የምንጥሳቸው ነገሮች B Pastor Miki ጨካኝ የእግዚአብሔር ባሮች ፣ የማያመቻምቹ ፣ የማይገላመጡ የተነሱበት ዘመን ላይ ስለደረስን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ምን አሉ የሚለውን ሳይሆን ምን አለ የሚለውን የሚሰማ ፣ ወሬን የማይሰማ ትውልድ ስለተነሳ ክብሩ ለጌታ ይሁን እንዲህ ያለ ትውልድ ጥሶ የሚወጣ ነው እንዲህ ያለ ትውልድ ፋሬስ ነው እግዚአብሔር ያለንን ለምነንና ተለማምጠን ፣ እጅ ነስተንና ጸባይ ገዝተን ሳይሆን ጥሰን እንወርሳለን የተወሰነልንን እነ ዛራ አይነጥቁንም የሰውን ወሬ የሐሰት ትንቢትንና የሰው መላምትን እንዲሁም የሰዎች ግምትን ጥሰን እንወርሳለን መጋቢ ሚካኤል ወንድሙን እግዚአብሔር ይባርከው
No comments:
Post a Comment