Thursday, 28 June 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 9 ) ክፍል አራት ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳየማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቊጣ ያድነንየውዳሴ ማርያም መርገፍ ማሳረጊያ ወትቤ ማርያም ከመባሉ በፊት ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ የሚባል ነው ገጽ 132 ወይም በአሥመራው እትም ገጽ 399 የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ ወደ አማርኛው ስተረጉመው የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ ቁጣ ያድነን የሚለውን ትርጉም ይሰጠናልና ይህ የዛሬው ትምህርት ለዚህ ሃሳብ የማሳረግያና የማጠቃለያ ትምህርት ነው በዛሬው ዕለት በፌስቡክ የላይቭ ቪዲዮ እንደ ትተከታተላችሁት የኢየሱስ ቁጣው ምክንያታዊ መሆኑን የሚገልጹ መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃን የያዙ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል እንደገናም ከዚሁ ጋር በንጽጽር ፈሪሳውያን ተቆጥተዋል ፣ ሰውንም ለመውገር ድንጋይ አንስተዋል ይሁን እንጂ የእነዚህ የሕግ መምህራን ቁጣቸውም ሆነ ለመውገር ድንጋይ ማንሳታቸው ሌላውን ሳይሆን እነርሱን የሚመለከትና ከእነርሱም የሚጀምር መሆኑን ፣ በአጠቃላይ ከእኛ ያልጀመረ ፣ እኛንም ያላማከለ ቁጣም ሆነ ፍርድ ለሌላው ሊሆንና ሌላውንም ሊበይን እንደማይችል በዝርዝር አይተናል በተጨማሪም እኛ ሌላውን እንቆጣለን ፣ በሌላውም ላይ እንፈርዳለን ስንል በተነሣሣንበትና አፋችንንም ሞልተን በተናገርንበት አንደበታችን በትላንቱ ዘመን ለዳዊት የተላከው ዮናታን ሳይሆን ዛሬ ላይ የኢየሱስን ቦታ ተክቶ በምድር ሁሉ ላይ በምልዓት የሚሰራው መንፈስቅዱስ መልዕክቱን ወደየግል ሕይወታችንና ወደ ራሳችንም ጭምር አዙሮ ያ ሰው አንተነህ ይለናል ያኔ ምን እንል ይሆን ? እግዚአብሔር ሆይ ተሳስተሃል !ወይንስ እኔ አይደለሁምና ሌላ ሌላ ሰው ነው ልንል ?መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ ለማንኛውም ግን ለሕይወታችን ጥቅምና ጥሩ ማስገንዘብያ እንዲሆን 2ኛ ሳሙኤል 12 ን በሙሉ እንድታነቡ ከትልቅ አክብሮት ጋር እጋብዛለሁ በዚህ ውስጥ ታድያ ዳዊት ሙሉ ለሙሉ ስሕተቱን አምኖ ናታንን እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው ናታንም ዳዊትን እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል አትሞትም አለው ይለናል እኛስ ዛሬ በናታን ቦታ ብንሆንና እንደ ዳዊት ያሉ ሰዎች ጥፋትን አጥፍተው ፣ ጥፋታቸውንም አምነው እግዚአብሔርን በድያለሁ ሲሉ ወደ እኛ ቢመጡ የምንሰጣቸው መልስ ምን ይሆን ? አሁንም መልሱን ለእናንተ መተው እፈልጋለሁ ሆኖም ግን ከዚህ የብሉይ ኪዳን ምንባብ አኳያ ዛሬ ላይ ያለነው በሐዲስ ኪዳን ዘመን ውስጥ በመሆኑ የበደሉ ሰዎች እግዚአብሔርን በድያለሁ ሲሉ የሚመጡትና ኃጢአታቸውንም የሚናዘዙት ለዚሁ ለጌታችን ስለሆነ ይሄው እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን በኩል ለሁሉም የሚሆን መልስ አለው ወደ ተነሳንበት የመጀመርያው ሃሳብ ስንገባ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቁጣ የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲ እንደተናገረው መዓትን የተሞላ ቁጣ ሆኖ የማርያምም ሆነ የሌሎች ቅዱሳን ምልጃ የሚያስፈልገው አይደለም ከዚህ ይልቅ ቁጣው ምክንያታዊ በመሆኑ ሚዛናዊ ነው ከዚህም የተነሳ ነው እንግዲህ ፦ ___ የማዳንህን ጋሻ ስጠኝ ተግሣጽህም አሳደገኝ ( 2ኛ ሳሙኤል 22 ፥ 36 ) ___ ለደኅንነቴ መታመኛን ሰጠኸኝ ቀኝህም ትረዳኛለች ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች ተግሣጽህም ታስተምረኛለች ( መዝሙር 18 ፥ 35 ) ___ መገሰጽስ እግዚአብሔር ገሰጸኝ ለሞት ግን አልሰጠኝም ( መዝሙር 118 ፥ 18 ) ___ ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው ሞገሱ ለሕይወት ዘመን ልቅሶ ማታ ይመጣል ጠዋት ግን ደስታ ይሆናል ( መዝሙር 30 ፥ 5 ) ___ በዚያም ቀን አቤቱ ተቆጥተኸኛልና ቁጣህንም ከእኔ መልሰሃልና አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ ( ትንቢተ ኢሳይያስ 12 ፥ 1 ) በማለት እነዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የተናገሩት የምናነበውን ቃል እግዚአብሔር ይባርክልን ለበለጠ መረጃ የተለቀቀውን ቪዲዮ ተከታተሉ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment