Thursday, 27 December 2018

የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ከዚህ በመቀጠል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ምክንያት በማድረግ አሁንም በድጋሜ መልዕክትን ወደ እናንተ ይዤ ቀርቤያለሁና ተከታተሉ የመልዕክት ርዕስ ፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና የዕለቱ የምንባብ ክፍል ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ( የማቴዎስ ወንጌል 2: 1 - 2 ) 1ኛ ) እነዚህ ሰዎች ሊሰግዱ መጥተው የቀሩ አልሆኑም ፣ ንጉሥ ሄሮድስም አላስቀራቸውም ፣ ኢየሱስ ጋር መጥተው ሰገዱለት ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት ( የማቴዎስ ወንጌል 2 : 11 ) 2ኛ ) ኢየሱስ ከተወለደ ጀምሮ ንጉሥ ነው ደግሞም የሚሰገድለት ነው :: ከሞት ተነስቶና ሞትን አሸንፎ ብቻ አይደለም የተሰገደለት በታንኳይቱም የነበሩት፦ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 14 : 33 ) እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 9 ) እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ( የሉቃስ ወንጌል 24 : 52 ) በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ ( ራዕይ 5 : 11 - 14 ) 3ኛ ) ኢየሱስን አንጠራጠረው ፣ ንጉሣችንና አዳኛችንም ነውና አንካደው ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ ( የማቴዎስ ወንጌል 28 : 17 ) ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት ( የማርቆስ ወንጌል 15 : 19 ) ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል 2ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 12 ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment