቸው ሰውን ላከ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ እያለ ይናገራል እስር ቤት እግረ ሙቅም ሆነ ሰንሰለት መራርነት ያለበት የጨለማ ሕይወት ነው ይሁን እንጂ ታድያ እግዚአብሔር በዚያ ስፍራ ለዮሴፍ ምሕረትን ያበዛለት ቢሆንም ዮሴፍ ግን ይህንኑ የተስፋ ቃል በመጠበቅ ምክንያት በሕይወቱ የተፈተነ ነበር ዘፍጥረት 39 ፥ 21 ፤ ዘፍጥረት 40 ፥ 15 ፤ ዘፍጥረት 40 ፥ 1 _ 23 3ኛ ) አብርሃምና ከአብርሃም በኋላ የመ ጡ የእምነት አባቶች ፈተና መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ስለ አብርሃም ሲናገር አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና ይለናል ዘፍጥረት 11 ፥ 8 _ 10 ከአብርሃም በኋላ ስላሉ የእምነት አባቶች ሲናገር ደግሞ እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና ይለናል ዕብራውያን 11 ፥ 13 _ 16 ይመልከቱ ታድያ እነዚህ አባቶች በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ፍጹማን የሆኑት በእኛ ነው ይህም እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና ዕብራውያን 11 ፥ 39 እና 40 ን በድጋሜ ይመልከቱ 4ኛ ) የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ እግዚአብሔር ፈቃዱ አይለወጥም ስለዚህም ይህን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ጌታ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመካከል በመሃላ ገብቶአል ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ በማለት የዕብራውያን ጸሐፊ ዘግቦልናል ዕብራውያን 6 ፥ 17 _ 20 በተስፋ ቃል ስንፈተን ፦ ሀ) በመጠበቅያችን ወይንም በማማችን ላይ መቆም ያስፈልገናል ዕንባቆም 2 ፥ 1 _ 3 ፤ ዕብራውያን 10 ፥ 37 _ 39 ለ) መጽናት ያስፈልገናል ዕብራውያን 10 ፥ 36 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 11 ፥ 2 እና 3 ፤ ራዕይ 22 ፥ 12 እና 13 ፣ 20 ሐ ) መትጋት ያስፈልገናል ዕብራውያን 6 ፥ 9 _ 12 ፤ የሉቃስ ወንጌል 12 ፥ 35 _ 48 መ) ለአንዳንዶች የተስፋውን ቃል አምኖና ከሩቅ ተሳልሞ መሞት ቢሆንም ለሌሎች ግን የተስፋውን ቃል ማግኘት ነበር ዕብራውያን 11 ፥ 13 ፣ 33 ቅዱሳን ወገኖች ከዚህ ጽሑፍ ባሻገር ይህንኑ ትምህርት በብዙ ሊያብራራ በቪዲዮ የተለቀቀ ትምህርት ስላለን ይህንኑ ትምህርት እየገባችሁ በመከታተል ለሌሎችም እንድታሰሙ ሼር እንድታደርጉ ከታላቅ አክብሮት ጋር በትሕትና እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ፣ ኑሮአችሁንና ሕይወታችሁን ሁሉ ይባርክ አሜን Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment