Friday 28 August 2015

006 የባሎች ሃላፊነት The Husband`s Responsibility  ባሎች ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በወደደበት መንፈስ ሚስቶቻቸውን መውደድ አለባቸው  ክርስቶስ ራሱን ለቤተክርስቲያን እንደሰጠ እራሳቸውን ለሚስቶቻቸው መስጠት አለባቸው  የባሎች ራስን ለሚስቶቻቸው የመስጠት ጠቀሜታ ለሚስቶች እውነተኛ ወዳጅነትን ጥልቅ ፍቅርን ለማሳየት ነው  የባል የመጀመርያው እና ትልቁ ሃላፊነት በማይወድቅ ፍቅር ሚስቱን መውደድ በቅድሚያ ባሎች ይህንን ለማድረግ መሞከር አለባቸው  ነገር ግን ጥረታቸው ጊዜ በመስጠት ያነሰ ነው  ባሎች ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደደ መውደድን መገንዘብ ብቻ ሳይሆን ለሚስቶቻቸው የጠየቁትን ዋጋ መስጠት ሁልጊዜ መጀመር አለባቸው  Men often begin to take their wives for granted , not realizing they are to love them "as Christ loved the church"  ይህ ታድያ ማለቅያ የሌለው የፍቅር አጥር እግዚአብሔር በከፍተኛ ደረጃ የደለደለው ከበድ ያለ ፍቅር ውስጥ መግባትን ያመጣል  ይህ ዓይነቱ መንገድ ደግሞ ክርስቶስ ለሙሽራዋ ቤተክርስቲያኑ የሚጠነቀቅበት መንገድ ነው  ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ፍቅሩን አያቆምም ፣ አይተውም ነገር ግን ይቅር ይላል ይረዳል ከሚስቱ ጋር ሆኖ በትዕግሥቱና በቻይነቱ አብሮ ይሠራል  Christ never gives up on the church but rather forgives , understands , is patient with tolerates and works with his wife to be  ክርስቶስ ከቤተክርስቲያን ጋር እንዴት እንደሚሠራ ያወቀ ባል እንዴት ሚስቱን ማከም ማዘጋጀት እንዳለበት ማወቅ አለበት ኤፌሶን 5 ፥ 28 _ 31  ባል በቤት ውስጥ ራስ ሆኖ ትክክለኛ የመሪነቱን ቦታ ለመያዝ ከእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ያለን የባል ሥልጣንና መረዳት ሊኖረውና ሊይዝ ያስፈልጋል 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 3  ጥቂት ባሎች በቤተሰብ ውስጥ ባለ የአባትነት መሪ ሥልጣን ቦታ ክፉና ያረጀ ጊዜ ያለፈበት ዘመናዊ ያልሆነ ሆነው ይታያሉ ይስተዋላሉ  Father`s leadership position withn the family is evil and outdated  እግዚአብሔር ለባል በሰጠው ቦታ ሚስቱንና ልጆቹን በፍቅርና በጨዋነት እንዲመራ ትከሻውን ሰፊ የሚያደርግበት ኃላፊነት ነው  እግዚአብሔር መሠረታዊና መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርት ያለበት የቤተሰብ አቋም አውጥቷል ቲቶ 2 ፥ 1 _ 5 ከዚህ የቃሉ መመርያ ባሻገር ጌታ እግዚአብሔር በምንሰማው የቪድዮ ትምህርት ይባርከን አሜን የተወደዳችሁ ወገኖች የባሎች ሃላፊነት ( The Husband`s Responsibility ) የሚለውን ትምህርት እንግዲህ በክፍል ስድስት ያሬዳዊና መንፈሳዊ ዝማሬ እናጠቃልላለን የክፍል ሰባት ትምህርታችን ደግሞ የሚስቶች ሃላፊነት (The Wife`s Responsibility ) በሚል አርስት የሚጀምር ይሆናል ይህንንም ትምህርት በዚህ መልኩ በኦድዮና በፓወር ፖይንት ሥዕላዊ መግለጫ መረጃነት ድጋፍ እየሰ ጠን የምናቀርበው ስለሆነ በማስተዋል እንድትከታተሉት ለማሳሰብ እንወዳለን ጌታ ለዘላለም ይባርካችሁ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment