Wednesday, 19 December 2018

Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...ይህቺ ናት ርትዕቷና ቀጥተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ተብላ የሚፎከርላት እንግዲህ :: መጨረሻዋ ይሄ ሆነ :: ጉድ አይሰማም አይባልምና አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የማይከበሩባት ፣ ጉሮሮአቸው ታንቆ የሚደበደቡባት ፣ መንፈሳዊ መሪዎች የማይከበሩባት እና የማይደመጡባት ፣ ሊያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አረጋዊ አባትና የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የተደበደቡባት ቤት ሆነች :: ወገኖቼ የእስራኤል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ፣ አናቂ ቁጥር 1 ሽፍቶች መነኮሳትን እስር ቤት ባይወስድ ፣ በቤተመቅደሱ ውስጥም የነበረውን ድብድብ ባያስቆም ፣ ጉሮሮአቸው የታነቀው ምስኪኑ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ለሕልፈተ ሕይወት በተዳረጉ ነበር :: ወገኖቼ እስቲ አንድ ጊዜ ይህንን ሁኔታ ቆም ብላችሁ አስቡት የራስ ሀገር ባልሆነ በኢየሩሳሌም ከአንድ ትልቅ ገዳምና የኃይማኖት ተቋም ይሄ ድርጊት ሊፈጸም ይገባልን ? የሦስት ሺህ ዓመት ክርስትና አለኝ የምትለዋ ይህቺ ቤተክርስቲያንስ በዚህ አሳፋሪ ጉዳይ ስሟ በዓለም ዙርያ ሊናኝና ሊነሳስ ይገባ ነበር ? ታድያ ለዚህ እኮ ነው እኛም አፋችንን ሞልተን አሁን ላይ ላለችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ ያስፈልጋታል የምንለው :: በሆሴዕ 4 ፥ 6 - 8 በተጻፈው ቃል መሠረት ከምዕመኖችዋ በፊት ያሉት ካህናትዎችዋ በደሙ የተገኘውን የኃጢአት ሥርየት ለማግኘት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በነፍስ ወከፍ የግል አዳኛቸው አድርገው ዛሬ ነገ ሳይሉ እና ሳይሞቱ በምድር ላይ አሁኑኑ ድህነትን ተቀብለው ቢገኙ ፣ የዳነ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላኩም መንፈስ የታጠበ ፣ የተቀደሰና የጸደቀ ስለሆነ ዓመጸኛ ተሳዳቢ ሴሰኛ ነጣቂ ተደባዳቢ ገዳይና የመሣሠሉትን አይሆኑም በ2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 9 - 11 የተጻፈውን ቃል በማስተዋል እናንብበው :: ቀራጩ ዘኬዎስ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ በቀረጥ ሰብሳቢነቱ አሁን ከዘረዘርኳቸው ተርታዎች የተመደበ ሰው ነበር :: ነገር ግን ኢየሱስን ይዞ ወደ ቤቱ በመግባት ዘኬዎስ ግን ቆሞ ይለናል ቃሉ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆነ አራት እጥፍ እመልሳለሁ ሲል ልባዊ ኑዛዜውን እንዳቀረበና ኢየሱስም አሁን ለቤቱ መዳን እንደሆነለት አውጆ የአብርሃም ልጅ ነህ እንዳለው እንመለከታለን የሉቃስ ወንጌል 19 ፥ 1 - 10 :: ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል እንደሚል ቃሉ ሮሜ 4 ፥ 5 የሚያስደንቀው እውነት ኢየሱስ ስለበደላችን የሞተ እኛንም ስለማጽደቅ የተነሣ ነውና በእርሱ በማመናችን ምክንያት ብቻ እምነታችንን ጽድቅ አድርጎ ይቆጥረዋል ሮሜ 4 ፥ 22 - 25 :: ለዚህም ነው ዘኬዎስን እውነተኛ ንስሐ በመግባቱ ብቻ ተቀብሎ መዳንን የሰጠው :: ወገኖቼ ሆይ ጽድቃችን ወይም ሥራችንማ ይኸው አረጋዊ ጳጳስ ሳይቀር እስከ መደብደብ ደርሶ በእግዚአብሔር ፊት አላቆመንም :: ይኸው ታየ ኦኮ በቃ ! ስለዚህ ትምክህታችን ጽድቃችን ቅድስናችንና ቤዛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 30 እና 31 ን እንመልከት :: መልዕክቴን ስጠቀልለው አሁን ላይ ያለሽው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚበጅሽ አንድና አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ነውና ወደ እግዚአብሔር ቃል ፊትሽን መልሺ ስል በወንድማዊና አባታዊ ምክሬን ልሰጥሽም ሆነ ላስገነዝብሽ እወዳለሁ:: በኢሳይያስ መጽሐፍ እንደተጻፈው በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ በማለት ይናገራል ትንቢተ ኢሳይያስ 2 ፥ 2 - 5 ይመልከቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ከወንድሞቼ ጋር በመነጋገር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መሪነትን አገልግሎትንና ክህነትን ሌሎችንም ጉዳዮች መሠረት ያደረገ ሰፋ ያለ ትምህርት ይዘን በቪዲዮ ልንቀርብ እንችላለን :: እስከዚያው ግን ይህቺን መልዕክት በማንበብ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ለወገኖቼ ትቻለሁ :: ሌላው መናገር የምፈልገው ወንድምህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ ነውና ይሄ ውሽንፍር ወደ ወንጌላውያኑም ቤተክርስቲያን ከሞላ ጎደል ጎራ ያለ በመሆኑ ይፋ ሆኖ ባይገለጥም በአንዳንድ ደካማና ያልበሰሉ ፓስተሮችም ሆነ ነቢያት እየታየ ያለ ክስተት ሆኗል ስለዚህ በአጠቃላይ የክርስቶስ ስም በእኛ ምክንያት እንዳይሰደብ ሁላችንም ልናስብበት ይገባል የሚለውን ምክር ልሰጥ እፈልጋለሁ :: ጌታ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከጸአተ ግብጽ ኦርቶዶክሳዊና ሐዋርያዊ የተሃድሶ አገልግሎት

Ethiopia:{ እጅግ አሳዛኝ መረጃ } አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ተደበደቡ! ግን ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እስኪገሎቸው ነው...

No comments:

Post a Comment